TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስምቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የካፌ አገልግሎቱን እንዲያሻሽል ጠየቁ። ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮ. በላኩት በፎቶ የተደገፈ መረጃ የዩኒቨርሲቲው የካፌ አግልግሎት እጅጉን ደካማ እንደሆነ ገልፀው ተቋሙ ተገቢውን ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው መፀዳጃ አገልግሎት ከአንድ ትልቅ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ እንደሆነ አንስተዋል። የዩኒቨርሲቲው የመፀዳጃ አገልግሎት ተማሪዎችን ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ መፍትሄ እንደሚያስፈልገውም ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ተማሪዎች እና የቴክኖሎጂ(አዋሮ ካምፓስ) ተማሪዎች ወደ ግቢው የገባው የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ሙሉ ለሙሉ ለቆ እስካልወጣ ድረስ ትምህርት አንማርም በማለት ግቢውን ለቀው ወደየ ቤታቸው እየሄዱ እንደሆነ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተላከልኝ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ ፦ ሻ.ቃ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ አውሮፓ በስደት ላይ የነበሩ 118 ኢትዮጵያውያን በዛምቢያ መንግሥት ቁጥጥር ስር እንዳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለሥ አለም ለሪፖርተር ገለፁ። የኢትዮጵያ መንግሥትም ታሳሪዎችን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
❗️ጥንቃቄ አዘል መረጃ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ተማሪዎች❗️

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በር አካባቢ ባጃጆች በመጠቀም ከፍተኛ ዝርፊ እየተፈፀመ መሆኑን ከተማሪዎች እየተላከው መረጃ ይጦቅማል።

ዝርፊያው የሚካሄደው ባጃጅ ውስጥ 3 ሆነው በመቀመጥ 1 ሰው ማሀላቸው እንዲገባ በማድረግ በግዳጅ ወዳልተፈለገ ቦታ በመውሰድ እና ባጃጅ ውስጥ የተቀመጠውን ተሳፋሪ ቂስ በመበርበር ነው። በርካታ ተማሪዎች በዚህ በተቀነባበረ የወንጀል ድርጊት ስልካቸውን እና ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል።

የጎንደር ከተማ ፖሊስ ይህን ጉዳይ የሚያውቀው ከሆነ በቦታው ልዩ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብ ላጠፉት ጥፋት ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ አለበት ባይ ነን። እንዲሁም ቦታውን ከወንጀል በማፅዳት ለተማሪዎች እና ለአካባቢው ነዎሪዎች ምቹ እንዲያደርግም እንጠይቃለን።

ምንጭ ፦ G

@tsegabwolde @tikvahethiopia
💚💛❤️ቀላል ይሆናል💚💛❤️

ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ
የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት እርስቴ
ቀላል ይሆናል ቀና አድርገኝ ፅናቴ፡፡

ቀላል ይሆናል ቀላል ይሆናል

ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ
አለ ይሄ ሰው ሁሉም አከተመ
ደቂቅ ተስፋን ካየናት አርቀን
ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን፡፡
ቀላል ይሆናል ቀላል ይሆናል

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ፈራን ፍቅር ፈራን
ልጅነት የለገሰንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ በረቂቅ ያለበሰንን
በመለኮት የቀባንን
ህብረት ፈራን
ፍቅር ፈራን፡፡

💚💛❤️ቀላል ይሆናል💚💛❤️

ቴዲ አፍሮ

ፍቅር ያሸንፋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሶማሌ ክልል ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ሀዘናቸውን ገልፀዋል እንዲሁም በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታም አሰምተዋል። ዛሬ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደሌለ ከግቢው ተማሪዎች የተላከልኝ መረጃ ይጠቁማል።

ምንጭ ፦ ዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢1
የስር ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ከልክሏቸው ይግባኝ ያሉት አቶ በቀለ ገርባን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ምንጭ ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ሀረር ካምፓስ) የጤና ተማሪዎች መንግስት ለጠየቅነው ጥያቄ ተግባራዊ መልስ ካልሰጠን አንማርም ሲሉ ገልፀዋል። መንግስት በጅግጅጋ የሚማሩ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚበትን የተሰማ ሲሆን ተማሪዎቹ እስካልመጡ ድረስ ምንም አይነት ትምህርት እንደማይማሩ አሳውቀዋል።

ዛሬ ጥዋት የግቢው ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጉ ሲሆን በትምህርት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ሊወጡ ተገደዋል።

በተጨማሪም በዋናው የሀረማያ ግቢ ለትምህርት ወደ ክፍል የገቡ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን አቋርጠው ሊወጡ ተገደዋል።

ምንጭ ፦ EK,Ab,Da

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ለጥያቄያቸው ግብረ መልስ እየሰጠ መሆኑን ገልፀው ተግባራዊ በሆነ መልኩ ተማሪዎቹ ወደ ግቢያቸው መጥተው ትምህርት እስካልጀመሩ ድረስ ትምህርት እንደማይማሩ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
በየአመቱ የወጪ መጋራት ገንዘብ (Cost) በየዩኒቨርሲቲዎቹ እንደሚዘገይ ይታወቃል። ለመሆነ በዘንድሮው አመት በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች የወጪ መጋራት ገንዘብ ዘግይቷል? እናተ የምትማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ብቻ ላኩ @tsegabwolde
👍1
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው።

አንተስ ? አንቺስ ? እናተስ ?

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አሳውቋል። ከዛሬ 3 ሳምንት በፊት ትምህርት የተጀመረ ቢሆን በተለያየ ምክንያት ሲቋረጥ ቆይቷል።

ለምሆኑ ግቢው ሲነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች በሰላም ፈቷል?

ምንጭ ፦ ሻ.

@tikvahethiopia
የትምህርት ተቋማት ወታደራዊ ማዘዣዎች ለሆኑ አይገባም።

የፌደራሉም ሆነ የክልል መንግስት የሚነሱ ጥያቄዎችን በሰከነ መንፈስ ሊያስተናግዱ እና ምላሽ ሊሰጡ ይገባል።

በሀይል እና በጉልበት ምንም ጥሩ ነገር ሊፈጠር አይችልም። ለዚህ ደግሞ ከአምናው እና ከካቻምናው ክስተት ትምህርት መውሰድ ያስፈልግ ነበር።

ሊፈቱ በሚችሉ ጉዳዮች የሰዎች ህይወት ሊጠፋ አይገባም።

ሰላም ለኢትዮጵያ !

የምትስማሙ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የትግራይ ክልል ህዝብ ግንኙነት ቢሮ የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ (OBN) "ዘረኛ" ላላቸው ዘገባዎቹ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ዛሬ ለ ድርጅቱ እና ለመንግስት ኮሚኒኬሽን በፃፈው ደብዳቤ ጠየቀ።

ምንጭ ፦ ዳንኤል ብርሀኔ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነቀምቴ ከተማ በተነሳ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የአማርኛው ክፍል አገልግሎት ትላንት ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የምግብ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀዋል።

ከተማሪዎቹ እንደተላከው መረጃ ከሆነ በሳምንት 3 ጊዜ የነበረው የሩዝ ፕሮግራም ሩዝ ገበያ ላይ የለም በማለት ዩኒቨርሲቲው አቋርጦታል። በሩዝ ቦታም ዩኒቨርሲቲው በሳምንት 5 ቀን ባዶ ዳቦ ተማሪዎችን እየመግበ ነው።

ተማሪዎችም በዚህ ጉዳይ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ምንጭ ፦ ሐብ..

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ ሆይ ሀገራችንን ጠብቅልን ! ክፉ አታሳየን፤ክፉም አታሰማን። አንድ አድርገህ አኑረን። አንተው ሿሚ አንተው ሻሪ ነህ እና የሚጠቅመንን ከላይ አድርግልን። ያላንተ ፍቃድ የሚሆን ሁሉ ጠፊ ነው።

ለኢትዮጵያ እንፀልይ ! ፈጠሪ ሁሉን ይችላል።

ሰው መከበር ያለበት መኖርም ያለበት በዘሩ እና በብሄሩ ሳይሆን በሰውነቱ ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ካሉባቸው በርካታ ችግሮች አንዱ የጊዜ አጠቃቀም እና ለተማሪዎች ተገቢውን የወጪ መጋራት ክፍያ በጊዜው አለመክፈል ነው። ዩኒቨርሲቲዎች አመቱን ሲጀምሩ ምን ያህል ወጪ እንደሚያወጡ ምን ያህል ተማሪ እንደሚያስተዳድሩ አውቀውት እና በቂ በጀት ተመድቦላቸው ነው።

በየጊዜው በየአመቱ ተማሪዎች ክፍያ ቶሎ አይፈፀምልንም እያሉ ያማርራሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ይህን ችግር መፍተት እንዴት ያቅታቸዋል ?? ተማሪዎች እና ቤተሰብስ በዚህ ጉዳይ ለምን ይሰቃያሉ ?? ለመሆኑ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የዩኒቨርሲቲ ክፍል ስራው ምንድነው ??

ይህ ሁሉ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በያዝነው አመት የወጪ መጋራት ገንዘብ (Cost) እስካሁን አልተከፈላቸውም ወይም ዘግይቶባቸዋል። በአንዳንዶቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሁለት ወር ክፍያ አልተከፈለም።

👉ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
👉አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖ.
👉ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
👉አምቦ ዩኒቨርሲቲ
👉ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ጤና ግቢ)
👉ጅማ ዩኒቨርሲቲ
👉ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
👉አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
👉ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
👉መቱ ዩኒቨርሲቲ
👉ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ
👉አክሱም ዩኒቨርሲቲ
👉ደብረተቦር ዩኒቨርሲቲ
👉ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
👉መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ
👉ዲላ ዩኒቨርሲቲ

እነዚህ እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መንግስት አቅም አለኝ ብሎ የከፈታቸው በመሆኑ ተገቢውን ስራ መስራት አለበት።

አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮችም ተማሪዎች እንደሚሉት በንቀት እና በግንዝነት የተሞሉ በመሆኑ ተማሪዎችን በክብር አያስተናግዱም ጥያቄም ሲጠየቁ አይመልሱም።

ትንሽ የሚመስሉ ቅሬታዎች ውለው ሲያድሩ ብዙ መዘዝ ይዘው መምጣታቸው አይቀርምና ዩኒቨርሲቲዎች እንችላለን ኑ ብለው ተማሪን ከተቀበሉ በአግባቡ ማስተዳደር አለባቸው።

ምንጭ ፦ በተጠቀሱት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ወድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታዮች እዚህ ቻናል ከናተ በኩል ያልመጣ ነገር በፍፁም አይፃፍም። አንዳንዶች ደግሞ የሚፃፈውን ማንበብ እና መገናዘብም መልካም ነው። የወጪ መጋራት ክፍያ "ያልተከፈላቸው ወይም የዘገየባቸው" ተከፍሎ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በወቅቱ ያልተከፈላቸውንም ያካትታል። ዘለን ሰዎችን ወይም መረጃ አድራሾቹን ለመውቀስ እና ለመሳደብ ባንሮጥ መልካም ነው።

@tikvahethiopia
መሬት ላይ የበቀለ አረም ቶሎ ሊታረም ይችላል፤አእምሮ ላይ የበቀለ አረም ግን ዘመናትን ይጨርሳል።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️

@tsegabwolde @tikvahethiopia