መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የሀሞት #ጠጠር

Cholilitiasis ወይም በCholi (stone) የተነሳ በሃሞት
ቀረጢት ላይ የሚከሰት መቆጣት Cholilitiasis እንለዋለን
የሀሞት ጠጠር በምን የተነሳ ይከሰታል፣ ምክንያቱስ ምንድንነው?
ለማን ና በምን ሁኔታ ይከሰታል? ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
የሚለውን ዛሬ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
የሀሞት ጠጠር እንዴት ይፈጠራል?
ሰውነታችን የሰጠነውን ተቀብሎ በጥሬ ፈጭቶ አዋህዶ ወደ
ጉልበት መቀየር ብቻ አይደለም ስራው ውህድን ከውህድ
አደባልቆ ሌላ አዲስ ውጤት መፍጠርም ከሚሰራቸው ስራዎች
ውስጥ አንዱ ነው የሀሞት ከረጢት በቀኝ በላይኛው ክፍል
ከጐድን አጥንታችን የታችኛው ክፍል ከጉበትና ከጣፍያ ጋር
ተገናኝ ታትገኛለች የሀሞት ከረጢት በውስጧ ሀሞት የተባለ
መራራ ቢጫ ፈሳሽ ይመረትባታል፡፡ ይሄ መራራ ቢጫ ፈሳሽ ስብን
ለመበተንና የሚጠቅም ሲሆን ጮማ በሚያዘወትሩ ሰዎች ላይ
በብዛት ሊታይ ይችላል
የሀሞት ከረጢት የሚያመርተው ይሄ ፍሳሽ የብዙ ውህዶች
ውጤት ነው፡፡ የውህዶች ማለትም የፍሳሽና የጠጠር መጠን
መለያየት የሀሞት ጠጠር መፍጠር ምክንያት ይሆናል፡፡
እንደሚፈጠረው የጠጠር አይነት የውህዶቹን መብዛት መለየት
ይቻላል፡፡
የሀሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ምልክቶቹ እንደ ጠጠሩ ትልቀትና መጠን የሚለያይ ሲሆን ይሄ
የተፈጠረው ጠጠር የሀሞት ከረጢት በምትንቀሳቀስበት ጊዜ
ጠጠሩ ወደ ዋናው መውጫ በር በመግባት ሊዘጋ ወይም
ከመውጫው አልፎ ወደ ጣራያ የሚወስደውን ዋናውን ግንድ
(common bile dut) ሊዘጋ ይችላል ይሄም በቀኝ የላይኛው
የሆድ ክፍል ላይ ከፍተኛ ሕመም ሊያስማን ይችላል
👉ማቅለሽለሽና ማስታወክ
👉ስብ ያላቸው ምግቦችን ወይም alchol ያላቸው መጠጦች
ብንወስድ የሚመጣ ቁርጠት እና ማስመለስ እንዲሁም ትከሻ
ላይ የማመም ስሜት
የሚያጋልጡ ነገሮች
👉 እድሜ>40
👉 ፆታ - ሴት
👉ውፍረት
👉 አመጋገብ cholesterol እና ስብ ያለባቸው
👉 አልኮል
👉ጭንቀት
👉ፈጣን የሆነ የኪሎ ለውጥ (መቀነስ)
#የሀሞት #ጠጠር #እንዴት #ይታከማል
ሕክምናው እንደ ጠጠሩ ብዛትና ትልቀት የሚወሰን ሲሆን
መድሃኒት ጀምሮ ኦፕራሲዮን ድረስ ሊሆን ይችላል
👉ስለዚህ ሕመሙ ከተሰማዎት ወይም እንዳለብዎት ከተጠራጠሩ
(Ultrasound) በመነሳት
የጠጠሩን መጠንና ብዛት ማወቅ
ይቻላል፡፡
@melkamtenaa