TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ40,000,000 ብር ድጋፍ ያደረጉት ሼክ ሁሴን መሐመድ አሊ አላሙዲ "የጣናን ጉዳይ ለእኔ ተዉት ሁሉንም ማሽኖች ከዉጭ አስመጥቼ ችግሩን አስወግደዋለን"ብለዋል።
ሰናይ ተግባር !
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሰናይ ተግባር !
@tikvahethiopia @tsegabwolde
🙏3
በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደ አነሳሱ ሰላማዊ ሳይሆን በመሃል በአንዳንድ ከተሞች ወደ ንብረት ማውደም እና ሰዎች ላይ ጉዳት ወደ ማድረስ አምርቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክልሉ ባለስልጣን (የኦሮሚያ መንግስት ኮሚኒኬሽ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ) ለVOA 24 በሰጡት ቃል ከ100 በላይ ከሌላ አካባቢ የመጡ ሰዎች መታሰራቸውን ገልፀዋል።
በአንዳንዶች ዘንድ እኚህ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች በንብረት ማውደም እና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን የመበጥበጥ ተልዕኮ የማስፈፀም ስራ ነበራቸው የሚል ጥርጣሬን አሳድሯል።
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በአንዳንዶች ዘንድ እኚህ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች በንብረት ማውደም እና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን የመበጥበጥ ተልዕኮ የማስፈፀም ስራ ነበራቸው የሚል ጥርጣሬን አሳድሯል።
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በአባይ ጉዳይ አንደራደርም !
በአባይ ግድብ ጉዳይ የሚመጣብን ጠላታችን ነው። ከ2 ሳምንት በፊት ሀገር ውስጥ እና ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ነን ባይ ግለሰቦች እና ሚዲያዎች የግድቡ ስራ ተቋርጧል ሰራተኞችም እየተባረሩ ነው በማለት ህዝብን ሲያሳስቱ ነበር።
ይሄን ሁለት ቀን ደግሞ የግድቡ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ስራቸውን ጥለው ሀገር ጥለው ጠፍተዋል ሀገር ጥለው ኮብልለዋል እያሉ ህዝብ በሀሰት መረጃ እያስታጠቁ ናቸው።
እኔ እንደሰማሁት እና እንደማውቀ 100000% እንግጠኛ ሆኜ መናገር ምችለው የግድቡ ስራ እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። የግ ድቡ ስራ አስኪያጅ ኢኒጂነር ስመኘው በቀለም የኢትዮጵያ ህዝብ የጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት እየተወጡ ይገኛሉ።
በአባይ ጉዳይ አንደራደርም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

❤1
ውዝግቡ ..ፎቶው የት ነው ?
"ትላንት በጎንደር የፋሲል ከነማ የሙዚቃ ድግስ ይደረጋል ተብሎ ነበር ሁሉም ዝግጅት ካለቀ በኃላ ግን ታዳሚው ቀርቷል።" ይህ ትላንት ምሽቱን ሲሰራጩ ከነበሩት ሰበር ዜናዎች አንዱ ነው።
ጎንደር የነበራችሁ ምስክርነት ስጡ ኮንሰርቱ ነበር ?ፎቶ ካላችሁም ላኩልኝ።
@tsegabwolde
"ትላንት በጎንደር የፋሲል ከነማ የሙዚቃ ድግስ ይደረጋል ተብሎ ነበር ሁሉም ዝግጅት ካለቀ በኃላ ግን ታዳሚው ቀርቷል።" ይህ ትላንት ምሽቱን ሲሰራጩ ከነበሩት ሰበር ዜናዎች አንዱ ነው።
ጎንደር የነበራችሁ ምስክርነት ስጡ ኮንሰርቱ ነበር ?ፎቶ ካላችሁም ላኩልኝ።
@tsegabwolde
ጎንደር ፦ ያሬድ ነጉ፣ሳሚ ዳን፣ብስራት ሱራፌል ይገኙበታል በተባለው የፋሲል ከነማ ኮንሰርት ህዝቡ ቀርቷል።
ማረጋገጥ ስለምፈልግ ነው ትላንት በጎንደር አብዮት አደባባይ ኮንሰርት ነበር ?? ከነበረስ ታዳሚ ነበር ??
የጎንደር ልጆች ብቻ መልዕክታቹን ላኩልኝ @tsegabwolde
ማረጋገጥ ስለምፈልግ ነው ትላንት በጎንደር አብዮት አደባባይ ኮንሰርት ነበር ?? ከነበረስ ታዳሚ ነበር ??
የጎንደር ልጆች ብቻ መልዕክታቹን ላኩልኝ @tsegabwolde
በቅድሚያ ይህ ማታ የጎንደር ኮንሰርት ተብሎ በፌስቡክ የተሰራጨው ፎቶ ውሸት ስለመሆኑ ማረጋገጥ ችያለሁ። ፎቶ የተወሰደው አዲስ አበባ ከተማ ከነበረ ሌላ ኮንሰርት ላይ ነው።
ስለ ጎንደሩ ኮንሰርት ....
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ጎንደሩ ኮንሰርት ....
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር 🎤 የፋሲል ከነማ ኮንሰርት
ትላንት በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ነበር። በትላንትናው ኮንሰርት የጎንደር ተወላጆችም ሆነ የአካባቢው ሰው አልተገኘም። ኮንሰርቱ ላይ የነበሩት ታዳጊዎች እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።
የጎንደር ህዝብ ምንም የፋሲል ከነማን የስፓርት ክለብ ቢወደውም በትላንትናው ኮንሰርት አልተገኘም።
በኮንሰርቱ የከተማው ነዋሪ እና አዋቂ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም ሲጠብቋቸው የነበሩ ሰዎች ባለመገኘታቸው አዘጋጆቹ በጣም ተናደዋል። ኘሮግራሙ ጀምሮ እንኳን አዘጋጆቹ ትኬት ይዘው ሲዞሩ በአይኑ የተመለከተ የቻናላችን ተከታይ ነግሮኛል።
ሌላው ...በኮንሰርቱ ምንም አይነት የአልኮል መጠጥ ሽያጭ አልነበረም።
ምንጭ ፦ ዮሲ፣ማሂ (ጎንደር)

በዋሊያ ቢራ ስፖንሰርነት ከጣና እንቦጭን ለማስወገድ ከወልዲያ ከተማ የተነሱት ወጣቶች ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ተወጥተው ዛሬ ወደ ወልዲያ እየተመለሱ ይገኛሉ። ሰላም ግቡ መልካም መንግድ !
ጣና የሁላችንም ነው !
ምንጭ ፦ @O1emoretime
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ጣና የሁላችንም ነው !
ምንጭ ፦ @O1emoretime
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ቅሬታ ፦ የዲላ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገና በግንባታ ላይ ባለ ካፌ ውስጥ ምግብ እንድንመገብ እየተደረግን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ዩኒቨርሲቲው የግንባታ አልያም የእድሳት ስራዎችን ሳይጨርስ ተማሪዎችን ማስተናገድ አልነበረበትም ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው ላይብረሪም እድሳት ላይ ነው።
ምንጭ፦ M
@tsegabwolde
ምንጭ፦ M
@tsegabwolde
⚪️🔘ሰበር ዜና🔘⚪️
ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሮበርት ሙጋቤን የአለም የጤና ድርጅት (WHO) የበጎ አድርጎት አምባሳደርነት ሰረዙ።
ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሮበርት ሙጋቤን የአለም የጤና ድርጅት (WHO) የበጎ አድርጎት አምባሳደርነት ሰረዙ።
ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ENN ምን እያደረገ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም። ኢትዮጵያችን ወዴት እያመራች ነው??? የሚወጡትን ሰበር ዜናዎች እንዲሁም ዴጋ እና ጮራ ምን እንዳለ ህዝቡ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እናጣራለን።
ህዝብን በትክክል መረጃ በሚሰጥ እና ግጭትን በማያባብስ ሁኔታ መረጃዎችን ወደ እናተ እናደርሳለን። የተገኘውን ሁሉ ሰበር ዜና ብሎ ማቅረብ ብዙ ጣጣ ይዞ ይመጣል።
እዛው የምትገኙ ደግሞ መልዕክታችሁን በ @tsegabwolde አድርሱ።
ህዝብን በትክክል መረጃ በሚሰጥ እና ግጭትን በማያባብስ ሁኔታ መረጃዎችን ወደ እናተ እናደርሳለን። የተገኘውን ሁሉ ሰበር ዜና ብሎ ማቅረብ ብዙ ጣጣ ይዞ ይመጣል።
እዛው የምትገኙ ደግሞ መልዕክታችሁን በ @tsegabwolde አድርሱ።
ያለሁበት ቦታ ኔትዎርክ አለመኖር እጅግ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን እንዳላደርሳችሁ አድርጎኛል። በቴሌ ስም ይቅርታ!
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
የምንሰማው ነገር ሁሉ እጅግ በጣም ያሳዝናል። ከብሄር፣ከዘር፣ከጎሳ ከምንም በላይ እኮ ሰው መሆን ይበልጣል።
እዚህች የተቀደሰች ሀገር በአንድ ሆነን እንድንኖር ደግሞ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት ነው።
ሁሉም የራሱን ጥቅም ፈላጊ ነው አሜሪካ እና አውሮፓ ቁጭ ብለው ለሀገር ለወገን የሚቆረቆሩ የሚመስሉ ቀንደኛ የኢትየጵያ ጠላቶች በገሀድ እየታወቁ ነው።
እነሱ ተመቻችቶላቸው እየኖሩ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ስንቶች ሀገር ውስጥ ህይወታቸው ሲያልፍ በፌስቡክ ፖስት ከማድረግ የዘለለ ስራ አይሰሩም። ሰው ከወደቀ በኃላ ከንፈር መምጠጥ ምንም አይፈይድም። እውነቱ ግን ይሄ ነው የኢትዮጵያ ጠላቶች አንድ በአንድ ይወድማሉ!
እኛ ግን መቼም የማንነጣጠል ኢትዮጵያዊነት ምንም ማለት እንደሆነ ኢትየጵያ ምን ያህል የተቀደሰች ሀገር እንደሆነች የምናውቅ ልጆቿ ነን።
✍✍ @tsegabwolde ✍✍
እኛ አንድ ነን የምትሉ ✅
@tikvahethiopia

👍1
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፨ ዛሬ ጥዋት ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ ክፍል የገቡ ተማሪዎች በተማሪዎች ሀይል ከክፍል እንዲወጡ እና ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ተደርጓል። ይህ ሁኔታ እየተደጋገመ መምጣቱ እጅግ በጣም እንዳሳሰባቸው መረጃውን ያደረሱኝ ተማሪዎች ነግረውኛል። ከ1ኛ እስከ 5ኛ አመት ድረስ ያሉ ተማሪዎች ናቸው ከክፍል ለቀው እንዲወጡ የተደረገው። እስካሁን ድረስ በስነስርዓት መማር እንዳልቻሉ እና አንዳንዶችም በመሀል እንደሚመቱ ገልፀውልኛል። ዩኒቨርስቲው እና መንግስት ይህን ሁኔታ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ጋር በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዳለበት ይታመናል።
ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። ከፎቶ ማስረጃ ጋር ይዤ እመለሳለሁ።
@tikvahethiopia
ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። ከፎቶ ማስረጃ ጋር ይዤ እመለሳለሁ።
@tikvahethiopia
👍2
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እና ቅሬታ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን መግለጫ አንቀበልም፤ሶማሌ ክልል ያሉት ወገኖች እዛ እንዲቀጥሉ አንፈልግም፤ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡትም ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ይመደቡ የሚል ነው።
#ቲክቫህ
#ቲክቫህ
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በህዝብ ያለውን አመኔታና ቅቡልነት ህዝበ ውሳኔ በማካሄድ እንዲያረጋግጥ ጠየቀ፡፡
የሀገሪቱ የፖለቲካ ችግር ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱንና ለሀገሪቱ ቀጣይ ህልውናም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ፓርቲው ጠቁሟል።
ምንጭ ፦ ኢራፓ
እናተ ምን ትላላችሁ የፓርቲው ጥያቄ ትክክል ነው ስህተት??
ትክክል✅
ስህተት❌
@tikvahethiopia @tsegabwolde
የሀገሪቱ የፖለቲካ ችግር ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱንና ለሀገሪቱ ቀጣይ ህልውናም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ፓርቲው ጠቁሟል።
ምንጭ ፦ ኢራፓ
እናተ ምን ትላላችሁ የፓርቲው ጥያቄ ትክክል ነው ስህተት??
ትክክል✅
ስህተት❌
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሰላማዊ ሰልፉ ቀጥሏል ፨ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ቀጥሏል። በርካታ ተማሪዎችም ሰልፉን ተቀላቅለዋል። በግቢው ውስጥ የሚገኙ አብዛኛው ተማሪዎች ሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። የጠየቅነው ጥያቄ መልስ ካላገኘ ክፍል በሚገቡ ተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው ነገር ተጠያቂ አይደለንም እያሉ ይገኛሉ። እኛ ከሰላማዊ ሰልፍ ውጪ ምንም አላማ የለንም ጥያቄያችን መልስ ያግኘ ነው የሚሉት።
ሌላው ...
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት ተማሪዎች እኛ የብሄር ልዩነት የለንም አንድ ነን ኢትዮጵያዊያን ነን በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላው ...
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት ተማሪዎች እኛ የብሄር ልዩነት የለንም አንድ ነን ኢትዮጵያዊያን ነን በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢሊባቡር ግጭት የተከሰተ መሆኑን ያመነው መንግስት በግጭቱ ሞቱ ብሎ የገለፀው ቁጥር አወዛጋቢ ሆኗል።
በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ እና የመንግስት መግለጫ የተካተተበትን ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ መረጃ ወደ በኃላ አደርሳችኃለሁ።
@tikvahethiopia
በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ እና የመንግስት መግለጫ የተካተተበትን ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ መረጃ ወደ በኃላ አደርሳችኃለሁ።
@tikvahethiopia
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ስብሰባ ባለመግባባት ተጠናቋል። በስበሰባው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፍቅሬ ለሜሳ እና ሌላኛው የክልሉ ባለስልጣን ሞቱማ ሚልኬሳ ተገኝተው ነበር።
ስብሰባው ባለመግባባቶች የተሞላ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ተማሪዎች ነግረውኛል።
በስበሰባው ከመድረክ የፌዴራሊዝም ጉዳይ በመነሳቱ ተማሪዎች በዚህ ጉዳይ መነጋገር እንደማይፈልጉ እና ላነሷቸው ጥያቄዎች መልስ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። እንደተማሪዎቹ ገለፃ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ባለመገኘቱ እና የስብሰባው አጀንዳ መስመር በመልቀቁ ስብሰባውን ረግጠው ለመውጣት መገደዳቸውን ገልፀዋል።
ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ተማሪዎች እዛው ግቢ በሚገኘው ሚኒ ስታዲየም ባደረጉት ስብሰባ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተው ተነጋግረዋል። ተማሪዎቹ ጥያቄያችን ካልተመለሰ ትምህርት አንማርም ብለዋል። ሁሉም ተማሪም ጥያቄዎቻቸው እስኪመለሱ ትምህርት እንዳይማሩ ላይብረሪ እዳይጠቀሙ አስጠንቅቀዋል።
የዩኒቨርሲቲውን ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም።
ምንጭ ፦ ኦሊ