መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የሽንት #ቧንቧ #ኢንፊክሽን #በሽታ

የሽንት ቧንቧ ኢንፌሽን በሽታ በሽንት ስርአት ውስጥ ያሉ አካሎች በባክቴርያ ሲጠቁ ሲሆን በዚህ ስርአት ውስጥ
👉ኩላሊት
👉ዮሬተር
👉የሽንት ፊኛና
👉ዩሬትራን ይካትታል፡፡
ሴቶች ከወንዶች የበለጠ በዚህ በሽታ ይጠቃሉ፡፡ ይህ በሽታ የሽንት ፊኛን ብቻ የሚያጠቃ ሲሆን ከፍተኛ ህመም አለው፡፡ ወደ ኩላሊት ሲደርስ ደግሞ ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡
ፀረ- ባክቴሪያ መድሀኒቶች በሽታውን ለማጥፋት ፍቱን ናቸው፡፡
👉#የሽንት #ቧንቧ #ኢንፎክሽን #መነሻ!
ሽንት ቤት ከተጠቀምን በኋላ በሶፍት ወይም በሌላ ነገር ስናጠዳ ከፊት ወደ ኋላ እንድናጸዳ /እንድንጠርግ/የሚመከርበት ዋነኛው ምክንያት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው፡፡
👉ዩሬትራ ቱቦ/ቧንቧ ሽንትና ከሽንት ከረጢት ወደ ውጪ ማለትም ከሰውንት ውጭ ማስወገድ ተግባርን ይወጣል፡፡
ይህ ቧንቧ ለፊንጢጣ ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡
በተለይ በሴቶች ትልቁ አንጀታቸው ላይ የሚገኝ ባክቴሪያዎች ለምሳሌ፦ ኢ- ኮላይ (E.coli) ከፊንጢጣ በመነሳት በቀላሉ ዮሬትራ ቧንቧን ወረራ ያደርጉበታል ከዚህም ወደ ሽንት ከረጢት ይጓዛሉ ህክምና ካልተደረገልን በመቀጠል ኩላሊትን ያጠቃል ለዚህም ነው ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በሽንት
ቧንቧ ኢንፊክሽን የሚጠቁት በተጨማሪም ሴቶች አጭር ዩሬትራ ስላለቸው ባክቴሪያ በቀላሉ የሽንት ከረጢት የመድረስ እድል አላቸው፡፡
👉#የሽንት #ቧንቧ #ኢንፊክሽን #ምርመራና #ህክምና!
የሽንት ናሙና በመውሰድ በላብራቶሪ ኢንፊክሽኑ እንዲከሰት ያደረገው ባክቴሪያ የተለያዬ ዓይነት ህክምና ምርመራዎች ይደረጉለታል፡፡
👉የዚህ በሽታ ህክምና ጸረ- ባክቴሪያ መድሀኒቶች ናቸው፡፡ ዋናው ልብ ልንል የሚገባን ጉዳይ እየተሸለን እንኳን ቢሆን የታዘዘልንን መድሀኒቶች ውጠን መጨረስ ግድ ነው።
መድሀኒቱን ከጀመርን በኋላ ምልክቶቹ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይጠፋሉ በድጋሜ ለማስታወስ የታዘዙትን መድሀኒቶች መጨረስ ግዴታም ጭምር ነው፡፡ ይህም ባክቴሪያው ሙሉ ለሙሉ ከሰውነታችን እንዲወገድና መድሀኒቱን ባክቴሪያዎቹ እንዳይለመድ ያደርጋል፡፡
በተደጋጋሚ በዚህ በሽታ የምንጠቃ ከሆነ ሀኪማችን የሚከተሉትን እርምጃዎች ሊወስድ ይችላል፦
👉ለረጅም ግዜ የሚወሰድ የጸረ ባክቴሪያ መድሀኒቶች ወይም በሽታው በሚጀመርበት ጊዜ በአጭር ጊዜ የሚወሰድ መድሀኒቶች እንድንጠቀም ሊታዘዝ ይችላል፡፡
👉በሽታው ከግብረ ስጋ ግንኙነት ጋር የሚያያዝ ከሆነ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በአንድ ጊዜ የሚወሰድ ጸረ - ባክቴሪያ ሊታዘዝልዎ ይችላል፡፡
#መከላከያ #መንገድ!
👉የሽንት ፊኛዎችን ባዶ ማድረግ ወይም ሽንትዎ በመጣብዎት ጊዜ ቶሎ መሽናት
👉ሶፍት ስንጠቀም ከፊት ወደ ኋላ መጠቀም
👉ውሃ በብዛት መጠጣት
👉በገንዳ ከመታጠብ ይልቅ በቁም ሻወር መጠቀም
👉ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት ብልተዎን ማጽዳት /መታጠብ
👉ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ወዲያውኑ መሽናትና ወደ ዮሬትራ የሚገቡትን ባክቴሪያዎች ማስወገድ
👉የብልት አካባቢ ሁሉ ጊዜ ደረቅ እንዲሆን ማድረግ
👉ከውስጥ የምንለብሳቸው (ፓንት) ኮተን መጠቀም ንፅህናውን መጠበቅ
መልካም ጤንነት!!
#ልብ #ድካም

❤️ልብ ድካን ማለት የልብ አካል ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም የአሰራር ለዉጥ
ምክንያት ለተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች የሚሰራጨዉ ደም በቂ ሳይሆን ሲቀር የሚከሰት የጤና መታወክ ነዉ፡፡
የልብ አካል ጉዳት ሲባል #የልብ #ቫልቮች #መጥበብ ወይም #መስፋት #የልብ #ደም #ስሮች #መጥበብ #የልብ #ጡንቻና #ማቀፊያ #መጎዳት ሊሆን ይችላል፡፡
👉#የልብ #ድካም #መንስኤዎች
ተፈጥሮአዊ የልብ በሽታ ወይንም ከጊዜ በኋላ በሚመጣ የልብ በሽታ ሊሆን ይችላል፡፡
-በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በተጨናነቀ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናት በተደጋጋሚ
በቶንሲል ህመም ይጠቃሉ፡፡ ለዚህ ቶንሲል በሽታ የተመረቱ አንቲቦዲ የተባሉ በሽታ ተከላካዮች የልብ ቫልቮች መጥበብና መስፋት ጋር ተያይዞ ለልብ ድካም ይዳርጋሉ፡፡
👉ከፍተኛ የደም ግፊት ከልብ ጡንቻና ልብ ማቀፊያ በሽታ ጋር ተያይዞ
የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡
👉ከልብ ደም ቧንቧ መጥበብ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉ የልብ ድካም በአብዛኛዉ በዕድሜ በገፉና በወንዶች ላይ ይከሰታል፡፡
👉በተጨማሪ በቤተሰብ ታሪክ ተመሳሳይ በሽታ መኖር፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ዉፍረት፣ ስኳር በሽታ፣ ኮሊስትሮል መብዛትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ለዚህ በሽታ የመጋለጥ ዕዱልን ይጨምራል፡፡
👉ሲጋራ ማጨስ ሲጋራ ለደም ቧንቧዎች መጥበብ እንደሚያጋልጥ በጥናት ተረጋግጧል፡፡
👉ከፍተኛ የደም ግፊት ለረዥም ጊዜ ሳይታከም የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊት
የልብ ደም ቧንቧዎችን በማጥበብና የልብ ጡንቻዎችን በማወፈር ለልብ ድካም ይዳርጋል፡፡
👉ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ሥርዓት ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ስብና ቅባቶችን አብዝቶ መመገብ ደም ዉስጥ የኮሌስትሮል መጠንን ከፍ በማድረግ ለደም ቧንቧዎች ጥበት ይዳርጋል፡፡
👉#የልብ #ድካም #ምልክቶች
በቀላሉ መድከምና አቅም ማጣት፣ ያለምንም እንቅስቃሴ ወይም መጠነኛ
የአካል እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ሰዓት ትንፋሽ ማጠር በመኝታ ላይ ትንፋሽ ማጠርና ከዚህ ጋር በተያያዘ የመኝታን ራስጌ ከፍ አድርጎ ወይም ትራስ ደራርቦ መጠቀም፤ ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ አስፈሪ እና ከፍተኛ የሆነ ትንፋሽ ማጠር፣ ሌሊት ላይ የሚበረታ ሳል፣ እግር ማበጥ ወይም ከእግር የሚጀምር የሰዉነት ማበጥ የልብ መምታትና የትርታ መጨመር፤ ፌንት ማድረግ፤ ደረት ህመም እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ማቅለሽለሽ፣ የሆዱ መንፋትና ሆድ ህመም ዋና ዋናዎቹ የልብ ድካም ምልክቶች ናቸዉ፡፡
#የደረት #ራጅ#ECG #ኢኮካሪዲዮግራፍና ሌሎች የደም ምርመራዎች የልብ በሽታን በደንብ ለመለየትና ለማከም አስፈላጊዎች ናቸዉ፡፡
👉#የልብ #ድካም #ህክምናና #የመከላከያ #መንገዶቹ
የልብ ድካም ቀላል የሆኑ አባባሽ ነገሮችን ከማከም እስከ ከፍተኛ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ሊያስፈልገዉ ይችላል
#የልብ #ድካምን #ሊያባብሱ #የሚችሉ #ነገሮችን #ማስወገድና ማከም ለምሳሌ
#የሳንባ ምች፣ #የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን #ደም #ማነስ#ከፍተኛ #የደም #ግፊት#መድሃኒትን #ማቋረጥ#እርግዝና#አልኮል #አብዝቶ #መጠጣት#ጨዉ #አብዝቶ #መመገብ #የልብ #ድካምን #የሚያባብሱ #ነገሮች ናቸዉ፡፡
👉በሀኪም የታዘዙ የልብ ድካም አጋዥ መድሃኒቶችን በሀኪም በታዘዘዉ
መሠረት በተገቢዉ ሁኔታ መጠቀም
👉ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ የልብ ቀዶ ጥገናዎችን በማድረግ በሽታዉን መከላከል ይቻላል፡፡
👉#የልብ #ድካም #ላለባቸዉ #አመጋገባቸዉ #ምን #መሆን #ይኖርበታል
👉የሚመገቡትን የጨዉ መጠን እንዲቀንሱ ይመከራሉ /በቀን የሚወስዱት
የጨዉ መጠን ከ2-3 ግራም መብለጥ የለበትም
👉ተመጣጣኝና ተጨማሪ ሃይል ሰጪ ምግቦችን በትንሹ መጠን ቶሎ ቶሎ መዉሰድ
👉አልኮል አለመጠጣት
👉በሀኪም ትዕዛዝ ካልተከለከለ በስተቀር በርከት ያለ ፈሳሽ መዉሰድ
#የአካል #ብቃት #እንቅስቃሴን #በተመለከተ
ከባድ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የልብ ድካም ላለባቸዉ ሰዎች
አይመከርም፡፡ ነገር ግን መጠነኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማዘዉተር እጅግ ጠቃሚ
ነዉ፡፡ መቋቋም የተቻላቸዉን ያህል የአካል እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ ማድረግ
ይመከራል፡፡
#የልብ #ድካም #መከላከያ #መንገዶች
👉ከፍተኛ ደም ግፊትን መቆጣጠርና ህክምና ማድረግ
👉 ስኳር በሽታን መቆጣጠር
👉 ሲጋራ አለማጨስ
👉የሰዉነት ክብደትን መቆጣጠር
👉 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ (አቅምን ያገናዘበ ቢሆን ይመረጣል)
👉ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በመድሃኒት መቀነስ
👉 ህፃናት ቶንሲል ሲታመሙ እንዲታከሙ ማድረግ
👉 የታዘዘን መድሃኒት ሳያቋርጡ በአግባቡ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡

መልካም ጤና ውዶቼ 👋