ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
እየሱስ ይመለካልን?

አንድ ወዳጄ በውስጥ በኩል አንዲት ያረጀች የሙሃመዳውያንን ፅሁፍ ልኮልኝ አስገርማኛለች። ፅሁፏ በአንድ ዑስታዝ ተብዬ ሰው ቢሆንም እራሱ አጥንቶ ያመጣው ሳይሆን ብዙ አመታት የቆየችና በተለይ ደግሞ ምዕራቡያዊያን ይሆዋ ምስክሮች ሲጠቀሟት የከረመች ሙግት መሆኗ አዝናንታኛለች። ትችቱም፣ እየሱስ ላለመመለኩ እንደማስረጃ የግሪኩን ቋንቋ በመጥቀስ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን፣ የሙግቱ ፅንሳ ሃሳብ እንዲህ የሚል ነው።
“ ‘አምልኮ’ የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አባድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ለአብ ብቻ እንደሚገባ ባይብል ላይ ሰፍሯል፦
ዘዳግም 10፥20 አምላክህን ያህዌህን ፍራ፥ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።
ዘዳግም 13፥4 አምላካችሁን
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ #አምልክ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ልብ አድርግ አንድ ማንነት ብቻ ያለው አንድ አምላክ መሆኑን ለማመልከት “እርሱን” ብቻ አምልክ በሚል በገላጭ”adjective” የተጠፈነገ ነጠላ ተውላጠ ስም እንጂ “እነርሱ” የሚል የለም። እስቲ ይህ ቃል ለኢየሱስ የዋለበትን ጥቅስ ጠቅሰህና አጣቅሰህ አሳየኝ።”

#መልስ
ይህንን ሙግት በሁለት ከፍለን እንመልሳለን
፩- λατρεύω ‘አምልኮ' ለእየሱስ መጠቀሙን
፪- በነጠላ (singular) ገላጭ ( whether noun,pronoun or adjective depending on what they are conveying) ዙሪያ ሙግት

፩- λατρεύω ‘አምልኮ' ለእየሱስ መጠቀሙን

በመጀመሪያ ደረጃ λατρεύω የሚለው ቃል ለአምላክ ብቻ የሚሰጥ ስግደትን ለመግለፅ አንጠቀምበትም። ትርጉሙም ‘አምልኮ' ብቻ ሳይሆን “ማገልገል to give service' ተብሎም ይመጣል። ለዚህ ደግሞ እንደማስረጀ፣ ታላቁ የአዲስ ኪዳን የግሪክ ቋንቋ ምሁር #Thayer በThayer’s Lexicon ፅፈውታል። እንዲህም ብሏል። “..ቃሉ በሰፊው ሲተረጎም ‘ሰዎችን ወይም አምላክን ማገልገል፣ ለባሪያዎችም የምንጠቀም ይሆናል፣ ...አጥብበን ከተጠቅምን ደግሞ ማምለክ ማለት ነው..”
λατρεύω; future λατρεύσω; 1 aorist ἐλάτρευσα; (λάτριςa hireling, Latinlatro in Ennius and Plautus; λάτρον hire); in Greek writings a. to serve for hire;
b. universally, to serve, minister to, either gods or men, and used alike of slaves and of freemen; in the N. T. to render religious service or homage, to worship (Hebrew עָבַד, Deuteronomy 6:13; Deuteronomy 10:12; Joshua 24:15); in a broad sense, λατρεύειν Θεῷ: Matthew 4:10 and Luke 4:8, (after Deuteronomy 6:13); Acts 7:7; Acts 24:14; Acts 27:23; Hebrews 9:14; Revelation 7:15; Revelation 22:3; of the worship of idols, Acts 7:42; Romans 1:25 (Exodus 20:5; Exodus 23:24; Ezekiel 20:32)

ይሁንና ትርጉሙን አጥብበን እንጠቀም ካልን እእራሱ መፅሐፍ ቅዱስ λατρεύωን ለእየሱስም ተጠቅሞ እናገኛለን።

የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22
3፤ ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል( λατρεύσουσιν ) ፊቱንም ያያሉ፥ 4፤ ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
3 And there will be no more curse: and the high seat of God and of the Lamb will be there; and his servants will be worshipping him; And they will see his face; and his name will be on their brows.
Λατρεύσουσιν- ይህ ቃል የ λατρεύω future tense መሆኗን በ ευ እና ουσιν መካከል ያለችዋ ‘σ’ ስታሳይ፣ -ουσιν ደግሞ third person plural መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ “ ያመልኩታል” የሚል ትርጉም ይሰጣል። ስለዚህ፣ ለእየሱስ እና ለአብ አንድ ላይ λατρεύω ተጠቅሞ እናገኛለን።

፪- በነጠላ (singular) ገላጭ ዙሪያ

ጥያቄው አሁን፣ “ያመልኩታል” የሚለው verb ለነጠላ ማንነት መሆኑን ለመግለፅ ቀጥሎ የሚመጣው αὐτῷ(him) singular pronoun ሆኖ እያለ፣ ለእየሱስ ወይም ለአብ መሆኑ አልተገለፀም(ያመልኳቸዋል አልተባለም) የምትል ትያቄ ነች።
ይህንን መልስ ከመስጠቴ በፊት በዚህው ክፍል ላይ ከፍ ብለን እናንብብ
የዮሐንስ ራእይ 22:1
በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ #ዙፋን θρόνου (throne) የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።"

221Καὶ ἔδειξέν μοι ποταμὸν ὕδατος ζωῆς λαμπρὸν ὡς κρύσταλλον, ἐκπορευόμενον ἐκ τοῦ θρόνου τοῦ θεοῦ καὶ τοῦ ἀρνίου.
θρόνου- “ዙፋን” የሚለው ቃል እዚህ ጋር ለበጉና ለእግዚያብሔር ቢጠቀምም ነጠላ. Singular ነው። በእንግሊዘኛውም thrones ሳይሆን throne ብሎ ለሁለቱም አንድ ላይ ተጠቅሟል። ይህ የሚያሳየው በጉንና አብን እንደ አንድ እየወከለ መሆኑን ነው። በዚው በተመሳሳይ ሁኔታና ክፍል ነው እንግዲህ αὐτῷ(him) የሚለውን ቃል ለበጉም ለአብም አንድ ላይ መመለካቸውን ለማሳያ የተጠቀመው። ልብ በል፣ #ዙፋን ስንል የሆነ መቀመጫ ወይም ወንበር አይደለም፣ የአምላክነታቸውን power or authority በአንትሮፖሞርፊክ መግለጫ ማሳያ ነው እንጂ። ስለዚህ፣ ይሄን ነገር ለሁለቱም በነጠላ ከተጠቀመ፣ ሁለቱን አንድ ላይ እየገለፀ ነው ማለት ነው። በሔርሜኒውቲክስ ደግሞ፣ አንድን ክፍል ስንተሮግም፣ ሙሉ አውዱን ማየትና ሌላ ቦታ ተመሳሳይ አጠቃቀም፣ ለሁለት ተመሳሳይ ባህሪያት መኖሩን ማጥናት ይኖርብናል። ካልሆነ፣ word study fallacy የምንለውን የኤግዜጄትካል ፋላሲ (ስህተት) መስራታችን አይቀሬ ነው፤ ልክ ኡስታዞቹ ቡማያውቁት ገብተው እንደሚበጠብጡት ማለት ነው።
አይሆንም፣ “ስድግደት እዚህ ጋር ለነጠላ ፐርሰን መሆን ስላለበት ለአብ ብቻ ነው” የሚል ቢኖር እራሱ፣ ሙግቱ ውድቅ ይሆናል። ምክኒያቱም፣በግሪክ ግራመር አንድ ፐርሰናል ፕሮናውን ለሆነ ስም ሲቆም፣ ሊገልፅ የሚችለው፣ ከሱ አጠገብ(immidiate noun) ያለውን ነው እንጂ ከአያያዥ በፊት ያለውን ስም አይደለም። “ያመልኩታል” ለሚለው ደግሞ፣ immidiate noun #በጉ ነው። ስለዚህ፣ በዚህም ሙግት ብንሔድ በጉ ነው የሚመለከው ማለት ነው

ቀጥለህ ኣንብብ...

Ναολ Τζιγι

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified