መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#መንጋጋ #ቆልፍ ወይም #ቲታነስ

የመንጋጋ ቆልፍ ወይም የቲታነስ በሽታ የሚመጣው
👉በአፈር
👉በአቧራ ብናኝ
👉በፍግና
👉በብረት ዝገቶች ላይ ከሚገኙ ቆሻሻዎች
ውስጥ ከሚኖር ክሎስትሪዲየም ቲታኒ(Clostridium tetani)
ከተባለ ባክቴሪያ ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ ከሌሎች
ባክቴሪያዎች በተለየ መልኩ ከሰው ልጅ ውጪ መኖሪያ አለው።ባክቴሪያው ለረጅም ጊዜ በአፈር በከብቶች አዛባ ውስጥ የመኖር ባህሪይ አለው። ይህ በሽታ የሚያጠቃው የነርቭ ስርዓትን ሲሆን ሲጠና የጡንቻ አካላት ከፍቃዳችን ውጪ
እንዲግተረተሩ ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ የሚጀምረው ከመንጋጋ ሲሆን #መንጋጋ #ቆልፍ የሚለው ስያሜም የመጣው ከዚሁ ነው፤
በመንጋጋችን አካባቢ ያለው ጡንቻችን በሽታው ሲጀምረን ዝግትግት የማለት ባህሪይ አለው። በመቀጠልም ወደሌላው
የሰውነታችን ክፍል ይስፋፋል ከሰውነት መግተርተር ውጪ
👉ላብ
👉ራስምታት
👉ማንኛውንም ነገር ለመዋጥ መቸገር
👉ከፍተኛ የደም ግፊትና የልብ ምት የሚታዩ ምልክቶች ናቸው ምልክቶች
መታየት የሚጀምሩት በባክቴሪያው ከተለከፍን ከ3-21 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡

#በሽታው #እንዴት #ይይዘናል ?

ይህ ባክቴሪያ ወደ ሰውነታችን የሚገባበት መንገድ በቁስሎች አማካኝነት ባክቴሪያውን የተሸከሙ የቆሸሹ
👉ስንጥሮች
👉ምስማሮች
👉 የተለያዩ ብረቶች
👉መርፌዎችና ሌሎች ቁሶች
ሲወጉን ሊሆን ይችላል እነኝህ ባክቴሪያዎች በጡንቻ ስርዓት ላይ ጣልቃ የሚገባ መርዝ ይለቃሉ ወይም ያመርታሉ በሽታው ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ አይደለም፡፡
#ሕክምናው #ምንድነው ?
ዋነኛ ሕክምናው የቲታነስ መድኀን( tetanus toxoid) ክትባት ሲሆን በመርፌ የሚሰጥ ነው፤ የክትባቱ ብርታት እስከ አስር አመት ሊቆይ የሚችል ነው እንዲሁም በባክቴሪያው ተለክፈናል
የሚል ጥርጣሬ ሲኖር የቲታነስ ኢሚዩኖግሎቡሊን(tetanus
antibodies or tetanus antitoxin) በመርፌ መልክ ሊሰጥ ይችላል ይህ ሕክምና የሚሰጠው የሕክምና ባለሙያን በማማከር መሆን አለበት በሽታው ስር ከሰደደ ለሕክምና አስቸጋሪና ውስብስብ ነው ሕክምናውን በጊዜ ካላገኘም ገዳይ ነው፡፡
#ማስጠንቀቂያ ❗️
ይህ ባክቴሪያ ህይወት በሌለው ነገር ውስጥ ሕይወት አልባ ሆኖ በመጠለል ወደ ሰውነት ሲገባ ደግሞ ህይወት ስለሚዘራ
ለማጥፋት ከባድ ነው በየትም ቦታ የመኖር ባህሪም ስላለውም በጣም አስቸጋሪ ነው በመሆኑም አንድ ሰው በመንጋጋ ቆልፍ
በሽታ ከተያዘ በኋላ የማዳን እድሉ አስቸጋሪ ስለሚሆን ዋናው ስራ መከላከልን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት ለመከላከልም ህፃናት ከአንድ ዓመት በታች እያሉ ሙሉ ለሙሉ ማስከተብ
ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቀድመው ቢከተቡ እንዲሁም ነብሰጡሮች ንፅህናውን በጠበቀ መልኩ በሆስፒታል
ቢወልዱ የሚመከር ነው ክትባቱን መውሰድ ከስጋት ያድናል
👉 ማንኛውንም በቁስ መወጋት የተፈጠረን ቁስለት በተለይ በስራ ላይ በቆሸሹ ቁሶች የሚያጋጥሙንን እንደቀላል ማየት
በኋላ ሕይወትን ሊያሳጣ ስለሚችል ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ወደ ሕክምና በፍጥነት መሄድ ያስፈልጋል።

#መልካም #ጤና