ለምን አልሰለምኩም?
2.92K subscribers
51 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Yahya Ibnu Nuhe "እየሱስ የሞተው 'ታንቆ' ነው ወይስ 'ተሰቅሎ'?" እያለ ነበር። ፅሁፉ እንዲህ ይላል:-

//" እናንተ በእንጨት ላይ #ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤"
(የሐዋርያት ሥራ 5: 30)
የአማርኛ ተርጓሚዎች ይህንን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ሲተረጉሙ በአማኙ ላይ ማታለያ ፈፅመዋል። የእንግሊዝኛውም ሆነ የግሪኩ ቃል "ሰቅላችሁ" አይልም። ይልቅስ የሚለው "አንቃችሁ" ወይንም "Hanged" አልያም በግሪከኛው "κρεμάννυμι" ነው። ለማስረጃነት ከታች ሁለቱንም ትርጉሞች አስቀምጥላችኃለው።"//

በመጀመሪያ ደረጃ፣ "#ታንቆ_መሞት" ለሚለው ቃል የምንጠቀመው የግሪክ ቃል κρεμάννυμι(ክሬማኑሚ) ሳይሆን ἀπάγχω (አፓግኾ) ነው። ለምሳሌ:-

" ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና #ታንቆ ሞተ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 27:5) (ስለ ይሁዳ ሲያወራ)
καὶ ῥίψας τὰ ἀργύρια εἰς τὸν ναὸν ἀνεχώρησεν, καὶ ἀπελθὼν #ἀπήγξατο.

κρεμάννυμι የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም አለው። መስቀል(ለምሳሌ :-ጃኬቴን እንጨቱ ላይ ሰቀልኩት ማለት ከፈለግኩ በግሪክ ይህን ቃል ነው የምጠቀመው(ጃኬቴን እንጨት ላይ #አነቅኩት አይባልም)፣ እየሱስም የተሰቀለው እንጨት ላይ ተንጠልጥሎ ነው(κρεμάννυμι) እንጂ እንጨት ላይ እንደ አልጋ ተኝቶ አይደለም። ለዛ ነው ይህን ቃል የተጠቀመው።

κρεμάννυμι "depend" (የተመረኮዘ) (hangs on) የሚል ትርጉምም ሊሰጠን ይችላል። ለምሳሌ:-

" በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል(κρέμαται)።"
"40 On these two commandments the whole law #hangeth(depends), and the prophets."
(Matthew 22:40)
(የማቴዎስ ወንጌል 22:40)

የህያ ወዳጄ፣ እየሱስ ላንተም ኃጢአት ተሰቅሎ ሞቶልሃል እና ከእንዲህ አይነት የህፃን ጨዋታ ውጣ።

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified