#በወር #አበባ #ጊዜ #የሚከሰት #ሕመም #በምን #እንከላከል?
ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት
ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ
መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡
የሕመሙ መጠን ከሰው ሰው የሚለያይ ሲሆን አንዳንዴም
የእለት ኑሮን እስከማቃወስ ይደርሳል፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሕመም ስሜት እንዲሰማ ተጋላጭነትን
የሚጨምሩ ሁኔታዎች
ዕድሜ
👉ከ30 ዓመት በላይ
👉ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ
👉ልጅ ያልወለዱ ከሆነ
👉በወር አበባ ጊዜ ከፍተኛ ሕመም የሚሰማው የቤተሰብ
አባል ካለዎት
👉 ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ናቸዉ፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ የሕመም ምልክቶች?
👉የሆድ ቁርጠት
👉የማያቋርጥ ከዕምብርት በታች ያለ የሕመም ስሜት
👉 ወደ ጀርባ ወደምጥ የሚሄድ ዓይነት ስሜት
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሴቶች
👉የማቅለሽለሽ
👉ተቅማጥ
👉የራስ ምታት
👉ማዞር የመሳሰሉት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰትን ሕመም ለማስታገስ?
👉የሞቀ ውኃ ያለበትን የውኃ መያዣ ላስቲክ በሆድዎ አካባቢ
ማስቀመጥ የሚሰማዎን ሕመም ያስታግሳል
👉በኦሜጋ 3 እና በቫይታሚን ኢ፣ቢ-6፣ቢ-1 እና
ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ይመከራል
👉የአልኮል መጠጦችንና ሲጋራ ማጨስን መስወገድ
👉ጭንቀትን በተቻለ መጠን መቀነስ
👉ለሕመም ማስታገሻነት የሚጠቅሙ መድኃኒቶችንም
መጠቀም ናቸው፡፡
የህመም ስሜቱ እጅግ ከፍተኛ ከሆነ እና ለህመሙ
መንስኤ በህክምና የተረጋገጠ ምክንያት ካለ ከሀኪምዎ ጋር
መማከር እና ተገቢዉን ህክምና ማድረግ ይመከራል፡፡
ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት
ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ
መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡
የሕመሙ መጠን ከሰው ሰው የሚለያይ ሲሆን አንዳንዴም
የእለት ኑሮን እስከማቃወስ ይደርሳል፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሕመም ስሜት እንዲሰማ ተጋላጭነትን
የሚጨምሩ ሁኔታዎች
ዕድሜ
👉ከ30 ዓመት በላይ
👉ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ
👉ልጅ ያልወለዱ ከሆነ
👉በወር አበባ ጊዜ ከፍተኛ ሕመም የሚሰማው የቤተሰብ
አባል ካለዎት
👉 ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ናቸዉ፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ የሕመም ምልክቶች?
👉የሆድ ቁርጠት
👉የማያቋርጥ ከዕምብርት በታች ያለ የሕመም ስሜት
👉 ወደ ጀርባ ወደምጥ የሚሄድ ዓይነት ስሜት
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሴቶች
👉የማቅለሽለሽ
👉ተቅማጥ
👉የራስ ምታት
👉ማዞር የመሳሰሉት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰትን ሕመም ለማስታገስ?
👉የሞቀ ውኃ ያለበትን የውኃ መያዣ ላስቲክ በሆድዎ አካባቢ
ማስቀመጥ የሚሰማዎን ሕመም ያስታግሳል
👉በኦሜጋ 3 እና በቫይታሚን ኢ፣ቢ-6፣ቢ-1 እና
ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ይመከራል
👉የአልኮል መጠጦችንና ሲጋራ ማጨስን መስወገድ
👉ጭንቀትን በተቻለ መጠን መቀነስ
👉ለሕመም ማስታገሻነት የሚጠቅሙ መድኃኒቶችንም
መጠቀም ናቸው፡፡
የህመም ስሜቱ እጅግ ከፍተኛ ከሆነ እና ለህመሙ
መንስኤ በህክምና የተረጋገጠ ምክንያት ካለ ከሀኪምዎ ጋር
መማከር እና ተገቢዉን ህክምና ማድረግ ይመከራል፡፡