መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ፎሮፎር

#ፎሮፎር እጅግ በጣም የተለመደ የፀጉር ቆዳ ችግር ነው፡፡ በፀጉር ቆዳ ላይ የሚታይ ነጭ የተፋቀ የሞተ ቆዳ ፎሮፎር ሲሆን አልፎ አልፎም የማሳከክ ሁኔታ ሊኖረው ይችላል፡፡
#ፎሮፎርን #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች
👉 ደረቅ ቆዳ፡- በቆዳ መድረቅ ምክንያት የሚመጣ ከፀጉር ቆዳ በተጨማሪ በእጅ እና በእግር ቆዳዎች ላይም ይታያል፡፡
👉 ቅባታማ የቆዳ መቆጣት ፡- የቆዳ መቅላት፣ቅባታማ ቆዳ በነጭ እና ቢጫ ቅርፊት መሳይም ነገርም በፀጉር ቆዳ ላይ ይታያል፡፡ ይህ ዓይነቱ የፎሮፎር ዓይነት በቅንድብ እና በጆሮ ጀርባ ላይም ይገኛል፡፡
👉የፀጉር ንፅሕና ማጣት፡- ፀጉርዎን በመደበኛ ሁኔታ የማይታጠቡ ከሆነ ለፎሮፎር ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
👉ፈንገስ ፡- በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የፎሮፎር ዓይነትም ያለ ሲሆን አንዳንዶች ለቆዳቸው ተስማሚ ያልሆኑ የፀጉር መዋቢያዎችን በመጠቀም ምክንያት ይከሰትባቸዋል፡፡
#ለፎሮፎር #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች
👉ዕድሜ፡-በአብዛኛው በልጆችና በወጣቶች ላይ ይታያል፡፡
👉ፆታ፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ባህርይ አለው፡፡
👉 ተጓዳኝ በሽታዎች መኖር ናቸዉ፡፡
#ፎሮፎርን #ለመከላከል
👉 በመደበኛ ሁኔታ የፀጉር ንፅሕና መጠበቅ
👉ለፀጉርዎ የሚጠቀሙትን መዋቢያዎች መቀነስ
👉ፎሮፎር በአብዛኛው ንፅሕናን በመጠበቅ እና አመጋገብን በማስተከካል የሚድን ሲሆን ችግሩ ለሳምንታት የሚቆይ፣የሚያሳክክ እና በፀረ ፎሮፎር የማይታገስ ከሆነ ወደ ሐኪም በመሄድ ሕክምና ማግኘት ተገቢ ነው፡፡ ሕክምናውንም በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት በመጠቀም ከፎሮፎር ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡

#መልካም #ጤና
#የሳንባ #ምች (Pneumonia)

የሳንባ ምች የምንለው በሳንባ ላይ ሚከሰትን ኢንፌክሽን ነው፡፡
#የሳንባ #ምች #እንዴት #ይከሰታል?
👉በባክቴሪያ
👉በቫይረስ
በሽታን የመከላከል አቅማቸው የደከመ ሰዎች ላይ ደግሞ #በፈንገስ ምክንያትም ይከሰታል
አንድ ሰው አየር በሚያስገባ ጊዜ እነዚህን በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደ ውስጥ ያስገባል ይህም ወደ ሳንባ በመሄድ ኢንፌክሽን ይፈጥራል
#ለሣንባ #ምች #ተጋላጭነት #የሚዳርጉ #ሁኔታዎች
👉ዕድሜ፦ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በታች የሆኑ እና ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ሰዎች
👉በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች
👉በጉንፋን የተጠቁ ሰዎች
👉የአስም ሕመም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች
👉ሲጋራን ማጤስ
👉የአልኮል መጠጥን እጅግ ማዘውተር
#የሳንባ #ምች #ሕመም #ምልክቶች
👉አክታ የተቀላቀለ ሳል
👉ትኩሳት
👉ትንፋሽ ማጠር
👉የራስ ምታት
👉ብርድ ብርድ ማለት
👉የደረት ውጋት በሳል ጊዜ የሚብስ የልብ ትርታ መጨመር
👉ላብ ላብ ማለት
👉የሰውነት ድካም
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

#የሳንባ #ምችን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል?
👉ሲጋራ ማጤስን ማቆም
👉እጅን በሚገባ መታጠብ
የሳንባ ምችን ሕመምተኞች በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችላቸው ሕክምናዎች፤
👉ፈሳሽ በብዛት መውሰድ
👉ዕረፍት ማድርግ
ትኩሳትን ማስታገሻ በመውሰድ መቆጣጠር
በቫይረስ የሚከሰት የሳንባ ምች በአብዛኛውን ጊዜ በጉንፋን ምልክቶች የሚጀምር ሲሆን #ትኩሳት #ደረቅ ሳል #ራስ ምታት#ቁርጥማት እና #የድካም #ስሜትን ያስከትላል ትንፋሽ ማጠር እና አክታ ከአንድ ቀን በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በባክቴሪያ የሚከሰት የሳንባ ምች ከፍተኛ #ትኩሳት #አክታን #የቀላቀለ #ሳል ከፍተኛ #የሰውነት #ማላብ #የልብ ምት መጨመር እና በፍጥነት የሚጨምር የአተነፋፈስ ስርዓት ይኖራቸዋል፡፡
የሣንባ ምች ሕክምና ህመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት፤ እንደ ሕመሙ ክብደት እና ተጨማሪ ሕመም መኖር ሁኔታ ይለያያል፡፡
በሕመሙ የተጠቁ ሰዎች ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ሐኪምን በማማከር ሕክምናውን በመውሰድና በሚገባ በመከታተል ከበሽታው መዳን ይቻላል

#መልካም #ጤና