TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ወረርሽኝ ሊባል በሚችል ደረጃ
እየተስፋፋ መምጣቱ ተገለፀ።

በዓመት ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ይይዛሉ የተባለ ሲሆን፥ ከ19 ሺህ በላይ የሰዎች ደግሞ በቫይረሱ አማካኝነት ይሞታሉ ነው የተባለው።

በዚህ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና በፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ እንደተገለፀው ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የስርጭት ምጣኔው ከ2 ነጥብ 5 እስከ 25 በመቶ ደርሷል።

በትልልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የአበባ ልማትና መሰል ሰፋፊ የልማት አካባቢዎች የኤች አይ ቪ አጋላጭ ባህሪያት መስፋት ለቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ሆኗል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ከበደ ወርቁ፥የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት የተመዘገበው ለውጥ መዘናጋት መፍጠሩን አንስተዋል።

ከአምስት እና ስድስት ዓመት በፊት የነበረውን ኤች አይ ቪን የመግታት ስራ ለመድገም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ምንጭ ፦ ለፋና ብሮድካስቲንግ (ትዕግስት አብርሀም)

እባካችሁ ራሳችሁን ጠብቁ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች እና በትልልቅ ፕሮጀክቶች አካባቢ የምትሰሩም የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በኦሮሚያ በኩል ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ቁጥሩም በማሻቀብ ላይ ነው። በአሁን ሰዓት የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 600 ሺ እተጠጋ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነና አንዳንዶችም ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ ተናግረዋል።

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ብቻ ወደ 72ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።

እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ላይ በትምህርት ቤቶች እና ጊዜያዊ የመጠለያ ሥፍራዎች ነበር የሚገኙት። አሁን ግን ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ክፍት በመሆናቸው ቅርብ ዘመድ ያላቸው ተፈናቃዮች ወደዚያ ሲያመሩ፤የተቀሩት ደግሞ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።

ሌላው እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ብቻ ለተፈናቃዮች የተሳበሰበው ገንዘብ መጠን 166 ሚሊዮን ብር ደርሷል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

እኔ አሳጥሬ ነው ያቀረብኩላችሁ ሙሉውን ማንበብ ከፈለጋችሁ ወደ ቢቢሲ የአማርኛ ድህረገፅ በማምራት ማንበብ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ወጣ።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ደረጃውን አስጠብቋል የትምህርት ሚኒስቴር 35ኛውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ በአሶሳ አካሂዷል፡፡

በየዓመቱ በሚካሄደው ጉባኤ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም እና የቀጣዩ ዓመት እቅዶች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

ይህ ጉባኤ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎችን በትውልድ በመክፈል በየዘርፋቸው
በማወዳደር በዓመቱ አፈጻጸማቸው የዓመቱን ደረጃ የሚሰጣቸው ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ መልኩ ደረጃ ተሰጥቷል፡፡

ከቀዳሚዎቹ ወይም የመጀመሪያ ትውልድ ከሚባሉት ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደ 2008 ዓ.ም ሁሉ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2009 ዓ.ም አፈጻጸሙ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ሲወጣ መቐለና ሀሮማያ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

ምንጭ ፦ ድሬ ትዩብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነችው ሀዊ ያዛቸው በ2009 ዓ.ም ነበር ለፋሲካ በዓል ቤተሰቦቿ ጋር ደርሳ ወደ ጅማ ስትመለስ የመኪና አደጋ የደረሰባት። ከዚያ ጊዜ አንስቶ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ብትቆይም ከትላንት በስቲያ ህይወቷ አልፏል። ቤተሰቦቿ፣የክፍሏ ተማሪዎች እና ጓደኞቿ በተገኙበት የቅብር ስነ ስርዓቷ በትላንትናው ዕለት ተፈፅሟል።

ሀዊ የ4ኛ አመት የባዮሜዲካል ተማሪ ነበረች።

እኛም...
በኢትዮጵያዊቷ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ፣ለጓደኞቿ እንዲሁም ለመላው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት መፅናናትን እንመኛለን!

ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው!
@tsegbawolde @tikvahethiopia @JUGALLANT
በኢትዮጵያዊቷ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ አመት የባዮሜዲካል ተማሪ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ፣ለጓደኞቿ እንዲሁም ለመላው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት መፅናናትን እንመኛለን!

🕯🕯ነብስ ይማር-ሀዊ🕯🕯

ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው!
@tikvahethiopia
ድምፅ ይስጡ📱ኢትዮ ቴሌኮም ከሚያገኘው ትርፍ አንፃር የሚሰጠውን አገልግሎት እንዴት ትመዝኑታላችሁ ?

በጣም ዝቅተኛ
መካከለኛ⭕️
ጥሩ

@tikvahethiopia
ዛሬ ወደ ደብረማርቆስ ሲያቀኑ የነበሩ በርካታ መኪናዎች ገብረ ጉራቻ በነበረው አለመረጋጋት ወደ የመጡበት ሊመለሱ ተገደዋል። ቁጥራቸውም ቀላል የማይባሉ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎችም እዛው ገብረ ጉራቻ ለማደር ተገደዋል። በተለይ ዛሬ ከበርካታ ከተማ ተነስተው ወደ ደብረማርቆስ ሲጓዙ የነበሩት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ናቸው። ወደ ስፍራው ደውዬ እንዳረጋገጥኩት ከሆነ ዛሬ ገብረጉራቻ የነበረው ሁኔታ ለጉዞ አስጊ ነበር። ጥዋት 1:30 ገድማ በተነሳ አንድ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ ከነበረች የአይን እማኝ እንደሰማሁት ወደ ደብረጉራቻ የደረሱት ከቀኑ 6:30 ገደማ ሲሆን እነሱ ሱደርሱ ህዝባዊ ሰልፍ እንደነበር ነግራኛለች። የነበሩበትን መኪና አሽከርካሪ የተወሰኑ ወጣቶች እጁ እንዲያጣምር እዳድረጉት እና ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ አሽከርካሪው ተሳፋሪውን ምሳ የግዴታ መብላት አለባችሁ በማለት ወደ አንድ ሆቴል እንዳስገባቸው ገልፃልኛለች። ወደ ሆቴሉ ከገቡ በኃላ ግን መ ውጣት እንዳልቻሉ እና ሁኔታው ጉዞ ለመቀጠል አስጊ መሆኑ እንዲሁም እዛው ሆቴል አልጋ ይዘው ለማደር መገደዳቸውን ገልፃለች። የአይን እማኟ እንደነገረችኝ ሁለት መኪናዎች ተቃጥለዋል። ነገሩን እጅግ አሳዛኝ የሚያደርገውም የተማሪዎች ዶክመንት እንዲሁም የተለያዩ እቃዎች አብሮ መቃጠሉ ነው። በርካታ መኪናዎችም ተሰባብረው ተመልክታለች። ከቦታው ወደፊትንም ሆነ ወደ ኃላ ጉዞ ለማድረግን አልቻሉም። አሁንም የሚገኙት እዛው ሆቴል ውስጥ ነው።

በተያያዘ ወደ ደብረ ማርቆስ ቴኬት የሸጡ የመጓጓዣ ባሶች ለተገልጋዮች ቴኬት እየመለሱ እንደሆነም ሰምቻለው።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በመክተት የመግቢያ ቀኑን እንዲያራዝም ተማሪዎቹ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፦ በተቃጠሉት መኪናዎች ምንም የሰው ህይወት አልጠፋም።

ሁኔታውን እየተከታተልኩ አደርሳችኃለሁ። የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ትልቅ አምላክ እንጂ ትልቅ ችግር የለም!

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tikvahethiopia
ቢንያም አስናቀው የተባልክ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ መታወቂያ ጥለህ የተገኘ ስለሆነ አ·አ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ብሎክ 502, ዶርም ቁጥር 225 በመሄድ መውሰድ ትችላለህ። ለበለጠው @Bisru_Me ማናገር ትችላለህ።

የምታውቁት ጓደኞቹ ይህን መልዕክት አድርሱት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
አውራምባ ታይምስ ድረ ገፁን "በተለያዩ ፈታኝ ምክንያቶች" ባላቸው ሁኔታዎች ከፊታችን እሁድ ኦክቶበር 22, 2017 ጀምሮ ለመዝጋት የሚገደድ መሆኑን ገለፀ።

መንግስትን በሚደግፉ ብዙ ፅሁፎቹ የሚታወቀው ሚድያው እ.ኤ.አ ከሜይ 2012 ጀምሮ ላለፉት አምስት አመታት የተለያዩ መረጃዎችን ሲያቀርብ ነበር።

"ለወደፊትም አቅማችን በፈቀደ መጠን... ቴክኖሎጂው በፈጠረልን ነጻ የማህበራዊ ሚዲያ "ፕላትፎርም" (Facebook፣ Youtube እና Twitter) አማካኝነት ለአገራችን ሰላም እድገትና ብልጽግና
ይጠቅማል የምንለውን ሀሳብ ማራመዳችንን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን" ሲል አዘጋጁ ዳዊት ከበደ ዛሬ ፌስቡክ ገፁ ላይ ፅፏል።

ምንጭ ፦ ENF
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በአለ-ስነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት በድግሪ መርሀግብር ለመማር የተመዘገባችሁ ፈተናው ዛሬ እንደሚሰጥ ይታወቅ ነበር። ዛሬ ፈተናው ያመለጣችሁ በነገው ዕለት ፈተናው ላመለጣቸው ፈተና የሚሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ነገ ከረፋዱ 3 ሰዓት ፈተናውን ሄዳችሁ እንድትወስዱ ለመግለፅ እንወዳለን። አጠቃላይ የተፈታኞች ቁጥር 130 ገደማ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ፈተናውን የወሰዱት 60 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ምንጭ ፦ @Deva21

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ2019 ዳይቨርሲቲ ቪዛ/ግሪን ካርድ ሎተሪ/ተብሎ የሚጠራው ዩናይትድ ስቴትስ በዕጣ ለውጭ ሃገር ሰዎች ቪዛ የምትሰጥበት መርሃ ግብር አዲስ የማመልከቻ ማስገቢያ ወቅት ከትላንት ጀምሮ ተጀምሯል።

ካሁን ቀደም የገቡ ማመልከቻዎች በቴክኒክ ዕክል ምክንያት ስለ ተሰረዙ አመልካቾች አዲስ ማመልከቻ ከትላንት እኤአ ኦክቶበር 18 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት 8 ጀምረው እስከ ኖቬምበር ሃያ ሁለት በኢትዮጵያ ህዳር 13 ቀን ድረስ እንዲልኩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቅርቡ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ ለተገደሉ ሰዎች ተጠያቂዎቹን የሚለይ ግልፅ ምርመራ እንደሚያስፈልግ በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ መንግሥት ሀሳብን በነፃነት መግለፅን እንዲፈቅድ እናበረታታለን ሲል መግለጫው አመልክቷል።

ምንጭ ፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ1 ሰዓት በኃላ እነዚህን ጉዳዮች ይዤ እመለሳለው ...

⚪️የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዛሬ ውሎ

⚪️የደብረ ማርቆስ ጉዳይ

⚪️በጅማ እና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተለጠፋት ማስታወቂያዎች

⚪️የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ

....ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን እና ጥቆማዎችን ይዤ እመለሳለሁ።

ከቲክቫህ ጋር ታመሻላችሁ?

@tsegabwolde @tilvahethiopia
ዛሬ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ተማሪዎች ከጥዋቱ 2 ሰዓት አንስቶ እስከ 5 ሰዓት በመንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እና ቅሬታ ማቅረባቸውን ከስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያሳያል። ዋና ጥያቄያቸው የነበረውም ፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለቆ ይውጣ እንዲሁም በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ የክልሉ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን ይከታተሉ የሚል ነበር።

በተጨማሪ ፦ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስብሰባ አድርገው የነበረ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳም ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችን የገንዘብ ማሰባሰብ እንዲደረግ ነው። ስብሰባውም በሰላም ተጠናቋል።

ምንጭ ፦ Jo

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዘገባዬ ላይ በገብረጉራቻ በነበረው አለመረጋጋት በአንድ ሆቴል ውስጥ ለማረፍ ተገደው ስለነበሩት ወደ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ ተማሪዎች እና ሌሎች ተጓዦች መረጃ አድርሻችሁ ነበር። እነዚሁ ተጓዦች ከለሊቱ 9 ሰዓት ተነስተው በሰላም ደብረማርቆስ መግባታቸውን እና ተማሪዎቹም ወደ ካምፓስ መግባታቸውን ወደ ቦታው ደውዬ ማረጋገጥ ችያለው።
ዛሬ በገብረጉራቻ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት የነበር ሲሆን መኪናዎችም ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሲያልፉ ተስተውሏል።

በነገራችን ላይ ትላንት በገብረጉራቻ መኪናዎች መቃጠላቸውን እና ንብረት መውደሙን ትልልቆቹ የዜና ማሰራጫዎችም ዘግበውታል።

ሌላው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመመዝገቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ከግቢው ተማሪዎች ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።

ትላንት በነበረው ሁኔታ በርካታ ተማሪዎች መንገድ ከጀመሩ በኃላ መመለሳቻው አይዘነጋም።

ምንጭ ፦ ባ(የአይን እማኝ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጅማ እና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(ASTU) የተለጠፉት ማስታወቂያዎች መነጋገሪያን ፈጥረዋል። ማስታወቂያዎቹ ላልተወሰነ ቀን ምንም አይነት ትምህርታዊ እንቅስቃሴ በግቢዎቹ አለመኖሩን የሚገልፁ ናቸው። ማስታወቂያዎቹ የተለጠፉት በተማሪዎች ሲሆን የዚህ ሁሉ መነሻ በመንግስት ላይ ያነሱት ቅሬታ ነው። እንደ ማስታወቂያዎቹ ከሆነ ላነሱት ጥያቄ ዩኒቨርሲቲው እና መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ነው የሚፈልጉት።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች እንደነገሩኝ ከትላንት ጀምሮ ትምህርት እንዳልተማሩ ነው።

በተያያዘ ፦ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ገቢ የማሰባሰብ ኘሮግራም በተማሪዎች እየተካሄደ እንደሚገኝ ሰምተናል። ይህን መሰሉ ሰናይ ተግባር ይቀጥል እንላለን።

@tikvahethiopia @tsegbawolde
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪግ የትምህርት ዘርፍ የተመደቡ ተማሪዎች ያለ ፍላጎታቸው እና ያለፍቃዳቸው ወደ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ሲስተም ወደተባሉ የትምህርት ዘርፎች እንዲመደቡ መደረጋቸውን ተማሪዎቹ ገለፁ። የተጠቀሱት የትምህርት ዘርፎች ኢንጂነሪንግ በመባል የማይጠሩ እና እራሳቸውን ችለው እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ የሚቆጠሩ ናቸው።

450 የሚደርሱ ተማሪዎች ቅድመ ምህንድስና(ፕሪ ኢንጂነሪንግ) እንዲማሩ ሲደረግ ሌሎቹ ግን ወዳልፈለጉት የትምህርት ዘርፍ ተመድበዋል።

ተማሪዎቹ ጉዳዩን ይዘው ወደ ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ቢያመሩም ይህ እኛን የሚመለከት ሳይሆን ዩኒቨርሲቲውን የሚመለከት ጉዳይ ነው ተመዝግባችሁ ወደ ትምህርት ሚንስትር ሂዱ በማለት መልሷቸዋል።

አጠቃላይ ተማሪዎቹ ወደ 300 የሚጠጉ ሲሆን ምርጫቸውን የሚያስጠብቅ ውጤት ይዘው(500,507,510...) ዩኒቨርሲቲው ይህን በማድረጉ እጅግ በጣም እንዳዘኑና የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ምንጭ ፦ BkAb እና Real 1
@tikvahethiopia @tsegabwolde
እምነት ማለት ፈጣሪ የምትፈልገውን እንዲያደርግልህ ማመን ሳይሆን፤ፈጣሪ በስራው ትክክል መሆኑን ማመን ነው።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tikvahethiopia
👍1
ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸው በምርት ሽያጮች ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተለዩ ነጋዴዎች
ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን የንግድ ውድድር እና የሸማቾት ጥበቃ ባለስልጣናት አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጭማሪ መታየቱን ባለስልጣኑ ባደረገው ዳሰሳና የህብረተሰብ ጥቆማ ማረጋገጡን
አመልክቷል፡፡ በተለይ የኤሌክትሮኒክስ እና የግንባታ ዕቃዎች ሰፊ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

በመሆኑም ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከህብረተሰቡ በተገኙ ጥቆማዎች እና በዳሰሳ በተለዩ ነጋዴዎች ላይ ክስ ለመመስርት ልየታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ምንጭ ፦ ኢብኮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia