TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቆሼ አደጋ የነፍስ ማዳንና የአስክሬን ማውጣት ሥራ ተሰማርተው የነበሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ቃል የተገባላቸው ገንዘብ እንዳልተሰጣቸው ግለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰጠውን ምላሽ ከላይ ተጭኗል አድምጡት..

ምንጭ ፦ ሸገር 102.1

@tikvahethiopia
😡ዛሬ የኔትዎርክ መቆራረጥ በቂ መረጃዎችን እንዳላደርሳችሁ አድርጎኛል ለዚህም ይቅርታ ጠይቃለው።
🥰1
በፈተና የሚፀና የተባረከ ነው። ፈጣሪ ለሁላችንም ትዕግስቱን ፅናቱን ያድለን። አሜን የሚል

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊1
⚪️🔘አሳዛኝ ዜና🔘⚪️

አንድ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ አመት የኮፒዩተር ሳይንስ ተማሪ አረፈ። ተማሪው ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ጉብሬ በሚባል ቦታ (ከዩኒቨርሲቲው ፊትለፊት) በመዝናናት ላይ እንደነበር ከቤቱ ቦዲ ጋርድ(ጠባቂ) ባልታሰበ ሁኔታ በስስ የሰውነቱ ክፍል ላይ በመመታቱ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ ተሰምቷል።

በአሁን ሰዓት መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከባድ ሀዘን ውስጥ ይገኛል። ቻናላችንም ለቤተሰቦቹ፣ጓደኞቹ እንዲሁም ለመላው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ ፦ እስራኤል(4ኛ የፉድ ፕሮሰስ ኢንጂነሪንግ ተማሪ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde
😢2
አቶ ለማ መገርሳ #BreakingNews »» Loading
🔘⚪️ሰበር ዜና⚪️🔘

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከሚዲያ ርቀው እና ጠፍተው የነበሩት የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘደንት ለማ መገርሳ ለህክምና ህንድ ደልሂ እንደሚገኙ ተሰማ።

አቶ ለማ መገርሳ ባለፉት 8 እና 9 ቀናት በህንድ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ናቸው። አቶ ለማ ክልሉን ማስተዳደር ከጀመሩ ወዲህ በርካታ ለውጦች የታዩ እና በበርካታ ህዝባዊ ሰልፎች ላይ ወጣቶች አመራራቸውን ሲያውድሱ ተስተውሏል።

ምንጭ ፦ ENF

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ይጠንቀቁ❗️

አንድ አንድ ሰዎች በፌስቡክ እና ቴሌግራም በኩል ልክ ከላይ በስዕሉ እንደምታዩት በስልካቹ
ጽፋቹ ላኩ፣ነጻ የኢንተርኔት ጥቅል ያገኛሉ በማለት ለመሸወድ እየሞከሩ ነው። እንዳትታለሉ! ይህ አገልግሎት የኢትዮ ገበታ የስጦታ አገልግሎት ሲሆን ከርስዎ ስልክ በመቀነስ ስልክ ቁጥሩ ወደተጻፈው ቁጥር (091XXXXX) እንዲልክ ያደርጋል። ስለዚህ ከማያውቁት ሰው እንደዚ አይነት መልእክት ሲደርስዎ ወይም ደሞ ፖስት ተደርጎ ካዩ እንዳይሸወዱ። ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ።
👍1
ዛሬ ጥዋት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እና ተቃውሞ አሰሙ። ተማሪዎቹ በእጆቻቸው የ"X" ምልክት በመጠቀም በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እንዳሰሙ በቦታው ከነበሩ ሰዎች ለመረዳት ተችሏል። የግቢው አስተዳደርም ተማሪዎቹ ማነጋገሩ ታውቋል። ሁናቴው እጅግ በጣም ሰላማዊ ነበር። በአሁን ሰዓት ግቢው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው ተመልሷል።

ምንጭ ፦ አማን
@tikvahethiopia
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን የሚገኝበት ገፅታ ጥቅምት 7/2010 ዓ.ም

ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር , EBC

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ባለስልጣናት ግን እንደ ቴዲ ነጠላ እየለቀቁ ለምን ያጓጉናል ? ምናለበት ሙሉውን ለቀው ቢያስደስቱንና ብንጨፍርበት!

🔹አበበ ትዕግስት ገበየሁ🔹

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የአቶ በረከት ስምዖንን የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አስመልክቶ ትላንት ምሽት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ያናገራቸው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ ሚንስተር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ይህን ተናግረው ነበር
"እኛም ከሚዲያ ነው የሰማነው"

ዛሬ ደግሞ ፋና ሬድዮ ለተባለው የሀገር ውስጥ የሚዲያ ተቋም እንዲህ ብለዋል..

"አቶ በረከት ስምኦን በፍቃዳቸው ከስልጣናቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸው አረጋግጠናል፡ ምክንያታቸው ግን አላወቅንም።"

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት የአብላጫ ድምፅ እና የተመጣጣኝ ውክልናን ያቀፈ “ቅይጥ ትይዩ” እንዲሆን ከአንድ
የፖለቲካ ፓርቲ በስተቀር ሁሉም ተስማምተዋል።

ፓርቲዎቹ በምርጫ ስርዓቱ ላይ የተስማሙ ቢሆንም፥የአተገባበር ሂደቱ ከየትኛው ምክር ቤት ይጀምር በሚለው ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን አቅርበዋል።

ቅይጥ ትይዩ የሚባለው በአብላጫ ድምፅ እና በተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት በየምርጫ ክልሉ አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ፓርቲ የሚያሸንፍበት ነው ተብሏል።

ተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት ደግሞ ፓርቲዎች በምርጫ ክልሎች የሚያገኙትን ድምፅ ለምክር ቤቶች ወንበር በማካፈል ወንበር እንዲያገኙ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ተነግሯል።

በዚህም የአብላጫ ድምፅ እና የተመጣጣኝ ውክልና በምን ያህል መቶኛ ይሁን የሚለውም የፓርቲዎቹ የልዩነት ሀሳብ ነው።

ኢህአዴግ በፌዴራል፣ በክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች የምርጫ ስርዓቱ እንዲተገበር የሚፈልግ መሆኑን በድርድሩ አቅርቧል።

90 በመቶ የፓርላማ ወንበር በአብላጫ ድምፅ ፣ 10 በመቶ
ደግሞ በተመጣጣኝ ውክልና የሚያዝ መሆኑን ባቀረበው የድርድር ሀሳብ ገልጿል።

ኢዴፓ፣ መኢአድ ጨምሮ የ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ደግሞ የቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓቱ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ባሉት ምክር ቤቶች ቢተገበር ፍላጎታቸው መሆኑን በልዩነት ሀሳባቸው አቅርበዋል።

በምክር ቤቶቹ ወንበሮች 50 በመቶ በአብላጫ ድምፅ፣50 በመቶ ደግሞ በተመጣጣኝ ድምፅ እንዲያዝ የሚል ሃሳብም በድርድራቸው አቅርበዋል።

መኢብን፣ መኦዴፓ እና የገዳ ስርዓት ፓርቲዎች የቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት ተግባራዊ ቢደረግ እንደሚስማሙ ገልፀው፥ በአተገባበር ሂደቱ ላይ ልዩነት ነው የጠቀሱት።

ኢራፓ በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት የማይስማማ መሆኑን በመግለፅ፥ በአብላጫ ድምፅ 52 በመቶ የፓርላማው ወንበር እንዲያዝ እና 48 በመቶ ደግሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲወዳደሩበት የሚል ሀሳብን አቅርቧል።

ፓርቲዎቹ በአብላጫ ድምፅ እና በተመጣጣኝ ድምፅ በቀረቡ የመቶኛ ድርሻ ላይ ከድምዳሜ መድረስ አልቻሉም።

ከምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል መቶኛው በአብላጫ፣ምን ያህሉ በተመጣጣኝ ድምፅ መያዝ አለበት በሚለው ላይ ከፓርቲዎቻቸው ጋር በመምከር የውሳኔ ሀሳብ ይዘው ለመቅረብ ለመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2010 ቀጠሮ ይዘዋል።

በምርጫ ስርዓቱ ላይ 16 ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች እየተደራደሩ ይገኛሉ።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

@tikvahethiopia @tsegabwolde
👍1
ሰሜን ኮሪያ በማንኛውም ሰአት የኒውክሌር ጦርነት ሊጀመር ይችላል ስትል አስጠነቀቀች። ትንሽ ቀዝቅዞ የነበረው የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጉዳይ ዳግም አግርሽቷል።

ምንጭ ፦ አልጀዚራ

@tikvahethiopia @tsegabwolde
በሀገራችን የስኳር እጥረት እንዳለ የሚታወቅ ነው። ኢቢሲ(EBC) ዛሬ "ስኳር ማብዛት ለካንሰር ያጋልጣል" ብሎ በፌስቡክ በለጠፈው የጥናት ውጤት ኢትዮጵያዊያን አዝናኝ አስተያየቶችን ሲሰጡ ውለዋል እኔም ለእናተ ጥቂቱን መረጥኩላችሁ ....

Bisrat Tademe

"kk..ኧረ? በቃ ይቅርብና ውጪ ይሸጥና አለምን በካንሰር ጨርሱት እኛ ጤና እንሁን።እንኳን ጠፋ ስኳር የታባቱ ድሮም ያለምክንያት አልጣፈጠም።"

Musema Jemal

'ወዴት ወዴት ነው ነገሩ? ምነው የመብራቱን ጥናት ረሳችሁትሳ? " መብራት አዘውትሮ ማብራት ለትራኮማ ያጋልጣል" ይላሉ አንዳንድ ጥናቶች ሃሃሃሃ ድሮም ሙጀሌ የሚፈነዳው ሲያብጥ ነው አለች አያቴ"

Gezahegn Hailu

"መንግስታችን የህዝቦቹን ጤንነት ከካንሰር ለመጠበቅ ሲል በቅርቡ 40ሺህ ኩንታል ስኳር ላይ የወሰደውን እርምጃ ከልብ እናደንቃለን!"

yeabatu lij

"እድሜ ለፀሐዩ መንግስታችን አርቆ አሳቢ ስለሆነ ይኸው ስኳር ካዬን 3 ወር ሞልቶናል..EBC ደግሞ መናፈቃችንን አውቀሽ..በሽታ ነው አይጠቅማችሁም...አውቀን ነው ያጠፋነው አልሽን! እናመሰግናለን። እናንተ ባትኖሩ ማን ይመክረን ነበር?"

Fish O'two

"ስኳር ሲጠፋ በዚህ መልኩ ህዝብ ስኳር እንኳን ቀረብኝ እንዲል መስራት ጀመራችሁ። ነገ ደግሞ ፋብሪካዎቹ የተሳካላቸው እለት ስለ ስኳር ጥቅም የሚዘግብ አዲስ ጥናት እንደማታጡ ተስፋ አደርጋለሁ።"

ምንም እንኳን በስኳር መጥፋት የተማረራችሁ ብዙ ብትሆኑም አስተያየቶቹ እንዴት ናቸው?

@tikvahethiopia @tsegabwolde
👍31
ሆሆ...ሰው ሁሉ ቀልደኛ እየሆነ ነው። ተመልከቱት ይሄን በ100 ብር መርፌ ስጠኝ ሲል😂😂😂

ሰሞኑን በሀገሪቷ ቀልድ በሁለት አሀዝ እያደገ ነው።😂ኑሮ...

@tikvahethiopia @tsegabwolde
👍1
ትላንት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ መንግስትን የሚቃወም ሰልፍ እንደነበረ ቅሬታ ያላቸውም ሰዎች ቅሬታቸውን መግለፃቸውን መረጃ አድርሻቹ ነበር።

ዛሬ ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥ በመንግስት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ድምፃቸውን አሰምተዋል። በተፈጠረው ሁኔታም በትምህርት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥለው እንዲወጡ ተገደዋል።

የቅሬታ አቅራቢዎቹ ጥያቄ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የኦሮሚያ ክልል ልጆች እዛው ጅማ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩበት እድል እንዲመቻች ነው።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር(በተለይ ፕሬዘደንቱ) እስከ መጭው ሰኞ ድረስ መልስ እንደሚሰጧቸው እና እንደሚያናግሯቸው እምነታቸው እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ በወቅቱ መግለፃቸውን በቦታው የነበሩ ሰዎች ገልፀዋል።

መንግስት በየቦታው እየተነሱ ያሉ ሰላማዊ ጥያቄዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ እንዲሁም በቂ ምላሽም እንደሚሰጥም ይጠበቃል።

ምንጭ ፦ DM

@tikvahethiopia
1
⭕️ ሰሜን ኮሪያ እና አሜሪካ ⭕️

በፒዮንግያንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው የኒውክሌር ፍጥጫ እያደር እያየለ በመጣበት ባሁኑ ወቅት፤ ለሠላማዊ መፍትሔ ያለው ተስፋ እየተመናመነ እና ወታደራዊ ግጭት የመከተሉ አደጋ በአንጻሩ መሆኑን የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ አጥኚዎች እየተናገሩ ነው።

የሰሜን ኮሪያ እና የአሜሪካ መጨረሻ ምን ይሆን ? አብረን እናየዋለን...

ምንጭ ፦ የአሜሪካ ድምፅ

@tikvahethiopia @tsegabwolde
በራስ ጥበብ በጣም እርግጠኛ መሆን መልካም አይደለም። ጠንካሮች ሁሉ እንደሚደክሙ እና ጠቢባንም እንደሚሳሳቱ ማስተዋል ይጠቅማል።

⭕️⭕️ማህተመ ጋንዲ⭕️⭕️

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia