#ሾተላይ (የጽንስ መጨንገፍ)
በተለምዶ ሾተላይ “በእንግሊዘኛው Rh-Incompatablitiy” በሚባለው ችግር ብዙ ሰዎች ወልደው መሳም ፈልገው ሳይችሉ መቅረታቸውን፣ በዚሁ ምክንያት አያሌ ቤተሰብ እንደተበተነ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው፡፡ ሾተላይ መፍትሄው ቀላል ሆኖ ሳለ በየአካባቢያችን የፈጠረው ቀውስ ቀላል አይደለም፡፡ የመጀመሪያው መፍትሄ ስለችግሩ ተዓማኒ እውቀት ማግኘት ነውና ይህንን መረጃ ለተከታዮቻችን እናደርሳለን፡፡
#ሾተላይ #ምንድን #ነው?
ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።
ይህ ለምን ይሆናል?
የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል
(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡
#አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና
#አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል። የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።
ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።
በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል። የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?
👉ሕክምናው
#1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።
#2. በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።
#3. በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።
#እንዴት #እንከላከለው?
👉ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።
👉 የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።
👉 እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።
👉እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት። ሼር በማድረግ ለወዳጆዎ ያጋሩ
💚መልካም 💛ቀን ❤️ለሁላችን