መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#እጃችንን_የመታጠብ_ጥቅም_እና_አስፈላጊነት

👉እጃችንን በሚገባ መታጠብ ራሳችንን ከተለያዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን እንደንከላከል እና ለሌሎችም ሰዎች እንዳናስተላለፍ ይረዳል፡፡
እጃችን ንፁህ ቢመስልም እንኳን በዓይናችን ልናያቸው የማንችለውን ዓይነት ጥቃቅን በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ሊይዝ ይችላል፡፡

#እጃችንን_የመታጠብ_ጥቅሞች

👉ከተቅማጥ አምጪ ተህዋስያንና ከሌሎች አንጅት ውስጥ በሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችን የመያዝ እድላችንን ይቀንሳል፡፡
በዓለማችን ከ5 ዓመት እድሜ በታች ያሉ ሕፃናት ሞት ምክንያት የሆነውን ተቅማጥ ሕመም እጅን በሚገባ በመታጠብ መከላከል ይቻላል፡፡
👉ዓይናችንን በምንነካበት ጊዜ ለተለያዩ ባክቴሪያዎች እና ቫይረሶች ስለምንጋለጥ ዓይናችን #ማሳከክ #መቅላት #ብርሃን #ለማየት መቸገር እና ያልተለመድ ፈሳሽ ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለዚህ እጃችንን መታጠብ በኢንፌክሽን ከመያዝ ይከላከልልናል፡፡
👉በመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን የመያዝ ዕድልን ይቀንሳል፡፡ እጅ መታጠብን የሚያዘወትሩ ከሆነ እራስዎን ከጉንፋን እና ከተለያየ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን መከላከል ይችላሉ፡፡

#እጅዎን_መቼ_መታጠብ_እንደሚገባዎ ያውቃሉ?

👉 ምግብ ከማብሰልዎ ወይንም ከማዘጋጀትዎ በፊት
👉ምግብ ከመመገብዎ በፊት
👉ሕመምተኛ ከማስታመምዎ በፊት እና በኋላ
👉ማንኛውንም ዓይነት ቁስል ካፀዱ በኋላ
👉መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ
👉የልጅዎን ዳይፐር (የሽንት ጨርቅ) ከቀየሩ ወይንም መፀዳጃ ቤት የተጠቀመ ልጅዎን ካፀዱ በኋላ
👉ካሳነጠስዎ፣ካሳልዎት እና አፍንጫዎን ካፀዱ በኋላ
👉የቤት ውስጥ እንስሳትን ከነኩ፣ከመገቡ ወይን ካፀዱ በኋላ
👉ቆሻሻን ከቤትዎ ወይንም ከማንኛውንም ቦታ ካስወገዱ በኋላ
እጅን መታጠብ በጣም ቀላል የሚመስል ድርጊት ቢሆንም አብዛኞቻችን ግን በትክክለኛው ሁኔታ አንተገብረውም፡፡

#እጅዎን_እንዴት_ይታጠባሉ ?

👉በመጀመሪያ እጅዎ ላይ የሚገኝ ማንኛውንም ጌጣጌጥ ያውልቁ
👉እጅዎን በንፁህ ውሃያርጥቡ
👉ሳሙና እጅዎን በሚገባ ይቀቡ
👉በፊትና ጀርባ እንዲሁም በጣቶችዎ መሃል እና የጥፍርዎን ዉስጥ በደንብ አድርገው ይሹት
👉በንፁህ ውሃ እጅዎን ያለቅልቁ
👉በንፁህ ፎጣ ወይንም ጨርቅ እጅዎን ያድርቁ
👉ውኃውን ለመዝጋት እጅዎን ያደረቁበትን ፎጣ ይጠቀሙ
👉እጅዎ የሚደርቅብዎት ከሆነ ማለስለሻ ቅባት ይጠቀሙ

መረጃዉ ከተመቾት 👍 መጫኖን አይርሱ

#መልካም #ጤና
#ሜኔንጃይትስ (ማጅራት ገትር)

#የማጅራት_ገትር_ህመም ወይንም በህክምናው አጠራር ሜኔንጃይትስ የምንለው አንጎልን እና ህብረሰረሰርን ሸፍኖ የሚገኝ የሰውነታችን ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው።
የማጅራት ገትር በሽታ #በቫይረስ #በባክቴሪያ ወይንም #በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
ይህ ህመም በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ለከፍተኛ ጉዳት ከዚያም ባለፈ ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ የሚችል ነው። ስለዚህም አንድ ሰው የማጅራት ገትር እንደያዘው ከጠረጠረ በአፋጣኝ ወደ ሀኪም በመሄድ ለከፋ ኣደጋ ከመዳረግ ይድናል።

ከዚህ በታች ስለ ማጅራት ገትር ምልክቶች፣ተጋላጥጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች እና መከላከያ መንገዶችን እናያለን

#የማጅራት_ገትር_ህመም_ምልክቶች_ምንድን ናቸው?

በመጀመሪያ የማጅራት ገትር ህመም የጉንፋን ህመም ዐይነት ሊሆን ይችላል ከቀናት በኃላ ግን የማጅራት ገትር ህመም መገለጫ የሆኑ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ።

👉ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
👉የአንገት መሸምቀቅ
👉ከፍተኛ የሆነ እና ከሌላው ጊዜ የላቀ የራስምታት ስሜት
👉ማቅለሽለሽና ትውከት (ማስመለስ)
👉ግራ መጋባት እና ትኩረት ማጣት
👉ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት መሰማት
👉ብርሃን ኣለመፈለግ
👉የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ማጣት
👉የቆዳ ላይ ሽፍታ( ኣንዳንዴ ሊከሰት የሚችል) ናቸው።

#ለማጅራት_ገትር_ህመም_ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ_ሁኔታዎች_ምንድን ናቸው?

👉ክትባት አለመከትብ
ወላጆች ልጆቻቸውን የማስከተብ ሃላፊነትን የመወጣት ግዴታ ኣለባቸው። ያልተከተቡ ከሆነ በዚህ በሽታ የመያዝ እድልዎ ይጨምራል።
👉እድሜ
በአብዛኛው በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ማጅራት ገትር እድሜአቸው ከ5 ኣመት በታች የሆኑትን ሲያጠቃ በባክቴርያ ምክንያት የሚከሰተው ደግሞ ከ20 አመት እድሜ በታች ባሉት ይስተዋላል።
👉በሽታን የመከላከል አቅም መዳከም
👉በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተጠቁ
👉የስኳር ህመም ያለባቸው
👉የአልኮል መጠጥን አብዝተው የሚያዘወትሩ እና በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድሃኒቶችን የሚውስዱ ሰዎች በማጅራት ገትር የመጠቃት እድላችው ከፍተኛ ነው።
👉እርግዝና
በእርግዝና ወቅት ለተለያዪ ለኢንፌክሽን ዓይነቶች የመጋለጥ ሁኔታ ስለሚጨምር በማጅራት ገትርም ሊከሰት ይችላል።
👉የአኗኗር ሁኔታ
ሰዎች በብዛትና በተጨናነቀ ሁኔታ ሊተላለፍ ይችላል።

#ሀኪምዎን_ማማከር_የሚገባዎ_መቼ_ነው?

የማጅራት ገትር ህመም ካልታከመ ኣደገኛ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወትን ሊይሳጣ ስለሚቸል እንዲሁም ደግሞ ዘግይቶ ህክምና የሚጅመር ከሆነ የአንጎል ችግርን ስለሚያስከትል ከታች የተገለጹት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሀኪም በአፋጣኝ ሄዶ መታየት ይግባዋል።
በማጅራት ገትር ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች በጣም የከፉ ሊሆኑ ይችላሉ።
አንድ ሰው ሳይታከም ከበሽታው ጋር የሚቆይ ከሆነ የሚጥል በሽታ እና ሌሎች ከአንጎል ጋር የተገናኙ ጉዳቶች ይደርስበታል።
እነዚህም፤
👉የመስማት ችሎታን ማጣት
👉የማስታዎስ ችግር
👉የመማር ብቃትን ማጣት
👉ሚዛን ጠብቆ የመቆም እና የመራመድ ችግር
👉የኩላሊት ህመም ናቸው።
ተገቢውን ህክምና በአፋጣኝ የሚያገኝ ታካሚ ግን ከህመሙ በሚገባ ማገገም ይችላል።

#የማጅራት_ገትር_ህመምን_እንዴት_መከላከል እንችላለን?
በአብዛኛው ማጅራት ገትርን የሚያመጡ ባክቴርያና ቫይረሶች #በማስነጠስ #በሳል እና የተለያዩ የመገልገያ ቁሳቁሶችን በመጋራት የሚተላለፉ ስለሆኑ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በመተግበር መከላከል ተገቢ ነው።
👉እጅዎን በሚገባ መታጠብ
እጅዎን በሚገባ በሳሙና መታጠብ የተለያዩ ጀርሞችን እንዲከላከሉ ስለሚረዳም ሙሉ ቤተሰብዎን በተለይ ደግሞ ከምግብ በፊትና በኋላ መጸዳጃ ከተጠቀሙ በኃላ በሚገባ መታጠብ እንደሚገባ ማስተማር ተገቢ ነው።
👉የግል ጽዳትዎን መጠበቅ
የመመገቢያና የመዋቢያ የመሳሰሉትን እንዲሁም የጥርስ ብሩሽ ከማንም ሰው ጋር በጋራ አለመጠቀም
👉ጤናዎን ይጠብቁ
በቂ እረፍት እና እንቅስቃሴ እንዲሁም ጤናማ አመጋገብ በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል።
👉በሚያስልዎ እና በሚይስነጥስዎ ጊዜ አፍንጫዎንና አፍዎን ሸፍነው መሆን ይኖርብዎታል።
👉ክትባት
ልጅዎችዎ ክትባታቸውን በሙሉ ማጠናቀቃቸውን በሀላፊነት መከታተል አስፈላጊ ነው። በዘመቻ የሚካሄድ ክትባት በሚሰጥ ጊዜም መከተብ ተገቢ መሆኑን በመረዳት ተሳታፊ መሆን ይኖርቦታል።

#መልካም_ጤና
#ካታራክት

#ካታራክት የምንለው የህመም ስሜት የሌለውና ሌንስ የምንለውን የአይናችንን ክፍል ጋርዶ የሚቆይ እና ብርሃን ወደ ሬቲና እንዳይገባ የሚከላከል ግርዶሽ የሚፈጠርበት ሁኔታ ነው።

#ካታራክት_እንዴት_ሊከሰት_ይችላል?

👉የእድሜ መጨመር እና
👉ለፀሀይ ብርሃን መጋለጥ
ካታራክት እንዲከሰት ምክንያቶች በመሆን ይጠቀሳሉ።
#ካታራክት በአይን ላይ በሚደርስ ጉዳት በተለያዩ የአይን ህመሞች ምክንያት ሊከሰት ይችላል። እነዚህም እንደ #ስኳር_ህመም እና የተለያዪ የመድሀኒት አይነቶች ናቸው።
አንዳንዴም ህፃናት ከካታራክት ጋር ሊወለዱም ይችላሉ።

#የካታራክት_ምልክቶች_ምንድን_ናቸው?

👉ካታራክት የእይታ ችግርን ያስከትላል። #ብዥታ #መደብዘዝ ወይም #በዳመና #የተጋረድ #የሚመስል #እይታ
👉የፀሀይ ወይንም የመብራት ብርሀን በሚያዪ ጊዜ በጨረር መብዛት ምክንያት በጨለማ መኪና ለማሽከርከር መቸገር።
👉በተደጋጋሚ የሚታዘዝልዎን መነፅር መቀየር የሚያስፈልግዎ ሲሆን።
👉 በአንደኛው አይናችን ብዥታ የመኖር ሁኔታ
👉 ካታራክት ሙሉ ለሙሉ እይታን እንዳይኖረን የሚያደርገው እጅግ ዝግመታዊ በሆነ ሁኔታ ሲሆን አንዳንዴም ምንም አይነት የእይታን ችግር ላይፈጥርም ይችላል።

#ካታራክት_ህመም_እንዴት_ሊታወቅ_ይችላል?

ሀኪምዎ አይንዎን በመመልከትና የተለያዪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ካስፈለገም ሌሎች እይታን የሚከለክሉ ህመሞች አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ ምርመራዎችን በማድረግ ለማወቅ ይቻላል።

#ካታራክትን_እንዴት_ማከም_ይቻላል?

👉የቀዶ ጥገና ካታራክትን የማከሚያ መንገድ ሲሆን ይህም የሚደረገው በካታራክቱ ምክንያት የእለት ተእለት ኑሮአቸውን ለመግፋት የሚከብድ ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው።
👉ካታራክት ህመምን በህክምና ባለሞያ የታዘዘ መነፅር በማድረግ የእይታ ችግሩን በመጠኑም መቀነስ የሚቻል ቢሆንም ሊያሻሻል ይችላል።
👉ከካታራክት ጋር የሚወለዱ ህፃናትና በአይን ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት የሚከሰቱ የካታራክት ችግሮች የቆዳ ጥገና ህክምና ያስፈልጋቸዋል።

#ካታራክትን_እንዴት_መከላከል_ይቻላል?

👉ካታራክትን መከላከል የሚቻልበት መንገድ ባይኖርም ካታራክት እድገቱን ግን በዝግታ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል ይህም
👉ሲጋራን ማጤስ በማቆም
👉የፀሃይ መከላከያ መነፅር ወይንም ኮፍያ በማድረግ
👉ጤናማ አመጋገብ እና
👉የስኳር ህመምን ካለ መቆጣጠር ተገቢ ነው።

#መልካም_ጤና
#ኒውሮብፋይብሮማቶሲስ

(Neurofibromatosis) በዘረመል መዛባት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን የነርቭ ህዋሳቶች እድገት ላይ ተፅእኖ አለዉ ይሄም የሰዉነታችን ቆዳ እንዲሁም አይናችን አካባቢ እና የተለያዩ የሰዉነታችን አካላት ላይ ባሉ የነርቭ ጫፎች ላይ የሚወጣ እባጭ ነዉ።

#ሁለት_አይነት_ኒውሮብፋይብሮማቶሲስ_አለ

#እነዚህም
👉Neurofibromatosis 1 :- ሲሆን ምልክቱም በተለይ በቆዳ ላይ የሚወጡ አነስ ያሉ ቡናማ እባጮች እንዲሁም ብብት አካባቢና ንፊፊት አካባቢ የሚወጡ በመጠን ቀለል ያሉ ብዛት ያላቸው እባጮች ናቸው
👉Neurofibromatosis 2 :-ሲሆን በቆዳ ላይ ተለቅ ያሉ እንደ ጆሮ የተነጠለጠሉ እባጮች እና የጡንቻዎች መላላት ከዚህም በተጨማሪ የአይን ሞራን ጨምሮ የመስማት ችግርንም ያስከትላል

#ህክምናዉ

እስካሁን ምንም አይነት መከላከያም ሆነ ህክምና አለተገኘለትም ነገር ግን አንዳንድ ጊዚያዊ የሆኑ ህክምና ዘዴ አለ እነዚህም
በቀዶ ህክምና እባጮቹን ማስወገድ በመጀመርያ ግን እባጮቹ በሚወጡበት ግዜ ሌላ ችግር እንደማያመጡ መታወቅ አለበት
በህፃናት ላይ ይህ በሽታ ሲከሰት ቶሎ ማወቅና በየአመቱ ያለውን ለዉጥ መከታተል ህክምናዉን ቀለል ያረገዋል

ለመረጃዉ 👍 አይንፈጉን

#መልካም_ጤና
#ሪህ (Gout Arthritis)

#የሪህ ሕመም የሚከሰተዉ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል የሚገኘው ፕሮቲንን በዉስጣቸዉ ከያዙ ምግቦች ነው፡፡ የሪህ ችግር አንድ ጊዜ ከጀመረ በኋላ የመከላከያ ዕርምጃዎችን ካልወሰድን የመመላለስ ባህርይም አለዉ፡፡
የአጥንት መገጣጠሚያዎች በተለይም በእግራችን #የአውራ_ጣት #በቁርጭምጭሚት #በጉልበት #በእጃችን #የክንድ እና #የእጅ መገጣጠሚያዎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል፡፡

#የሪህ_ህመም_ስሜት_ቀስቃሽ_ሁኔታዎች

👉 ዉስጣዊ የሆኑ ህመሞች
👉 አልኮል መጠጦችን ማዘዉተር
👉ፕሮቲን የበዛባቸው የምግብ ዓይነቶችን መመገብ (ስጋ፣ሽሮ የመሳሰሉት)
👉 የሰዉነት ቁስለት
👉 ድካም
👉ጭንቀት
👉በሃኪም የታዘዘን የሪህ መድኃኒት ማቆም ናቸዉ፡፡

#የሪህ_ህመም_ምልክቶች_ምንድን_ናቸዉ ?

👉 ከአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚኖር ኃይለኛ የሕመም ስሜት፡፡
👉 የመገጣጠሚዎች ማበጥ፣ መቅላት እና የሙቀት መጠን መጨመር
👉ትኩሳት መኖር
👉ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ

#ሪህ_ተደጋግሞ_እንዳይመጣ_ምን_ማድረግ #ይገባል ?

👉ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች በተለይም ቀይ የበሬ ሥጋ፣አሳ፣እንቁላል፣የመሳሰሉት ምግቦች መቀነስ ወይንም ለጊዜው ማስወገድ፣
👉ውሃ በብዛት መውሰድ፣
👉የአልኮል መጠጦችን አለመጠጣት፣
ከላይ የተጠቀሱት የሕመም ስሜቶች ሲሰማዎትም ሐኪምዎን ማማከር የኖርቦታል፡፡

#መልካም_ጤና
#መጥፎ_የአፍጠረንን_ለመከላከል_ወይንም #ለመቀነስ_ማድረግ_ያለብዎትን_ያውቃሉ ?

👉የአፍዎን ንጽህና በሚገባ ይጠብቁ፡- ጥርስዎን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት እንዳለብዎ ይወቁ ከተቻለ ከምሳ በኋላም ለማጽዳት የጥርስ ብሩሽና የጥርስ ሳሙና በቦርሳዎ በመያዝ ጥርስዎን ያፅዱ፡፡
👉 ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ፡- ውሃን መጠጣት በአፍ ውስጥ እርጥበትን ሰለሚፈጥር በብዛት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ ከስኳር ነፃ ሆኑ ማስቲካዎችና ከረሜላዎች መውሰድ በአፍ ውስጥ (Saliva) ምራቅ እንዲመነጭ በማድረግ በአፍ ውስጥ የቀሩ ምግብና ባክቴሪያዎችን እንዲያጥብ ያደርጋል፡፡
👉ሲጋራን ማጤስ ማቆም፡- ሲራጋ ማጤስ ለመጥፎ የአፍ ጠረን መኖር ምክንያት ስለሚሆን
ማቆም ይኖርብዎታል፡፡
👉የሚወስዱትን ምግብ ወይንም መድኃኒት መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያመጣብዎ ካወቁ ወደጥርስ ሐኪምዎ በመሄድ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡
👉የጥርስ ሐኪምዎን በዓመት አንዴ እንዲያይዎት ማድረግ እንዲሁም በሕክምና የታገዘ ባለሙያዊ የጥርስ ዕጥበት በዓመት አንድ ጊዜ ማድረግ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል

#መልካም_ጤና
#የጀርባ_ሕመምዎን_ለማስታገስ_የሚረዱ #ጠቃሚ_ምክሮች

👉 #አቋምዎን_ያስተካክሉ

የጀርባ ሕመም የሚያሰቃይዎት ከሆነ በመጀመሪያ አቀማመጥዎን እና ከባድ ዕቃን የሚይዙበትን ሁኔታ ያስተካክሉ፡፡ ለብዙ ሰዓት ተቀምጠው የሚሠሩ ከሆነ ለወገብዎ መደገፊያ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ ከመቀመጫዎ ሲነሱ ቀጥ ብለው መነሳት እና ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በሚያነሱበት ጊዜ ከጉልበትዎ በርከክ ብለው ጀርባዎን ቀጥ በማድረግ መሆን አለበት፡፡
የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚጠቀሙበትን ሰዓት ይቀንሱ
በሥራም ሆነ በማኅበራዊ ጉዳይ ምክንያት ለረጅም ሰዓታት ከኮምፒዩተሮችና ሌሎች የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ አጎንብሰን እና ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን የምንጠቀምባቸው ከሆነ የጀርባ ሕመም እና የራስ ምታትን ያስከትላሉ፡፡

👉 #መደበኛ_የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴን #ያድርጉ

የጀርባ ሕመምን ቀላል በሚባል የአካል ማፍታታት እና አንገትን እና ወገብን በማንቀሳቀስ መከላከል ይችላሉ፡፡

👉 #ጭንቀትን_ይቀንሱ

ጭንቀት ለብዙ ዓይነት ሕመሞች እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን ከጀርባ ሕመም ጋርም ተያያዥነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም ለራስዎ ጊዜ በመስጠት እና በመዝናናት ጭንቀትዎን ይቀንሱ፡፡

👉 #የሰውነት_ክብደትዎን_ይቀንሱ

የሰውነትዎ ክብደት መጨመር በተለይም በወገብ አካባቢ ስብ ከተከማቸ የጀርባ ጡንቻዎችን ስለሚጎዳ የጀርባ ሕመም ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ አመጋገብዎን ማስተካከል እና ክብደትዎን መቀነስ የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_ዕረፍት_ያድርጉ

በቂ እረፍት ማድረግ ለሙሉ ጤናማነት ጠቃሚ ነው፡፡ እንቅልፍ በሚተኙ ጊዜ በጎንዎ በኩል መተኛት የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_የፀሐይ_ብርሃን_ያግኙ

የፀሐይ ብርሃን ቢያንስ በቀን ለ10 ደቂቃ መውሰድ ለአጥንትዎ ጠንካራነት እጅግ ጠቃሚ እና ለጀርባ ሕመምዎ አንደኛው መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡

👉 #ሲጋራ_ማጤስን_ያቁሙ

ሲጋራ ማጤስ ወደ ታችኛው የጀርባችን አጥንቶች የሚሄደውን የደም ዝውውር ስለሚቀንስ ለጀርባ ሕመም ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም ሲጋራ ማጤስዎን እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

#መልካም_ጤና
#የማይግሬን_ራስ ምታት

#የማይግሬን ምልክቶች የምንላቸው

👉ከፍተኛ ራስ ምታት ከደቂቃዎች እስከ ሰአታት የሚቆይ ብዙን ጊዜ በአንድ በኩል ከፍሎ የሚሠማ ህመም በተጨማሪም
👉የማቅለሽለሽ
👉የድብርት እና
👉ማስመለስ ከከባድ ራስምታት ጋር ተያይዞ ሊኖሩ ይችላሉ ።

#የማይግሬን_ራስ_ምታትን_ቀስቃሽ_የሆኑ #ምክንያቶች_በጥቂቱ

👉ምግብ

የቆዩ ምግቦች፤ ጨው የበዛባቸው ምግቦች እና የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ለማይግሬን ራስ ምታት መቀስቀስ ምክንያት ናቸው፡፡ ምግብ ሳይመገቡ መቆየትም ማይግሬንን ሊያስነሳ ይችላል፡፡

👉መጠጥ

የአልኮል መጠጥ መውሰድ ወይንም ካፌን የበዛባቸውን መጠጦችን መውሰድ የራስ ምታትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡

👉ምግብ ማጣፈጪያዎች

በታሸጉ ምግቦች ውስጥ የሚጨመሩ ምግብ ማጣፈጫዎች እና ምግቦች ሳይበላሹ እንዲቆዩ የሚያደርጉ ኬሚካሎች የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳሉ፡፡

👉ጭንቀት

በግል ሕይወት ወይንም በሥራ ምክንያት የሚፈጠር ጭንቀት የራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡

👉እንቅልፍ ላይ የሚመጡ ለውጦች

በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ወይንም ከበቂ በላይ እንቅልፍ መተኛት የማይግሬን ራስ ምታትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡

👉የአካባቢ ለውጥ

በአካባቢያችን በሚፈጠር የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የማይግሬን ራስ ምታት ሊነሳ ይችላል፡፡

👉ከፍተኛ የሆነ ብርሃን፤ የሚጮህ

ድምፅ፤ያልተለመደ ሽታ (የሽቶ፤የቤት ቀለም) ሲጋራ እና የመሳሰሉት የማይግሬን ራስ ምታትን የቅሰቅሳሉ፡፡

#ህክምናው

ህመሙን በቶሎ ማስታገስ እናም ወደፊት እንዳይደጋገም ማድረጉ ላይ ያተኩራል ለዚም የሚወሠዱ የህመም ማስታገሻዎች አሉ ።

በዋናነት መንስዔዎችን እና ቀስቃሽ ነገሮችን በመለየት ጥንቃቄ ማድረግ ተመራጭ ህክምና ነው ።

#መልካም_ጤና
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የጆሮ_ማሳከክ_ምክንያቶች_በጥቂቱ

ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት ሲጎዳ ከሚከሰቱ ምልክቶች አንዱ የማሳአክ ስሜት ነው።
የጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችን ማወቅ በቶሎ መፍሄዎቻቸውን እንድንፈልግ ይረዳናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችም ናቸው።
👉 የጆሮ ኩክ መከማቸት
የጆሮ ኩክ (Earwax) የምንለው ሰውነታችን የሞቱ ሴሎችንና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳበት መንገድ ሲሆን በብዛት በሚገኝበት ወቅት ግን የማሳከክ ስሜትን ይፈጥራል።
ጆሮን ለማጽዳት መሞከር ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ። ወደ ሀኪም በመሄድ ከታዪና ትክክለኛ ምክንያቱ የኩክ መጠራቀም ሆኖ ከተገኘ በጠብታ መድሀኒት ወይንም በህክምና ባለሞያ እርዳታ እንዲወጣ ይደረጋል።
👉ኢንፌክሽን
የጆሮ ማሳከክ አንዳንዴ ደግሞ የ ኢንፌክሽን መኖር ምልክት ይሆናል። ጉንፋንን ወይንም ቶንሲልን የሚያስከትሉ ባክቴርያና ቫይረስ በደም ተዘዋውረው ወደ ጆሮ በመሄድ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋሉ።
ውሀ ዋና የሚዋኙ ሰዎችም ውሃው በጆሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እና ተፈጥሮአዊ የሆነውን ጀርሞችን የመከላከል አቅም በእርጥበት ምክንያት እንዲያጣ ስለሚያድርግ ሌላው የ ኢንፌክሽን መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል።
የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ ወደ ሀኪም በመሄድ ጸረ ባክቴርያ የሆኑ የጆሮ መድሀኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው።
👉የቆዳ አለርጂ
በጆሮዎ ውጨኛው ክፍል የሚገኘው ቆዳዎ በአለርጂ ምክንያት የማሳከክ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል።
የመዋቢያ ቅባቶች ወይንም ቁሳቁሶች አለርጂን ሊይስከትሉ ይችላሉ። የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ አለርጂው የተከሰተበትን ምክንያት ተከታትሎ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛም መጠቀም ማቆም ተገቢ ነው።
👉ጆሮን በሹል እና ጎጂ ሊሆኑ በሚችሉ እንደ ጸጉር ሻጤ፣ አግራፍ፣ የክብሪት እንጨት በመሳሰሉት ማጽዳት የጆሮ ቆዳን ለመሰንጠቅ ስለሚችል ለኢንፌክሽን ይዳርጋል ከዚህም ባለፈ የጆሮን ውስጣዊ ክፍል በመጉዳት የመስማት ችሎታችንን ሊያሳጣን ይችላል።

#መልካም_ጤና
💊💊 💊💊
ውድ #የመሀደረ_ጤና ቻናል ተከታታዮች እባካችሁ ቻናሉን #MUTE አድርጋችሁ የምትጠቀሙ #UNMUTE አድርጋችሁ ተጠቀሙልን እባካችሁ🙏 የኛ ክፍያችን ጤናን በተመለከተ የምንለቀዉ መረጃ ሁላችሁም ጋር ደርሶ ትንሽ ስለ ጤናችን ያለንን መረጃ ከፍ ለማድረግ ነው ከናተም ለሚደርሰን ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው እና አባካችሁ #UNMUTE አድርጋችሁ ተጠቀሙ እናመሰግናለን

ስለቻናሉ ያሎትን አስተያየት በ @Teenaa_bot
አድርሱን

ሀሳቡን የደገፋችሁ አብሮነታችሁን 👍👍 በዚህ
አሳዩን

#መልካም_ጤና
#ታይፈስ (Typhus)

#ታይፈስ ሪኬትስያ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት አማካኝነት የሚመጣ የሕመም ዓይነት ሲሆን፣ የታይፈስ ዓይነቶች በዋነኛ ደረጃ
#በሁለት #ይከፈላሉ
ነገር ግን ሌሎች የታይፈስ አይነቶችም ይገኛሉ፡፡
👉Epidemic Typhus
በወረርሽኝ መልክ የሚመጣ ታይፈስ ሲሆን ይህ የታይፈስ ዓይነት በሪኬትሲያ ፕሮዋዚክ በሚባል ባክቴሪያ ዓይነት የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያውን አስታላላፊዎች ደግሞ በሰውነት ላይ በሚገኙ ቅማሎች ናቸው፡፡
👉Murine Typhus (ሙሪን ታይፈስ) የምንለው ሁለተኛው የታይፈስ ዓይነት ሲሆን ይህ ደግሞ ሬኬትሲያ ታይፈስ በሚባለው ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ነው የባክቴሪያው አስተላላፊዎች በአይጦች ላይ የሚገኝ ቁንጫ ናቸው
#በወረርሽኝ_መልክ_የሚመጣ_የታይፈስ #ሕመም_(Epidemic Typhus)_ምልክቶቹ
👉ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
👉 የመገጣጠሚያ ሕመም
👉የጀርባ ሕመም ስሜት
👉 የደም ግፊት መጠን መቀነስ
👉የሰውነት ላይ ሽፍታ
👉 ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት
👉 ከፍተኛ የሆነ የጡንቻ ሕመም
#ሙሪን_ታይፈስ_(Murine Typhus)
#ምልክቶቹ
👉እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
👉 የሆድ ሕመም ስሜት
👉 የጀርባ ሕመም ስሜት
👉 ደረቅ ሳል
👉 ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት ስሜት
👉የሚገጣጠሚያ ሕመም ስሜት
👉የጡንቻ ሕመም
👉ማስመለስ
👉በሰውነት ላይ የሚወጣ ሽፍታ
👉ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ፡፡
#ለታይፈስ_ሕመም_ተጋላጭ_የሚያደርጉ #ሁኔታዎች
👉 በተጨናናቀ እና ሰው በበዛበት አካባቢ መኖር
👉 ከከተማ/ከአገር የወጡ ከሆነ
👉 የታይፈስ ወረርሽኝ በመኖሪያ አካባቢዎ የመጣ ከሆነ
#የታይፈስ_ሕመም_ሊያስከትል_ከሚችላቸዉ #ሌሎች ሕመሞች
👉የጉበት ሕመም (ኢንፌክሽን)
👉 የአንጀት ውስጥ መድማት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
#የታይፈስ_ሕመምን_ለመከላከል_መደረግ #ያለባቸው_ጥንቃቄዎች
👉የግል ንጽሕናን በሚገባ መጠበቅ
👉 በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ የአይጥ ዝርያዎችን ማጥፋት
👉የታይፈስ ሕመም ወረርሽኝ ያላባቸው አካባቢ አለመሄድ ናቸው፡፡
የታይፈስ ሕመምን በምልክቶች ብቻ መለየት ከባድ የሚሆን ሲሆን ይህም ከሌሎች ሕመሞች ጋር ተመሳሳይ ምልክቶች ስለሚያሳይ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲሰማዎ ወደ ሐኪም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

#መልካም_ጤና