ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ወንጌል  👉  ክፍል 1

እንደተለመደው፣ የ ሙሓመድ ጠበቃዎች (ኡስታዝ ተብዬዎች) ኢንግሊዘኛውን በደምብ እንኳ ማንበብና መጥቀስ ባይችሉም ከክርስቶስ ተቃዋሚ የመጽሓፍ ቅዱስ ምሁራን ነን ባዮች መፅሓፍ ቀድተው፣ ኮርጀው፣ የኮረጁትን ደግሞ  በጽናት እየተሳሳቱ እየፃፉ አዋቂ መሳይ አላዋቂ መሆናቸውን ለኛ ማረጋገጣቸውን ተያይዟል። ከነሱ አንዱ፣ እንዲያውን 4 ተከታታይ ኦድዮችን "ወንጌል" ብሎ ሰርቷል። እጅግ በጣም ብዙ ስህተቶችንም አግኝተንበታል። ሰው ቢያንስ የኮረጀውን እንኳን አንብቦ ተረድቶ፣ እውነት መሆኑን፣አለመሆኑን ማረጋገጥ ይከብደዋል?? ለማንኛውም፣ እያንዳንዱን ነጥብ ብናነሰ ብዙ ስህተት ስላለበት በመፅሓፍ ካልሆነ በቻነላችን ብቻ አንጨርሰውም። ይሁንና ሰዎቹ የሚጀምሩት ከ #አዲስ_ኪዳን_ቀኖና ስለሆነ ከሱ እንጀምራለን። መሓል መሓል ላይም በስሕተቶቻቸውና አላዋቂነታቸው እየተዝናናን እንጨርሰዋለን።

ወንጌል የተሰኘው በ ኡስታዝ ተብዬው የተሰራ ኦድዮ ሁለተኛ ክፍል ላይ (አንደኛው ክፍል ዝም ብሎ ትርክት እንጂ ታሪክ አይደለም፣ እንመጣበታለን) ልጁ፣ ዛሬ ላይ ያለው ወንጌል የተለዋወጠ ነው ለማለት የተጠቀመው፣ ወንጌል ከመፃፉና ከተፃፈ በኋላ ልዩነት እንዳለውና  አሁን ላይ የ አዲስ ኪዳን ቀኖና ያልሆኑ ወንጌላት (የጼጥሮስ ወንጌል፣ የበርናባስ ወንጌል  ወዘተ)  ሆነ ተብለው በ 1ኛ ና 2ኛ ክፍለ ዘመን ከመጽሓፍ ቅዱስ እንደወጡ ማሳየት በመሞከር ነው። ወደ ጥናታችን ሳንገባ፣ እንዲያውም አንደኛው ስህተቱን አጋልጠን እንለፍ። ልጁ ነጥቡን በማስረጃ ለማሳየት 1ኛ ጢሞ 5:14 ላይ ያለውን ይጠቀማል።

" መጽሐፍ። የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥ ደግሞ። ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:18)
ኡስታዝ ተብዬው ያለው " የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር'  የሚለው እኮ ተፅፎ  በ ባይብል ውስጥ አናገኘም። ከየት አምጥቶ ነው ጻውሎስ መልዕክቱን ወደ ጢሞትዮስ ሲልክ ፣"ይህ ነገር ተፅፏል ያለው?" የሚል ነው። ነጥቡ፣ ይሄ ነገር ዛሬ በእጃችን ላይ ባለው 4ቱ ወንጌል ውስጥ ተጽፎ ስለማይገኝ፣ ወንጌል ተበርዟል ነው።

ምነው ወዳጄ? መጽሓፍ ቅዱስን "ሓፍዤያለው" ስትል ነበር አላሉም?? እና ታዲያ ዘዳግም 25:4 ን ዘለህ ነው "ያፈዝከው??"  ነው ወይስ ጻውሎስ እዚህ ላይ "መጽሓፍ" ያለው የግድ ከ አራቱ ወንጌል ብቻ መሆን አለበት??ያለማወቅ ጥግ!!

" እህል የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። " ይሔው!!
(ኦሪት ዘዳግም 25:4)

ለማንኛውም ወደ ርዕሳችን እንመለስና ስለ መጽሓፍ ቅዱስ ቀኖና እናውራ።

#የ_አዲስ_ኪዳን_ቀኖና_እንዴት_ተሰበሰበ?

 የሙሓመድ ጠበቃ የሆነው አንዱ፣ ስለ ቀኖናዎቹ ትክክል አለመሆን ሲያብራራ የ #ባርት_ሔርማንን ስም እና እንዳለ መፅሓፍቶቹን ጠቅሷል። የአዲስ ኪዳን ቀኖናም ልክ አራተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ላይ እንደተወሰነና ከሱ በፊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌሎች ብዙ ባይብሎችን፣ ከ አራቱ ወንጌላት ውጪ፣ ይጠቀሙ እንደ ነበር አውርቷል። እስኪ ባርት ሔርማን የፃፈውን እናንብብ።
   "በክርስትና ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 27ቱ የ አዲስ ኪዳን ቀኖና መቼ እንደተሰበሰቡ ማወቅ እንችላለን።..በሚገርም ሁኔታ ይህ የተከናወነው በ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ ነበር፤ የ አዲስ ኪዳን መጽሓፍቶች ከተፃፉ ከ 300 አመት በኋላ። 27ቱንም የሰበሰበው የ አሌክሳንድሪያው ቄስ #አታናሲዮስ በ 367 C.E ነው። አታናሲዮስም ግብጽ ወዳሉት የቤተ ክርስቲያን አመራር ዬትኞቹ መጻሕፍት በ ቸርች ውስጥ መነበብ እንዳለባቸው መልዕክት ፅፎ ነበር።.." #ባርት_ሔርማን

ከላይ እንዳነበብነው፣ የባርት ሔርማን እንዲውም የሙስሊሞች ስህተት ሁለት ነገር ነው።

1. እስከ አራተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የትኞቹ መጽሓፍቶች ስልጣን እንዳላቸው (ተቀባይነት እንዳላቸው) (Authoritative) ምንም አይነት ስምምነት ወይም እውቅና አለመኖሩን መናገራቸው
2. ለቤተ ክርስቲያን ስታንዳርድ(standard) የሆነው የአንድ ቄስ ጽሁፍ ብቻ እንደነበረ መግለፃቸው ከእውነት የራቀ ነው።

እውነታው ግን፣ የትኞቹ መፅሓፍቶች ስልጣን እንዳላቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታወቀው ገና በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን እንደሆነ ከብዙ የቀደምት አባቶች ፅሑፍ ማወቅ ተችሏል። እነኚህ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቀኖና እንዲሆኑ ያስተላለፉልን "#የጌታችን_የእየሱስ_ክርስቶስ_የ_አይን_ምስክሮች_ጋር_ግንኙነት_ያላቸው_ፅሑፎችን_ብቻ" ነበር።

የሒዬራፖሊሱ ፓፒያስ (70-155 AD) ይኖር ነበር። የጌታችን ሓዋሪያ ዮሓኒስ በሕይዎት እያለ መለት ነው። በዚህ ዘመን መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ዬትኞች መፅሓፍቶች ስልጣን እንዳላቸው በ ፅሑፉ ውስጥ ገልጾልናል። ላስነብባቹ
"..ብዙ በሚያወሩ ሰዎች ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንስ እውነተኛውን ትምህርት በሚያስተምሩት እንጂ። ብዙ ግራ የሚያጋቡ ትምህርቶችን የሚያስተምሩን አልቀበለም፤ ከጌታ እራሱ ትዕዛዙን የተቀበሉትን እንጂ።.. ስለዚህ ማንም ዛሬ ምጥቶ ይሄን ቃል ከ ኤጌሌ ነው የሰማሁት ብሎ ቢነግረኝ፣ ቃሉን ለመቀበል መጀመሪያ  ኢንድሪያሥ ወይም ጴጥሮስ  ወይም ፊሊጶስ ወይም ከያዕቆብ ወይም ደግሞ ቶማስ.. ምን አሉ? ብዬ እስካረጋግጥ ድረስ አልቀበልም"
(ምንጭ፡ Fragments of Papias, ANF: From exposition of the Oracles of the Lord)

ይሄ ክፍል የሚነግረን በ መጀመሪያ መቶ ክፍለ ዘምን እንኳን፣ ስልጣን ያላቸው መጽሓፍቶች ከጌታችን የአይን ምስክሮች የተገኙ መሆን እንዳለባቸው ነው። ልብ በሉ፣ ሰዎች የውሸት ወንጌሎችን በሓዋርያት ስም ሊፅፉ ይችላሉ። እነሱም እንዴት እንደተለዩና እንደቀኖና ለምን እንዳልተቀበልነው እንመጣበታለን።