መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#አልኮል #መጠጣት #ለምን #ያወፍራል?

መጠኑ ይለያይ እንጂ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች መውሰድ በየትኛውም ማህበረሰብ የተለመደ ነው። አልኮል በመጠኑ ሲወሰድ የተለያዩ የማህበራዊና የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም ከልክ ሲያልፍ ግን መዘዙ ብዙ ነው። የአዕምሮ መመሳቀል፣ የስኳር እና ጉበት በሽታ፣ ሱስኝነት እና መሰል ጉዳቶች አልኮልን ከማዘውተር የተነሳ የሚከሰቱ የጤና እክሎች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አልኮል የሚያዘወትሩ ሰዎች ለከፍተኛ ውፍረት እንደሚጋለጡ ነው የሚነገረው። ከአልኮል የምናገኘው ካርቦሃይድሬት፣ ፕሮቲን እና ስብ ምንም አይነት የምግብ ይዘት የሌለው መሆኑም ሰውነታችንን ለበርካታ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆን ያደርጋል። ከዚህ በታችም አልኮል ለሰውነት ክብደት መጨመር ያለውን አስተዋጽኦ እንመለከታለን።
#አልኮል፡-
👉ሰውነታችን በርካታ ኤስትሮጂን እንዲያመርት ያደርጋል
ኤስትሮጂን በሰውነታችን ውስጥ የስብ መከማቸትን ከማሳደጉም ባሻገር የጡንቻ ጥንካሬ እንዲቀንስ ያደርጋል።
👉የምግብ ፍላጎትን ያሳድጋል
አልኮል የምግብ ፍላጎታችን እንዲጨምር በማድረግ ከልክ በላይ እንድንመገብ ያበረታታል።
አንዳንድ ሬስቶራንቶችም ከምግብ በፊት የአልኮል መጠጦችን ማቅረባቸው ደንበኞቻቸው የሚወስዱት የምግብ ፍጆታ እንዲጨምር በማሰብ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።
👉የስብ መቃጠልን ያዘገያል
ጉበታችን የምንጠጣውን አልኮል ወደ ኮምጣጤነት በመቀየር ሲጠመድ የሰውነታችንን ስብ በማቅለጥ ሃይል ከማግኘት ይልቅ ከኮምጣጤ ሃይል ለማግኘት ይገደዳል።
ኮምጣጤ የስብ መቅለጥንና የሃይል ምንጭነትን ሲተካም ውፍረት ይከሰታል።
አንድ ጥናት አልኮል አብዝተን የምንወስድ ከሆነ ሰውነታችን እስከ አራት ቀናት ያህል ስብን ማቅለጥ እንደማይችል አመላክቷል።
👉የድካም ስሜት ይፈጥራል
አብዝቶ መጠጣት ለውሃ ጥም በመዳረግ እና በማዳከም ክብደትን በተሻለ ፍጥነት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ይጎዳል።
በአልኮል ምክንያት የሚከሰት የውሃ ጥም ለቆዳ መሸብሸብ እና ድርቀትም ያጋልጣል።
👉የስኳር መጠኑ ከፍተኛ ነው
አልኮል የተፈጥሯዊ ምግቦች ጭማቂ እንደመሆኑ ከፍተኛ የስኳር ይዘት አለው፤ ይህም በቀላሉ ለውፍረት ያጋልጣል።
👉ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ ማዕድናት (ሚኒራሎችን) ያሳጣል
አልኮል እንደ ማግኔዢየም፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም እና ዚንክ ያሉ የስብ መቅለጥን የሚያፋጥኑ ማዕድናትን እንደሚያሳጣ ይነገራል።
👉የመነቃቃትን ስሜትን ያዳክማል
አልኮል አዕምሯችን ተግባሩን በአግባቡ እንዳይወጣ በማድረግ ለጭንቀትና ድብርት ከመዳረጉም በዘለለ ክብደት ለመቀነስ የሚደረግ እንቅስቃሴን በንቃት ገቢራዊ እንዳናደርገው ያደርጋል።
በአጠቃላይ አልኮል ምንም እንኳን በተለምዶ ክብደትን ይቀንሳል እንጂ ይጨምራል ተብሎ ባይታሰብም ከላይ የተመለከትናቸውና ሌሎች በርካታ ምክንያቶች አልኮል የውፍረት ምንጭ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል።
@melkamtenaa
ምንጭ፡- www.nowloss.com