TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚኒ እስታዲየም የነበረው የተማሪዎች ስብሰባ ይህ ይመስላል።

ፎቶ ፦ ረ.ዲ.

@tikavhethiopia @tsegabwolde
👍1
የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ በምርቶች ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሁለት ቀናት የንግድ እንቅሰቃሴ ላይ ባደረገው የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በጤፍ፣ ስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የብረት ምርት ውጤቶች ላይ ፍትህዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ገልጿል።

ጥናቱ በተለይም በመርካቶ አካባቢ የተደረገ ሲሆን፥ በዚህም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ላይ ጭምር የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ነው የተባለው።

በጥናቱ መሰረት የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ ተመልከቱ ..

በኩንታል ከ2 ሺህ 400 ብር ይሸጥ የነበረው ነጭ ጤፍ አሁን በ2 ሺህ 500 ብር፤ ሽንኩርት በኪሎ ከ19 ወደ 20 ብር፤ ቲማቲም በኪሎ ከ20 ብር ወደ 24 ብር ጭማሪ ተደርጎባቸው እየተሸጡ መሆናቸውን ጥናቱ ያሳያል።

የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመለከተም በፊት በኪሎ 14 ብር ይሸጥ የነበረው የስንዴ ዱቄት አሁን በ16 ብር እየተሸጠ ሲሆን፥ በፊት 22 ብር የነበረው ፓስታ አሁን ላይ 26 ብር እንዲሁም በሊትር 62 ብር ይሸጥ ነበረው የኑግ ዘይት አሁን 72 ብር
መግባቱም በጥናቱ ተገልጿል።

በሁለት ቀኑ ጥናት ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ አራት ሱቆች እና ከመጠን በላይ ምርት ተሸሽጎበት የተገኘ አንድ መጋዘን መታሸጉም ተነግሯል።

መንግስ የአልአግባብ ዋጋ በሚጨምሩ እና በአቋራጭ ለመበልፀግ በሚፈልጉ ነጋዴዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የኦሮሚያ ክልል የኮሚዩኔኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኢኤንኤን(ENN) እና ዛሚን(ZAMI 90.7) ግጭትን የሚያባብሱ ዘገባዎችን እያቀረቡ ነው ሲሉ ወቀሱ።

በትላንትናው ዕለት እኔም ENN የሰራው ሰበር ዜና ከፍተኛ ችግር ሊያስከትል የሚችል እንዲሁም ግጭትን የሚያባብስ መሆኑን ተናግሬ ነበር።

እናተስ?
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው ሁሉ ‼️

ያለፈውን በማየት ስለወደፊቱ እንማር !

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tikvahethiopia
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ረፋድ የነበረው የተማሪዎች ስብሰባ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ረፋድ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመሰባሰብ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ እና አዲስ የተመደቡ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ጠይቀዋል። የጠየቁት ጥያቄም መልስ እስከሚያገኝም ትምህርት እንደማይጀምሩ ገልፀዋል።

ባለፈው ሳምንት ሰኞ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የነባር ተማሪዎች የትምህርት መርሀ ግብር እስከ ዛሬ አልተጀመረም። በተጨማሪም ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የተጠበቀው የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባም እስካሁን አልተጀመረም።

ዩኒቨርሲቲው በዚህ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ የለም።

ምንጭ ፦ ሙኒየ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚንስቴር ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት አስቸኳይ ደብዳቤ ፃፈ። በፃፈው ደብዳቤ መሰረት ያላግባብ ከኢን. ውጭ የተመደቡ ተማሪዎች ወደተመደቡበት የትምህርት መስክ እንዲመለሱ እና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያሳስብ ነው።

ምንጭ ፦ Golden 1

@tsegabwolde
ወደ ደሴ መስመር የሚወስደው ዋና የጋሸና መግቢያ ላይ አንድ ተሳቢ ቦቲ መኪና መሀል መንገድ ላይ በመውደቁ በሁለቱም አቅጣጫዎች የሚመጡት መኪናዎች ማለፍ አልቻሉም።

ምንጭ ፦ @Anumuhammediy

የሚመለከተው አካል አፍጣኝ መፍትሄ በሰጥ መልዕክታቻ ነው።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ዛሬ ወደ ደሴ መስመር በሚወስደው ዋና የጋሸና መግቢያ ላይ የወደቀው ተሳቢ ቦቲ መኪና ከቀኑ 11:05 ላይ ሊነሳ መቻሉን ከስፍራው ማረጋገጥ ተችሏል። መሀል መንገድ ላይ በመውደቁ ከሁለቱም አቅጣጫዎች የሚመጡት በርካታ መኪናዎች ማለፍ ባለመቻላቸው በርካታ ተጓዦች ተስተጓጉለው ነበር።

@Anumuhammediy
#BreakingNews »» Loading
⚪️⚫️ሰበር ዜና⚪️⚫️

ENF የተባለው የዜና አውታር ከምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ በትላንትናው እለት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እስከ ለሊት ድረስ ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበረ ገልጿል። እንደ ዜና አውታሩ ምንጮቻች ጥቆማ ምናልባትም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ለመመለስ እየታሰበ እንደሆነ ነው የሚገልፀው። በዛሬ ዕለት ደግሞ ፌስቡክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተቆራረጠ እንደሆነ ለዜና አውታሩ የተላኩት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiop
በየሁለት ሳምንቱ ሰኞ ስለ ቻናሉ የእናተ አስተያየቶች እንደሚስተናገዱ ይታወቃል። ዛሬ ግን ለየት ባለ መልኩ ድምፅ ትሰጣላችሁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወቅቱን የጠበቀ በቂ መረጃ እየሰጣችሁ ነው ?? እናተ እንዴት ትመዝኑታላችሁ ?

እጅግ በጣም ጥሩ
ጥሩ✳️
መካከለኛⓂ️
ዝቅተኛ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት ምሽት 5:40 አካባቢ (ወሎ)መርሳ ከተማ ልዩ ቦታው አዲሱ ገበያ በተነሳ የእሳት አደጋ ከ20 በላይ የሚሆኑ ኮንቴነሮች ተቃጠሉ። እስካሁን ድረስ የእሳቱ መነሻ በውል አልታወቀም።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ሰለሞን( @sonofgold )

@tikvahethiopia @tsegabwolde
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ዮሀን ቦርግስታም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተነሱትን ግጭቶች በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆኑ ገልፀው የሰው ህይወት በማለፉ እንዳዘኑ ገልፀዋል። አምባሳደሩ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግልፅ ንግግር እንዲያደርግም ዛሬ ጠይቀዋል።

ምንጭ ፦ ENF

#ቲክቫህ
ጥቆማ፣ትዝብት እንዲሁም መረጃ ማድረስ ይቻላል። በተለይ በየዩኒቨርሲቲው የምትገኙ ተከታዮቻችን ማንኛውም አይነት ቅሬታ እና የደረሰባችሁ በደል ካል ወይም የምትመለከቱት የአስተዳደር ችግር ካለ አሳውቁን። በተጨማሪም በየምትኖሩበት አካባቢ የምታስተውሉ ችግር ካለ እና ከሰሞኑን የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግድ ተቋማት ስማቸውን በፎቶ አስደግፋችሁ ላኩልን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢቢሲ(EBC) በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ሶስት ግዜ የተሳሳተ የወሰን ካርታ አስተላልፎ ሁለት ግዜ ይቅርታ ጠይቋል።

ለመሆኑ EBC አስተዳዳሪ፣ ተቆጣጣሪ፣ መሪ ፣መካሪ፣ባለሞያ አለው ??ኧረ ለመሆኑ EBC ባለቤትስ አለው ??

ይህ የእናተም ጥያቄ ከሆነ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ IoT (ቴክኖ) ካምፓስ ተማሪዎች በያዝነው ሳምንት ዝርፊያ ተፈፅሞብናል አሉ።

የዩኒቨርሲቲውን የጥበቃ እና ደህንነት ክፍልንም ክፉኛ ወቅሰዋል።

ከትላንት በስቲያ ለሊት ስለት የያዙና ጭምብል የለበሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የወንዶች ዶርም ድረስ ገብተው ዝርፊያ መፈፀማቸውን ተማሪዎች ይናገራሉ። ለሊት 8:00 ሰዓት ለሽንት የወጣውን ተማሪ በማገት እና በማስፈራራት ቁልፍ በመቀበል ሌሎቹ ዘራፊዎች ደግሞ ዶርም ድረስ በመግባት ዝርፊያ ፈፅመዋል። በዝርፊያውም የተማሪዎች መገልገያ የሆኑ ላፕቶፕ፣የሞባይል ስልክ፣ጫማ፣ልብስ መሰረቁን ገልፀዋል። በሌላ ጊዜ በሱሰኞች የተማሪዎች ላፕቶፕ ስርቆት የተለመደ ቢሆንም የዚህን ሳምንት ዝርፊያ አስፈሪ ያደረገው በስለት በተደገፈ እንዲሁም በተደራጁ ሰዎች መሆኑ ነው።

ትላንት ለሊት ደግሞ 2 የአዲስ ተማሪዎች ዶርም ተዘርፏል።

ተማሪዎቹ ከዚህ የሚያክል ትልቅ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ የጥበቃ እና የደህንነት ማስጠበቅ አሰራር ብለውታል። የጥበቃ ሰራተኞቹ ስራቸው ምን እንደሆነ ሊገባንም አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።

ከዝርፊያው በኃላ የግቢው ፖሊሶች የወንዶችን ዶርም አንድ በአንድ ሲበረብሩ ውለዋል።

ምንጭ ፦ የግቢው ተማሪዎች ( የግል ስም መጥቀስ አስፈላጊ አይደለም።)

በእኔ በኩል ይህን ለማለት እፈልጋለው። ይህን መሰሉ የዝርፊያ ተግባር አንደኛ የከተማውን ስም የሚያጎድፍ ሲሆን ሁለተኛ በትምህርት ሚንስቴር ስር የሚተዳደረውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያስወቅሰዋል። ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ይህን መጥፎ ተግባር በማጣራት ዘራፊዎቹን ለህግ በማቅረብ ተበዳዮችንም መካስ ያለበት ይመስለኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 29 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ የፕሬዝዳንቱን ንግግር አስመልክቶ በቀረበው የድጋፍ ሞሽንና ከአባላቱ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ነገ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት የመንግሥትን አቋም ይገልፃሉ፡፡

ጉባኤው እንደተጠናቀቀ የሚነሱትን ጉዳዮች ተከታትዬ ነገራችኃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከጠራ በኃላ ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያከናውኑ ቢያደርግም እስካሁን ድረስ ትምህርት እንዳልተጀመረ ከተማሪዎቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተቋሙ ዝግጅት ሳይጨርስ ተማሪዎችን መጥራቱ አስወቅሶታል። የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተ መፅሀፍ እንዲሁም የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ በእድሳት ላይ ናቸው።

ትምህርት ባለመጀመሩ ምክንያት ተማሪዎቹ ጊዜያቸው እየባከነ መሆኑን ይገልፃሉ። ከቅርብ ከተማ የመጡ ተማሪዎችም ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው።

ምንጭ ፦ H1(ዲላ)

እንደ አንድ ዜጋ በጉዳዩ ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት በስልክ አለመስራት ምክንያት አልተሳካም።

ለመሆኑ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር ይህን ጉድ ያውቀዋል ? ዩኒቨርሲቲዎች በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ እንዴት ተማሪዎችን ይጠራሉ ??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎጃም ያረሰውን፣ለጎንደር ካልሸጠ
ጎንደር ያረሰውን፣ለጎጃም ካልሸጠ
የሀረር ነጋዴ ፣ ሸዋላይ ከልሸጠ
የትግሬ አባት ልጅን ፣ለወለጋ ካልሰጠ
ፈቅር ወዴት ወዴት፣ ወዴት ዘመም ዘመም
ሀገርስ አለቺኝ፣ሀገር የኔ ህመም
ስሩ እዳይበጠስ ፣ መቋጠሪያ ደሙ
አረጓዴ ቢጫ ቀይነው ቀለሙ

@tikavhethiopia