ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ወንጌል  👉  ክፍል 2

#የማኑስታክሪብቶች_ልዩነት

አንዳንድ ሙሓመዳውያን በጥንት የግሪክ አዲስ ኪዳን ማኑክሪፕቶች መኻከል ያለውን ልዩነት እየጠቀሱ፣ ቃላቶች በዚህኛው መኑስክሪፕት ላይ አለ እዛኛው ላይ የለም እያሉ ለማደናገር ይሞክራሉ። ወደ እያንዳንዱ ከመሔዳችን በፊት ስለ መፅሓፍ ቅዱስ ማኑስክሪፕቶች እናጥና ፤ እንመለስበታለን።

በመጀመሪየ ደረጃ፣ ለመፅሓፍ ቅዱሳችን ያለን የጥንት ማኑስክሪፕቶች(እደ ኪታባት)፣ ከየትኛውም አለም ላይ ከሚገኙ የጥንት ፅሑፎች በብዛት እጅግ የላቀና እጅግ ወደፀሓፊዎቹ በጊዜ ቅርበት የቀረቡ መሆናቸውን ምሁሮች አረጋግጠውልናል። ይሄን ስንል፣ ኦሪጅናል በጳውሎስ እጅ በብራናው ላይ የያተጳፈው ፅሁፍ በጊዜ ምክኒያት ላናገኘው  እንችላለን። ነገር ግን ጳውሎስ በእጁ ከፃፊው ላይ በ 145A.D የተገለበጡ ማኑስክሪብቶች እድሜያቸው ረዝሞ ዛሬ ላይ መገኘታቸው እጅግ አስደናቂ ነው። የትኛውም የጥንት ማኑስክሪፕት ሆኖ እንደ አዲስ ኪዳን ወደ ኦሪጅናሉ የሚቀርብ ስነ ፅሁፍ አለም ላይ የለም። ታድያ ሙስሊሞች ሁሌ ኦሪጅናሉ ፅሑፍ የለም ብሎ ሙግት ሲስሩ(actually ሲሰርቁ) ያስቃል። ወረቀት መቼስ ዘላለም አይኖርም፤ ነገር ግን ፅሁፎቹ በጥንቃቄ እየተገለበጡ ለዘላለም ይኖራሉ እንጂ። ለማንኛውም፣ ወደ ርዕሳችን እንግባ።

ሙስሊሞች እንደሙዚቃ የሚያዜሟት ከ"ባርት ኤሕርማን"(ከክርስትና ያፈነገጠ የአዲስ ኪዳን ቴክስቿል ክሪቲክስ ፕሮፌሰር ነው) የሰረቋት ሙግት አለች። "በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉት የቃላት ብዛት ይልቅ በአዲስ ኪዳን(ግሪክ) እደ ኪታባት መኻከል ያለው ልዩነት ይበልጣል" የሚል ነው። በነገራችን ላይ፣ ይህቺ ዐረፍተ ነገር በራሷ ተነጥላ ስትታይ እውነት ነች። ነገር ግን ማብራሪያ ስታገኝ ምንም በእምነታችን ላይ ወይም በመፅሓፍ ቅዱሳችን ላይ የሚያመጣው ችግር ወይም ጥርጣሬ አይኖርም።

በአዲስ ኪዳን ግሪክ ውስጥ ወደ 138,000 ቃላት አሉ። የግሪክ ማኑስክሪፕቶች ደግሞ ብዛታቸው ከ5,700 በላይ ናቸው። በእነኚህ ማኑስክሪብቶች መካከል ከቃላቶቹ ብዛት 3 እጥፍ (300,000-400,000) ልዩነቶች አሉን። ነገር ግን እነኚህ ልዩነቶች ምንድናቸው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። ለመጀመር ያህል፣ የግሪክ ቋንቋ እጅግ ኮምፕሌክስ እና አንዳንዴ ወደ ሌላ ቋንቋም ሊተሮጎሙ የማይችሉ ቃላቶችን ያዘለ ነው። በተጨማሪም አንድን አረፍተ ነገር፣ትርጉሙን ሳንቀይረው በብዙ አይነት መንገድ መናገር እንችላለን። ለምሳሌ፣ "#እየሱስ_ጳውሎስን_ይወዳል" ለማለት በግሪክ ቋንቋ ትርጉሙ ሳይቀየር በብዙ መንገድ መፃፍ ይቻላል።
1.᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ Παῦλον᾿
2.Ιησοῦς ἀγαπᾷ τὸν Παῦλον
3.ὁ ᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ Παῦλον
4.ὁ ´Ιησοῦς ἀγαπᾷ τὸν Παῦλον
5.Παῦλον ᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ
6.τὸν Παῦλον ᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ
7.Παῦλον ὁ ᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ
8.τὸν Παῦλον ὁ ᾿Ιησοῦς ἀγαπᾷ
9.ἀγαπᾷ ᾿Ιησοῦς Παῦλον
10.ἀγαπᾷ ᾿Ιησοῦς τὸν Παῦλον
11.ἀγαπᾷ ὁ ᾿Ιησοῦς Παῦλον
12.ἀγαπᾷ ὁ ᾿Ιησοῦς τὸν Παῦλον
13.ἀγαπᾷ Παῦλον ᾿Ιησοῦς
14.ἀγαπᾷ τὸν Παῦλον ᾿Ιησοῦς
15.ἀγαπᾷ Παῦλον ὁ ᾿Ιησοῦς
16.ἀγαπᾷ τὸν Παῦλον ὁ ᾿Ιησοῦς
ልብ በሉ፣ለዚህች አንድ አጭር ዓረፍተ ነገር እንኳን ይሄ ሁሉ የተለያየ ግን ተመሳስይ ትርጉም ያላቸውን አፃፃፍ መስቀመጥ እንችላለን። በዚህ እይታ ስናየው ልዩነቶቹ ውሓ የማይቋጥሩ ሙግት  ይሆናሉ። ከልዩነቶቹ መካከል #99% ምንም የትርጉም ወይም አረዳድን የሚለውጡ (meaningful and viable) አለመሆናቸው ምሁራን አስረግጠው ደምድመውታል።

ዛሬ ላይ ያሉ የአዲስ ኪዳን(ግሪክ) ቀደምት ማኑስክሪፕቶችን በገፅ ብንቆጥራቸው ወደ 1.3 ሚሊዮን ገፅ ናቸው። ልብ በሉ፣ ብዙ ማኑስክሪፕት ሲኖርህ፣ብዙ ልዩነቶች ይኖሩሓል። ያውም፣ መፅሓፍቶቹ በእጅ በሚገለበጡበት ዘመን።  ስለዚህ፣ የ3መቶ ሺህ  አንድ ፐርሰንት የማትሞላ viable "የቃላት ልዩነት" በ 1.3ሚልዮን "ገፅ" እደ ኪታባት መካከል አለ ተብለህ ስትነገር፣ መፅሓፍቶቹ በሚገርም ጥንቃቄ ለ 2000 አመት እንደተላለፉልህ ትረዳለ። ከዛ ያሉትን ልዩነቶች ደግሞ ማጥናት ትጀምራለህ። 

በሚቀጥለው ክፍልና በቅርቡ በምንለቀው መፅሓፍ (የባርትና የ ዋላስ ውይይት በመፅሓፍ) ይህኑ "ልዩነት" የተባሉትን የምናስነብባቹ ይሆናል።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified