ዛሬ በአምቦ ከተማ ሲደረግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች ተበተነ። በከተማው መንገዶች ተዘጋግተዋል። የንግድ ተቋማትም ዝግ ናቸው።
@tikvahethiopia @tsegavlbwolde
@tikvahethiopia @tsegavlbwolde
ኬንያውያን ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እያመሩ ነው ኬንያውያን በዳግም ምርጫው ድምፃቸውን ለመስጠት ዛሬ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እያመሩ ነው፡፡
በምርጫው የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲጋ ራሳቸውን አግለዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸውም ድምፅ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ ግጭት እንዳይቀሰቀስ ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት ምርጫውን ከግጭት ለመታደግ በስፋት እንደተሰማሩ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡
በምርጫው ምክንያት የተፈጠረው ውጥረትም አሁን ድምፅ ለመስጠት እየወጣ ያለው ህዝብ ከሁለት ወር በፊት ከወጣው ህዝብ ያነሰ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ያለ ተቀናቃኝ በምርጫው የቀረቡት ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንያታ ፕሬዝዳንትነታቸውን በዚህ ምርጫም እንደሚያስጠብቁ ይጠበቃል፡፡
የኬንያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዳግም ምርጫው ተቃዋሚዎች የማይሳተፉ ከሆነ በቀጥታ ኡህሩ ኬንያታ እንዳሸነፉ እንደሚቆጠር ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
@tikvahethiopia @tsegabwolde

የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኃላፊነት የተመላበት ዘገባ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ ባለሥልጣኑ ባለፈው አንድ ዓመት ባካሄደው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በመገናኛ ብዙኃን ሕዝቡንና ሕገመ ንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ስሜታዊ ዘገባዎች መስተዋላቸውን ገልጿል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ጥዋት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ተማሪዎችን ሊያስተምር ወደ ክፍል የገባው መምህር ስዩም ተሾመ ክፍሉን ባዶ አግኝቶታል። መምህር ስዩም በፌስቡክ ገፁ እንዲህ ብሏል
"ዛሬ ጠዋት ክላስ ነበረኝ!! ተማሪ ግን የለም!! ጉድ ፈላ ዘንድሮ!"
ምንጭ ፦ ስዩም(ፎቶ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዛሬ ጠዋት ክላስ ነበረኝ!! ተማሪ ግን የለም!! ጉድ ፈላ ዘንድሮ!"
ምንጭ ፦ ስዩም(ፎቶ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አንዳንድ አዋሳኝ ቦታዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መንስኤው በአካባቢዎቹ ያልተፈቱ
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከቶች እንጂ የወሰን ጉዳይ ነው ብለው እንደማያምኑ ዛሬ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል። በተለይም በአካባቢዎቹ የጫት ንግድን
በሞኖፖል ለመያዝ ያለ ትግል እና በአከባቢው ያለው የዶላር የጥቁር ገበያ ንግድ ላይ ብሄራዊ ግብረሃይል ተቃቁሞ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ጥቅማቸው
የሚነካባቸው ጥገኞች የፈጠሩት አለመረጋጋት ውጤት ነው ብለዋል።
ምንጭ ፦ EBC

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ አቶ በረከት ስምኦን የመልቀቂያ ጥያቄ
የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን ተናግረዋል። አቶ በረከት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ መንግስት ውሳኔያቸውን እንደተቀበላቸው ነው የገለጹት። በሌላ በኩል የአቶ አባዱላ ገመዳ የመልቀቂያ ጥያቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበ በመሆኑ ውይይት እየተደረገበት ነው ብለዋል።
ምንጭ ፦ FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን ተናግረዋል። አቶ በረከት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ መንግስት ውሳኔያቸውን እንደተቀበላቸው ነው የገለጹት። በሌላ በኩል የአቶ አባዱላ ገመዳ የመልቀቂያ ጥያቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበ በመሆኑ ውይይት እየተደረገበት ነው ብለዋል።
ምንጭ ፦ FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በኦሮሚያ ክልል በአምቦ ከተማ ከባድ ተሽከርካሪዎች «ሕገ ወጥ ስኳር» ጭነዋል፣ «ስኳሩን ጭነዉ ጉዦ የጀመሩበትና አምቦ ከተማ የደረሱበት ቀንም እጅግ ሰፊ ልዩነት አለዉ» በማለት በትላንትናዉ እለት ራሳቸውን «ቄሮዎች» ብለው በሚጠሩ ወጣቶች ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ከማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ለመረዳት ተችሏል። ከዛም ወጣቶቹ አምቦን ጨምሮ በ12 ኪሎሜትር ላይ የምትገኘዉን የጉደር ከተማ መንገዶችን መዝጋታቸዉን፣ ዛሬ ጥዋት ወደ አምቦ ያቀናዉ የአጋዚ ኃይል ተኩስ እንደከፈተ ብሎም ሰዎች እንደተጎዱ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጠቅሰዋል። የክልሉ የኮሙኒኬሼን ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጥዋት ሰዎች እንደቆሰሉና ሕይወት እንዳለፈም በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ አስፍረዋል።
ምንጭ ፦ ዶቸ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ ዶቸ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ውጥረት ነግሷል። ከተማው ጭር ብሏል። ሰዎች ቆስለዋል፤ተገለዋል።
ዛሬ ጥዋት ወደ አምቦ ያቀኑ የጸጥታ ኃይሎች ተቃውሞ በሚያሰሙ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ታውቋል። የአምቦ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ተኩሱን የከፈተው የአጋዚ ኃይል ሲሆን 10 ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል። በተኩሱ 20 ሰዎች መቁሰላቸውንም ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጠዋት በፌስቡክ ገፃቸዉ በአምቦ ሰዎች መሞታቸውን እና የቆሰሉም እንዳሉ አረጋግጠዋል።

ዛሬ እየተካሄደ ባለው የኬንያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ግጭት ተፈጠረ። በተለያዩ ከተሞች ውጥረቱ አይሏል። በኪሱሙ አንድ የ19 አመት ልጅ ከታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ቢቢሲ ዘግቧል። ኪሲሙ በርካታ የመንግስት የተቃዋሚዎች የሚገኙበት ከተማ ነው።
ምንጭ ፦ አፍሪካ 24,ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ አፍሪካ 24,ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኬንያ ኪሱሙ አንድ የ19 አመት ልጅ ከታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ቢቢሲ ዘግቧል። ኪሲሙ በርካታ የመንግስት የተቃዋሚዎች የሚገኙበት ከተማ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
በአምቦ ከተማ ህይወታቸውን ባጡት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን። ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ ናት ለስንት ነገር የሚጠበቁ ጀግና የሀገር ልጆች በአጭሩ እየተቀጩ ነው።
ለሁሉም ፈጣሪ መልስ አለው። ተግተን እንፀልይ ! ፈጣሪ ሁሉን ይችላል።
⚫️⚫️ነብስ ይማርልን⚫️⚫️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሁሉም ፈጣሪ መልስ አለው። ተግተን እንፀልይ ! ፈጣሪ ሁሉን ይችላል።
⚫️⚫️ነብስ ይማርልን⚫️⚫️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በአምቦ ከተማ በተከሰተው ሰፊ ብጥብጥ ቢያንስ የአስር ሰው ህይወት አልፏል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከርሮ የነበረው ውጥረት ዛሬ የፀጥታ ሀይሎች ወደ ከተማው ሲገቡ ተባብሶ የሰው ህይወት እንዳለፈ እና ብዙ ሰውም እንደቆሰለ ለማወቅ ተችሏል። የአሜሪካን ኤምባሲ ማምሻውን በሰው መሞት ማዘኑን ገልፆ ግጭትን በሰላም መፍታት ያስፈልጋል ብሏል።
@tikvahethiopia @tsegabwolde
@tikvahethiopia @tsegabwolde
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
በሀገሪቱ አብዛኛው ክፍል የኔትዎርክ መቆራረጥ አለ። በዚህም በርካታ ሰዎች ምሬታቸው እየገለፁ ነው። ከዕለት ወደ ዕለት ኢትዮ ቴሌኮም አሰራሩን ያሻሽላል ያስተካክላል ቢባልም ጭራሽ እየባሰበት መጥቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም👎
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም👎
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋሽንግተን ፖስት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ሮበርት ሙጋቤን ለምን የክብር አምባሳደር አድርገው እንደሾሙ እንዲጣራ እና ሙስና ካለበት ከሀላፊነታቸው ይነሱ
የሚል አስተያየት ዛሬ ይዞ ወጥቷል።
https://www.washingtonpost.com/news/democracy-post/wp/2017/10/25/another-week-another-scandal-at-the-united-nations/?sw_bypass=true&utm_term=.704248aa6512
@tikvahethiopia @tsegabwolde
የሚል አስተያየት ዛሬ ይዞ ወጥቷል።
https://www.washingtonpost.com/news/democracy-post/wp/2017/10/25/another-week-another-scandal-at-the-united-nations/?sw_bypass=true&utm_term=.704248aa6512
@tikvahethiopia @tsegabwolde
Washington Post
Opinion | Another week, another scandal at the United Nations
The continuing fallout from a scandalous appointment at the World Health Organization.
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢው ውስጥ በቂ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች ባለመኖራቸው እንደተቸገሩ ገለፁ።
ተማሪዎቹ በአቅራቢያቸው ሱቅ ባለመኖሩ የሞባይል ካርድ እንኳን ለመግዛት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
የግቢው ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው ቅሬታቸውን ደጋግመው ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ እንዳላገኙ በላኩልኝ መረጃ ጠቁመዋል።
ሌላው ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግ የትምህርት ክፍል በደረሰኝ መረጃ ትምህርት ይጀመራል ከተባለበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ የተማሩት 1 ኮርስ ብቻ ነው። ተማሪዎች ጥዋትም ከሰዓትም ወደ መማሪያ ክፍላቸው ረጅም ደቂቃዎችን እየተጓዙ ቢመላለሱም መምህራንን ማግኘት አልቻሉም። በዚህም ዩኒቨርስቲው ያወጣውን መርሀ ግብር ማስፈፀም አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች(ስም መጥቀስ አስፈላጊ አይደለም)
እናተስ በያላችሁበት ምን ታዘባችሁ ? @tsegabwolde

የሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በመንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እና በትላንትናው ዕለት በአምቦ ከተማ በጠፋው የሰው ህይወት ሀዘናቸውን ገለፁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ከሶስት ካምፓሶች የተውጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እና ሀዘናቸውን ገለፁ።
የግቢው ተማሪዎች የትላንቱን የአምቦ ከተማ ህይወት መጥፋት ምክንያት አድርገው የተሰማቸውን ሀዘን ለመግለፅ ቁርስ ያለመብላት አድማ መተው ነበር።
በተጨማሪም ከእንጂነሪንግ ግቢ የተነሳ እና በዋናው ካምፓስ ያለፈ ሰልፍ በማድረግ ስታዲየም ውስጥ ተገኝተው የሻማ ማብራት ስነስርአት በማድረግ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ ከጅግጅጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች መፍትሄ እንዲሰጥ እና ከዚህ ቀደም ለጠየቁት ጥያቄ መንግስት መልስ እንዲሰጥ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። መላሽ እስከሚያገኙም ትምህርት እንደማይማሩ ወደ ክፍልም እንደማይገቡ ገልፀዋል።
የተማሪዎቹ የሻማ ማብራት ስነስርአት እና ተቃውሞ ከቀኑ 6 ሰዓት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል።
ምንጭ ፦ MR( ሀለማያ ዩኒቨርሲቲ)

❤1👍1
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ስለ ትላንቱ እና ከትላንት ወዲያው የአምቦ ግጭት ይህን ብለዋል ..
ግጭቱ "ከፊንጫ ወደ አዲስ አበባ ህገ ወጥ ስኳር እየተጓጓዘ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል።"
ምንጭ ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግጭቱ "ከፊንጫ ወደ አዲስ አበባ ህገ ወጥ ስኳር እየተጓጓዘ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል።"
ምንጭ ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⚪️🔘ሰበር ዜና🔘⚪️
ካታሎንያ ከስፔን መገንጠሏን አወጀች። የካታሎንያ ግዛት ፓርላማ ዛሬ ከስፔን የመገንጠል ውሳኔን አሳልፏል።
ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ባገለሉበት ሁኔታ ውሳኔው በ70 ድጋፍና በ10 ተቃውም ጸድቋል።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ካታሎንያ ከስፔን መገንጠሏን አወጀች። የካታሎንያ ግዛት ፓርላማ ዛሬ ከስፔን የመገንጠል ውሳኔን አሳልፏል።
ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ባገለሉበት ሁኔታ ውሳኔው በ70 ድጋፍና በ10 ተቃውም ጸድቋል።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia