ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ሌላ ምሳሌ እንመልከት። ሺፐርድ ኦፍ ሔርማስ (Shepherd of Hermas) የተሰኘ አንድ አንድ ሰዎች ቀኖና ውስጥ እንዲገባ ሞክረው የነበሩ መፅሓፍ አለ። በኮዴክስ ሲናይቲከስ ውስጥ እናገኘዋለን።
2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩ ፀሓፊዎች፣ ይህ መፅሓፍ ለምን ቀኖና ውስጥ እንዳልተካተተ ሲገልጹ እንዲህ ጽፏል። (ልብ በሉ፣ ይሄ ገና እነ አታናሲዮስ ሳይወለዱ ነው።)
"ሔርማስ ይሄንን መፅሓፍ  በቅርቡ በእኛ ጊዜ በሮማ ውስጥ ሆኖ ነው የፃፈው። መጽሓፉ ቢነበብ መልካም ቢሆንም፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነበብ የለበትም፤መታተምም የለበትም። ምክኒያቱም እሱ #ከሓዋሪያት_አንዱ_አይደለም ሁሉም ሞቷልና፣ ከነብያትም አይደለምና።"
Muratorian Canon in Latin, verse 44-49

በዚህም ክፍል ላይ በግልፅ ስልጣን ያላቸው ፅሑፎች ከጌታችን የአይን ምስክሮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስክሪፕቸሮች እንደሆኑ ነው።

በ 199 A.D ሴራፒዮን የሚባል የ አንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ የሆነው "የ ጴጥሮስ ወንጌል" ስለተባለው መጽሓፍ እንዲህ ብሎ ጽፏል።
"እኛ ጴጥሮስንና ሌሎች ሓዋርያትን ልክ ክርስቶስን እንደተቀበልን እንቀበላቸዋለን። ነገር ግን በእነሱ ስም የተጻፉትን መጽሓፍትን ግን ከነሱ ያልሆኑትን ሁሉ አንቀበልም። ምክኒያቱም እነኚህ መጽሓፍቶች ከእነሱ ወደ እኛ የተላለፉ ስላልሆኑ ነው።"  ብሎ ይህንን የጴጥሮ ወንጌልና ሌሎች የሓሰት ወንጌሎችንም በመቃወም በሰፊው ጽፏል። ልብ በሉ፣ ይህ የሆነው፣ ገና አታናሲዮስ ቀኖናውን ሰብስቦታል ከተባለው ከ 200 አመት በፊት ነው።
Eusebius' Church history; book 6, chapter 12. Serapion and his extant works.

200 A.Dአከባቡ፣ "የጳውሎስ ስራ" (Acts of Paul) የሚባል መጽሓፍ ልክ ጳውሎስ እንደፃፈው ተደርጎ ተፅፏል። እዚህ መጽሓፍ ውስጥ ተጽፈው የሚገኙ ነገሮች አስገራሚ ናቸው። ለምሳሌ፣ ጳውሎስ አንድ ትልቅ አንበሳ አጥምቆ እንደነበር አለ። በኋላ ላይ ሰዎች ይህንን መጽሓፍ በሰፊው እንደቀኖና መጠቀም ሲጀምሩ የካርቴጁ #ቴርቱሊያን  ጥናት አድርጎ የዚህ መጽሓፍ ፀሓፊ ጳውሎስ ሳይሆን አንድ የ ኤዥያ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ከ ጳውሎስ ሞት ከ40 አመት በኋላ የፃፈው እንደሆነ ስለደረሰበት፣ ከቀኖናው ውጪ ሆኗል።
(Tertullian of Carthage De Baptismo 17)

እነኚህ መጽሓፍቶች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም፣ ለምሳሌ፣ " የይሁዳ ወንጌል፣ የፊሊጾስ ወንጌል፣ የማርያም ወንጌል፣ የግብጾች ወንጌል..ወዘተ" ሁሉም የአይን ምስክሮቹ ከሞቱ ከብዙ አመታት በኋላ የተጻፉ በመሆናቸው ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያውኑ እንደ ቀኖና አልተቀበለቻቸውም። እንዲህ አይነት ኢ-ቀኖናዊ የሆኑ ወንጌላት እየበዙ ሲሔዱ እነ አታናሲዮስ በ 367 A D ዛሬ በእጃችን ያለውን ወንጌል ለይተው አንድ ላይ እንዲታተም አደረጉ እንጂ እራሳቸው የፈጠሩት አዲስ ቀኖና የለም። ስልጣን ያላቸው መፅሓፍቶች ገና ከመጀመሪያውኑ የታወቁ ናቸው እንጂ አዲስ በ 367 የተፈጠረ  ነገር የለም።

በመጨረሻም፣ ሓዋርያት እራሳቸው የትኞች ንግግሮች ወይም ፅሑፎች ስልጣን እንዳላቸው ነግረውናል።

" ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።"
(የሐዋርያት ሥራ 1:21-22)

(ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ 1)
----------
7፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።

8፤ ነገር ግን #እኛ_ብንሆን_ወይም_ከሰማይ_መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
1😱1