መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የአፍ #መድረቅ ( Xerostomia)

#የአፍ #መድረቅ #ችግሮች #ምክንያቶችና #መፍትሄዎቻችው

#የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።
ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚራዳ ሁኔታን ያመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናደርግና ለምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኤንዛየምስ የማመንጨት ተግባርን ያከናውናል።
የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊያቃውስ ይችላል።

#የአፍ #መድረቅ #ምልክቶች #ምንድን ናቸው?

👉አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን
👉መጥፎ የአፍ ጠረን
👉ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር
👉የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት
👉የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።

#የአፍ #መድረቅ #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉የአፍ መድረቅ የሚመጣው ምራቅ አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።
👉 መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንየሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።
👉እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።
👉የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።
👉ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።
👉ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።
👉ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን የመሳስሉ ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
👉ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

#ከአፍ #መድረቅ #ጋር #በተያያዘ #የሚመጡ #ሌሎች #ችግሮች #ምንድን #ናቸው?

👉የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
👉የከንፈር ቁስለት
👉የፈንገስ ኢንፌክሽን
👉የከንፈር መሰነጣጠቅ
👉የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።
አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ መድሀኒት እንዲውስዱ ይደረጋል።

#የአፍ #መድረቅ #እንዲቀንስልን #በቤት #ውስጥ #ልንጠቀማቸው #የምንችላቸው #ነገሮች #ምንድን #ናቸው?

👉ውሀን ይጎንጩ
ውሀን መጎንጨት የዘወትር ልማር ማድረግ፣ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ ለማላመጥ እና ለመዋጥ እንዳይችሉ በውሃ ማወራረድ።
👉በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ
የማንኮራፋት ችግር ካለብዎና ሌሊት አፍዎን ገጥመው መተኛት ካልቻሉ ለማንኮራፋቱ ሀኪምን ያማክሩ።
👉ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካ ወይንም ከረሜላ መጠቀም
👉ከንፈርዎን ቫዝሊን ወይንም የከንፈር ቅባት በመቀባት ያለስለሱ።

እንደተለመደዉ መረጃዉ ከተመቾት ላይክ 👍 ማረጎን አይርሱ

#መልካም #ጤና
#ከልክ #ያለፈ #ላብ (hyperhidrosis,)

ከልክ ያለፈ ላብ ከስፖርት እንቅስቃሴና ከሙቀት ውጭ የሆነ የላብ መብዛት ነው ከእጅ፣ከእግር፣ከብብት እና ፊት አካባቢ በመመንጨት ሙሉ ሰውነትን በላብ እንዲዘፈቅ ያደርጋል።
በዚህ ችግር የሚጠቁ ሰዎች መጠነኛ የሚባል የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለማድረግ እስኪቸገሩ ድረስ በከባድ ላብ ይዘፈቃሉ። ከዚያም ባለፈ ለማህበራዊ ችግሮችና በሰው ፊት ለመሳቀቅ እና መሸማቀቅ ይዳርጋቸዋል።

#መፍትሄዎች

👉ሰውነትዎን በየቀኑ መታጠብ
👉ሰውነትዎን ከታጠቡ በኃላ በሚገባ ማድረቅ
👉እግርዎ አየር እንዲያገኝ ማድረግ ፣ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ካልሲ መጠቀም

#ከፍተኛ #ላብ #ሊያስከትሉ #የሚችሉ

👉የስኳር ህመም
👉የእንቅርት ህሙም
👉ዝቅተኛ የስኳር መጠን
👉የልብ ችግር

#ሀኪምዎን #ማማከር #የሚገባዎት #መቼ #ነዉ

👉የላብ መጠኑ እጅግ በዝቶ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎ ላይ ችግር ካስከተለ
👉ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ የሚያልቦት ከሆነ
👉ያለምክንያት ማታ በላብ የሚዘፈቁ ከሆነ ናቸው።

#መልካም #ጤና