Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
#ስቅለትን_በተመለከተ_እስላማዊ_ውዝግብ
ለሙስሊሞች ሙግት የተሰጠ ምላሽ
——————————
ሰሞኑን አንድ ሰለምቴ ነኝ ባይ ሙስሊም አፖሎጂስ የክርስቶስን ስቅለት በተመለከተ የጻፈውን ጽሑፍ አንዳንድ ወገኖች ሲቀባበሉት አይቼ ነበር፡፡ ጸሐፊው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተጻፉትን ዘገባዎች በማጋጨት “አልተሰቀለም” የሚለውን እስላማዊ የታሪክ ስህተት ለማጽደቅ ይሞክራል፡፡ እርሱ ያልተገነዘበው አንድ ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት መሆኑ ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባል መጽሐፍ እንኳ ባይኖር እስልምናን ከታሪካዊ ስህተቱ ማዳን የሚችልበት ዕድል አለመኖሩን ነው፡፡ የክርስቶስ ስቅለት በመጀመርያውና በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ ላይ በኖሩት የግሪክ፣ የሮም፣ የአይሁድና የክርስቲያን ጸሐፊያን የተዘገበና የተረጋገጠ በመሆኑ የክርስቶስን ስቅለት የሚክዱ ሙስሊሞች ከታሪክ መዛግብት ጋር ይላተማሉ፡፡ የክርስቶስን ስቅለት የሚክድ በሊቃውንቱ ዓለም ቦታ የሚሰጠው የታሪክ ምሑር ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን ግን ከክርስቶስ ስቅለት ከ600 ዓመታት በኋላ ወደ ዋሻ ገብቶ በመውጣት የክርስቶስን ስቅለት በተመለከተ ለብዙ ትርጎሞች የተጋለጠ የተምታታ ንግግር የተናገረውን የመሐመድን ቃል እውነት ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይባጥጡት ተራራ የለም፡፡ ይህንን ለማድረግ ከሚጣጣሩባቸው መንገዶች መካከል አንዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ስቅለትና ስለ ትንሣኤ የተጻፈውን ዘገባ እርስ በርስ ማጋጨት ነው፡፡ ይህ ጸሐፊ እንዲህ በማለት ይጀምራል፡-
———-
{{{{{የአዲስ ኪዳን ምሁር ሄርማን ቻርለስ በ 1890 AD ሲናገሩ፦ 5,800 የሚደርሱ የአዲስ ኪዳን ግሪክ እደ-ክታባት ይገኛሉ፤ እነዚህ እደ-ክታባት እርስ በእርሳቸው የቃላት ሆነ የትርጉም ልዩነት አላቸው፤ ለምሳሌ በሳይናቲከስና በቫቲካነስ እደ-ክታባት መካከል የ 3,036 የቃላትና የትርጉም ልዩነት አላቸው ብለዋል፤ ይህ ልዩነት የመጣው የአዲስ ኪዳን ስረ-መሰረት”orgion” ስለሌለና አሁን ያለት እደ-ክታባት የቅጂዎች ቅጂ ስለሆነ እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ፤ ይህ ልዩነት ጤናማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን የክርስትናን ዶግማ ክፉኛ ይፈታተናል፤ ምክንያቱም እነዚህን አራት ወንጌላት ሃዋርያት አለመፃፋቸው ብቻ ሳይሆን በእነርሱ የዳቦ ስም የገለበጡት ፅሁፍም ችግር ስላለበት ነው፤ እስቲ ይህንን ልዩነት ዛሬ በስቅለቱ ዙሪያ ያሉትን ዘገባዎች እንመልከት፦}}}}
————
#መልስ
ርዕሱ ስለ ክርስቶስ ስቅለት ሆኖ ሳለ ወደ ቴክስቹዋል ክሪቲሲዝም መዝለልህ አስገራሚ ነው፡፡ የክርስቶስን ስቅለት ከዚህ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ የዘመናችን ዕውቅ ቴክስቹዋል ክሪቲክና የሙስሊሞች ተወዳጅ የክርስትና ተቃዋሚ ባርት ኤህርማን እንኳ የክርስቶስን ስቅለት አጥብቆ ያምናል፣ የክርስቶስን ህልውና በሚክዱ ወገኖች ላይም ሲሳለቅ በተደጋጋሚ ይታያል፡፡ የክርስቶስን ስቅለት ከቴክስቹዋል ክሪቲሲዝም ጋር አገናኝቶ ሲክድና አጠራጣሪ አድርጎ ሲመለከት አንድም ጊዜ አልታየም፡፡ ስለ ቴክስቹዋል ክሪቲሲዝም እንነጋገር ከተባለ ራሱን በቻለ ርዕስ መነጋገር ይቻላል፤ በዚያውም በቶፕካፒና በሰመርቃንድ ቁርአኖች መካከል ስለሚገኙት ከ 2000 በላይ ስለሆኑት ልዩነቶች፣ በሰነዓ የቁርአን ማኑስክሪፕቶች ውስጥ ስለሚገኙት ስርዝ ድልዞች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰራጨው የአረብኛ ቁርአን የሐፍስ ቅጂ ስለመሆኑና ሐፍስ ደግሞ ሐሰተኛ ሰው በመሆኑ ምክንያት እርሱ የዘገባቸው ሐዲሶች ተቀባይነት ስለማጣታቸው፣ በዚህ ዘመን በዓለም ላይ ከ26 በላይ የአረብኛ ቁርአኖች ስለመኖራቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ ልዩነቶችን ስለማሳየታቸው፣ ወዘተ. ታብራራልናለህ፡፡ ኦሪጅናሉም ቁርአን ከኡሥማን የማቃጠል ዘመቻ ተርፎ እንደሆን ታረጋግጥልናለህ፡፡ የማይገናኝ ነገር በማገናኘት ማምታታት ለመግባባት ስለማይጠቅመን እንዲህ ያለ አካሄድ ብትተው ጥሩ ነው፡፡
————
{{{{{ነጥብ አንድ “የቤተ መቅደስም መጋረጃ”
የሉቃስ ዘጋቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ ይተርካል፦
ሉቃስ 23፥45-46 “የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ”። ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
የማቴዎስ ዘገቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ ይተርካል፦
ማቴዎስ 27፥ 50-51 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ “የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ”፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ የሚተርክልን የሉቃስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ የሚተርክልን የማቴዎስ ዘጋቢ?}}}}}
————-
#መልስ
አሁን እንዲህ ያለ ጥያቄ አንድን ታሪካዊ ክስተት ለማስተባበል የሚቀርብ ነው? ሲጀመር እነዚህ ነገሮች ሁሉ የተከናወኑት በአንድ ጊዜ (Simultaneously) በመሆኑ በየትኛውም ቅደም ተከተል ብትጽፋቸው ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተቀደደው ኢየሱስ ነፍሱን በሰጠበት በዚያው ቅፅበት ነበር፡፡ ሙግትህ ሚዛን አይደፋም፡፡ ቅደም ተከተል ሊያሳስብህ የሚገባው እንዲህ ፈጣን የሆኑ ክስተቶች በተስተናገዱበት ሁኔታ ሳይሆን ክስተቶቹን በቅደም ተከተላቸው መሠረት ማየት በአጠቃላይ ታሪካዊ ሒደቱ ተዓማኒነት ላይ ተፅዕኖ በሚያመጣበት ሁኔታ ነው፡፡ ትርጉም ያለው የጊዜ ልዩነት (significant time gap) በሌለበትና የክስተቶቹ ቅደም ተከተል በአጠቃላይ ታሪኩ ተዓማኒነት ላይ ተፅዕኖን በማያመጣበት ሁኔታ በአጉሊ መነፅር ግጭትን መፈለግ ተቀባይነት የለውም፡፡
————
{{{{{ነጥብ ሁለት “በሰቀሉትም ጊዜ”
ቅድሚያ የአራቱ ወንጌላት ተራኪዎች ጊዜን የሚቆጥሩት በዕብራውያን አቆጣጠር ብቻ መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው፤ የሮማውያን አቆጣጠር አንዳንዶች ይጠቀሙ ነበር የሚለው ቅጥፈት የታሪክ፣ የአውድና የባህል ማስረጃ የለውም፤ ይህ ቅጥፈት ግጭትን ለመደበቅ ሆን ብሎ ግምታዊ ነው፤}}}}}
———
#መልስ
ሮማውያን በዚያን ዘመን ከአይሁድ የተለየ የሰዓት አቆጣጠር እንደነበራቸው የታወቀ ነው፤ ይህ የመጀመርያው ክፍለ ዘመን ሮማዊ የታሪክ ጸሐፊ በነበረው በአረጋዊው ፕሊኒ ሳይቀር ተዘግቧል (Pliny the Elder, Natural History 2:77)፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ጽፎ የነበረው ከሮማውያን ዋነኛ ማዕከላት መካከል አንዷ በነበረችው በኤፌሶን ከተማ ከሆነ የሮማውያንን አቆጣጠር የማይጠቀምበት ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? በወንጌሉ ውስጥስ የሮማውያንን አቆጣጠር መጠቀሙን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ካሉ የክርስቶስን ስቅለት በተመለከተ የሮማውያንን አቆጣጠር አልተጠቀመም የሚያስብል ምን ምክንያት ይኖራል?
———
{{{{{ለምሳሌ ማርቆስ የዕብራዊያን አቆጣጠሩ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለበት በዕብራውያን 3 ሰአት ነው ይለናል፦
ማርቆስ 15፥25 “”በሰቀሉትም ጊዜ” “”ሦስት ሰዓት”” ነበረ።
ማርቆስ 15፥33 “ስድስት ሰዓትም”” በሆነ ጊዜ፥ እስከ “”ዘጠኝ ሰዓት”” በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።