መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የሆድ #ድርቀት/Constipation

የሆድ ድርቀት የአንጀት ጡንቻዎች የእንቅስቃሴ ድግግሞሽ በቁጥር ሲያንስ ወይም ዓይነ ምድራችንን ለማስወገድ/ ለማስወጣት መቸገር ሲሆን ይህ ሁኔታ ለጥቂት ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ቆይታ ሲኖረው ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ መሃል ያለው የጊዜ ልዩነት ከሰዎች ሰዎች ይለያያል፡፡
አንዳንድ ሰዎች በቀን ሶስት ጊዜ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ ያለምንም የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ሶስት ቀን ከሆነ በጣም እረጂምና አደገኛ ሲሆን ከሶስት ቀን በኋላ ዓይነ ምድራችን ስለሚደርቅ ወይም ጠንካራ ስለሚሆን ለማስወገድ/ለማስወጣት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
የሆድ ድርቀትን ጠቅለል ባለ ሁኔታ ለመግለጽ ያክል የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሶስት ጊዜ በታች/ያነሰ ሲሆን ነው፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ የሆድ ድርቀት በአጋጣሚዎች የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ከባድ የሆድ ድርቀት ያጋጥማቸዋል ይህም የቀን ከቀን ስራቸውን ያስተጓጉላል፡፡
የሆድ ድርቀት መነሻዎች!
የሆድ ድርቀት በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ዓይነ ምድራቸን በምግብ መፍጨት ስርዓት ውስጥ ሲያልፍ በጣም በሚዘገይበት ጊዜ ይፈጠራል ይህም ዓይነ ምድራችን ጠንካራ እና ደረቅ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ የሚከተሉት የሆድ ድርቀት መነሻዎች ናቸው፦
👉በቂ ውሃ አለመጠጣት
👉በምግብ ገበታዎ ውስጥ በቂ ያልሆነ ፋይበር አለመኖር
👉መደበኛ የምግብ ሠዓት መስተጓጎል(በጉዞ ወቅት)
👉በቂ የሆነ እንቅስቃሴ አለማድረግ
👉ከፍተኛ መጠን ያለው የወተት ተዋጽዎ መመገብ
👉ጭንቀት
👉ሃይፖታይሮይዲዝም
👉 ከመጠን በላይ የዓይነ ምድር ማለስለሻ(Laxatives) መጠቀም
👉የአንጀት ወይም ፊንጢጣ መደፈን/መዘጋት
👉በአንጀት እና ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ ነርቮች ችግር/በሸታ ፓርኪንሰንስ በሽታ የጀርባ አጥንት ጉዳት ስትሮክ
👉ዓይነ ምድር ለማስወጣት መቸገር የዳሌ ጡንቻዎች በተቀናጀ ሁኔታ መጨማደድና መዝናት አለመቻል ደካማ የዳሌ ጡንቻዎች
👉የሰውነታችን ሆርሞኖችን የሚጎዱ ሁኔታዎች የስኳር በሽታ እርግዝና የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
👉የአንጀት እና ፊንጢጣ ካንሰር።
#የሆድ #ድርቀት #ምልክቶች!
የሆድ ድርቀት ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
👉 የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ድግግሞሽ ማነስ
👉ደረቅ እና ጠንካራ ዓይነ ምድር
👉 በመጠን ትንሽ የሆነ ዓይነ ምድር
👉የሆድ መነፋት ወይም የሆድ ህመም
👉ህመም
👉ማስታወክ/ማስመለስ
👉በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች መጸዳዳት
👉በምንጸዳዳበት ጊዜ ፊንጢጣችንን ከዓይነ ምድር ባዶ አለማድረግ ወይም ጨርሰን አለመጸዳዳት
👉ስንጸዳዳ ዓይነ ምድራችንን ለማውጣት እርዳታ መፈለግ ለምሳሌ፦ ዓይነ ምድርን ከፊንጢጣ ለማውጣት ጣትን መጠቀም፡፡
#የሆድ #ድርቀት #እንዴት #ሊታከም #ይችላል?
አብዛኛዎቹ ሰዎች ከባድ የሆነ ምርመራ አያስፈልጋቸውም በጣም ጥቂት የሚባሉት ደግሞ ከባድ የህመም ችግር ስለሚያጋጥማቸው ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በላ የቆየ የሆድ ድርቀት ካጋጠምዎት የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልግዎታል፡፡ ይህ የሆድ ድርቀት በአንጀት ካንሰር ከተከሰተ ቅድሚያ ማወቅና መታከም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የሆድ ድርቀትን መነሻ ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉትን ያካትታል፦
👉የደም ምርመራ፦ የሆርሞኖች አለመመጣጠን የሚጠረጠር ከሆነ
👉የባርየም(Barium) ጥናት፦ የአንጀት መዘጋት የሚጠረጠር ከሆነ
👉 ኮሎኖስኮፒ፦ የአንጀት መዘጋት/መታገድን ለማወቅ ይጠቅማሉ፡፡
የሆድ ድርቀት ካጋጠመኝ ምን ማድረግ አለብኝ?
የሆድ ድርቀት ካጋጠምዎት የሚከተሉትን ይሞክሩ፦
👉ከሁለት እስከ አራት ተጨማሪ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ
👉ሞቅ ያለ ፈሳሽ ይጠቀሙ በተለይ ጠዋት ላይ
👉የምግብ ገበታዎ ላይ ፍራፍሬና አትክልቶች ይጨምሩ
👉የጥራጥሬ ውጤቶችን ይመገቡ
👉አስፈላጊ ከሆነ በጣም በጥቂቱ የዓይነ ምድር ማለስለሻዎች ይጠቀሙ ለምሳሌ፦ ሚልክ ኦፍ ማግኒዚያ
👉ሃኪምዎን ሳያማክሩ የዓይነ ምድር ማለስለሻ ወይም ላክሳቲቭ ከሁለት ሳምንት በላይ አይጠቀሙ ምክንያቱም ከመጠን በላይ ላክሳቲቭ መጠቀም ምልክቶቹን ያባብሳቸዋል፡፡
የሆድ ድርቀትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የሆድ ድርቀትን ለመከላከል የተለያዩ መንገዶች አሉ ከነዚህም መካከል፦
👉የተመጣጠኑ ምግቦችን በተለይ ፋይበር በብዛት ያላቸውን ይመገቡ፡፡ ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ያላቸው ምግቦች፦ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ለጊዩም፣ ዳቦና ጥራጥሬዎች ናቸው፡፡ ፋይበር እና ውሃ አንጀታችን ዓይነ ምድርን በቀላሉ እንዲያሳልፍ ያደርገዋል፡፡
👉ከአንድ ሊትር ተኩል እስከ ሁለት ሊትር ተኩል ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾችን በቀን መጠጣት ጠቃሚ ነው(ውሃ መጠጣት በሌሎች የህክምና ችግር እስካልተከለከልን ድረስ)፡፡
👉ካፌን የያዙ/ያላቸው ፈሳሾች ለምሳሌ፦ ቡና እና ለስላሳ መጠጦች የሰውነት ፈሳሽን የማድረቅ ባህሪ ስላላቸው አጠቃቀማችንን መቀነስ አለብን፡፡ አንዳንድ ሰዎች ወተት ሲጠጡ ስለሚያባብስባቸው ቢቀንሱ ይመረጣል፡፡
👉በየጊዜው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ፡፡
ስለ ሆድ ድርቀት ማስጠንቀቂያ!
የሚከተሉት ነገሮች የሚከሰቱ ከሆነ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ይሂድ፦
👉የሆድ ድርቀት ለእርስዎ አዲስ ችግር ከሆነ
👉በዓይነ ምድርዎ ውስጥ ደም ካለ
👉የክብደት መቀነስ ካለ
👉የአንጀት ጡንቻዎች ህመም ካለ
👉የሆድ ድርቀት ችግርዎ ከሁለት ሳምንት በላይ ከሆነ፡፡
መልካም ጤና!!