መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የአእምሮ #ጤንነት
#ለአንጎል #ጎጂ #የሆኑ #ልማዶች


👉#ቁርስ #አለመመገብ
ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።
👉#በህመም #ወቅት #በቂ #እረፍት #አለማድረግ
ሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖር ይረዳል።
👉#ሲጋራ #ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባ ካንሰር እና ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
👉#ከፍተኛ #የስኳር #መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።
👉#የአየር #ብክለት
አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።
👉#የእንቅልፍ #እጦት
እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።
ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡
👉#የአልኮል #መጠጥ #ማብዛት
በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
👉#የምግብ አይነቶችን መምረጥ
ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።
ጤና ይስጥልኝ