ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ኩረጃ ሱሱ የሕያ በማስረጃ ከተጋለጠ በኋላ “አልኮረጅኩም” የሚለውን ክህደቱን ወደ ጎን በማድረግ ሌላ ዘዴ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ እርሱም እኛን ወደ ራሱ ደረጃ ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ከአንሰሪንግ ኢስላም ድረገፅ ላይ የወሰዳቸውን ሐሳቦች በኛ ገፅ ላይ ከሚገኙት ጋር መሳ ለመሳ በማቅረብ “እኔ ብቻ ሳልሆን እናንተም ኮርጃችኋል” ዓይነት ማስተባበያ አቅርቧል፡፡ ጥቂት ነገር ልበል፡-

እስልምናንና ክርስትናን በተመለከተ ከኛ በፊት ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ስለዚህ የሐሳብ መመሳሰል መኖሩ ወይንም የሌሎች ሰዎችን ሥራዎች እንደ መነሻ መውሰዳችን አያስገርምም፤ በኩረጃም አያስከስስም፡፡ የሕያ ከዚህ ቀደም በሌሎች የተባለውን በራሱ መንገድ አቅርቦ ቢሆን ኖሮ ማንም ግድ ባልሰጠው ነበር፡፡ ሌላው ይቅርና በኢንተርኔት ላይ ብቻ ተወስኖ የሌሎች ሰዎችን ሥራዎች ቃል በቃል ተርጉሞ ለአንባቢያን ጥቅም በቅንነት ቢያቀርብ ኖሮ በኩረጃ ባልከሰስነው ነበር፡፡ ሌሎች ሙስሊሞችም እኮ ከእነርሱ በፊት የተሠሩ በእንግሊዘኛ የምናውቃቸውን ሥራዎች በአገርኛ እያስነበቡን ነው፡፡ ምናልባት መልስ ስንሰጥ “ከዚህ ቦታ ነው የወሰዳችሁት” የሚል ጥቆማ እንሰጥ እንደሆን እንጂ ከእነርሱ ጋር እንዲህ ያለ እሰጥ አገባ ውስጥ አልገባንም፡፡ ይህንን ልጅ በጠንካራ ቃላት እንድንገስፅ ምክንያት የሆኑን ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ፡- የመጀመርያው ምክንያታችን የሕያ የሰው ሥራ ቃል በቃል ገልብጦ ከተረጎመ በኋላ ምንጭ ሳይጠቅስ ለንግድ ሲል በመጽሐፍ አሳትሞ ለሽያጭ ማቅረቡ ነው፡፡ እስከ አሁን ሁለት መጻሕፍትን ያሳተመ ሲሆን በሁለቱም መጻሕፍት ውስጥ ምንም ዓይነት ዋቢ መጽሐፍ አልተጠቀሰም፡፡ ይሄ ሌብነት ነው፡፡ ሌላው ምክንያት መጽሐፉ የተኮረጀ መሆኑ በግልፅ እየታየ ይዘቱን በግል ጥናት ያገኛው እንደሆነ በማስመሰል መናገሩ ነው፡፡ በሌላ ጽሑፋችን እንዳልነው በተለይም የቁርአን ግጭቶችን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ከኛ በፊት የተነሱ በመሆናቸው የሌሎች ወገኖች ጽሑፎች መነሻ ቢሆኑንም በራሳችን አባባል ለማስቀመጥ ሞክረናል፡፡ እኛ እንደ የሕያ የሰው ሥራ መቶ በመቶ ገልብጠን ቃል በቃል በመተርጎም “በግል ጥናት ያገኘነው” ከሚል መግለጫ ጋር በመጽሐፍ አሳትመን ለሽያጭ አላቀረብንም፡፡ በግል ጥናቶቻችን የተማርናቸውንም ሆነ ከሌሎች ሰዎች የተማርናቸውን ጉዳዮች ለወገኖች ጥቅም ስንል የማንንም የቅጂ መብት በማይነካ መንገድ በራሳችን አቀራረብ በነፃ እናስነብባለን፡፡ ምንጭ መጥቀስም ወሳኝ ሆኖ ሲገኝ ምሑራዊ ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ እንጠቅሳለን፡፡ የሰው ሥራ መቶ በመቶ ገልብጦ፣ ቃል በቃል ተርጉሞ፣ አንድ ምንጭ እንኳ ሳይጠቅስ “በግል ጥናት ያገኘሁት ነው” የሚል መግለጫ በመግቢያው ላይ አክሎ ለሽያጭ ገበያ ላይ ያወጣ እንደ የሕያ ያለ ሰው እኛን የመተቸትና በኛ ደረጃ ቆሞ የመናገር የሞራል ብቃት የለውም፡፡ ስለዚህ ለየሕያ ያለን ምላሽ እኛ እንዳንተ የሰው ሥራ፣ ያለ ደራሲው ፈቃድ፣ ቃል በቃል ተርጉመን፣ “በግል ጥናት የደረስንበት” የሚል መግለጫ በመግቢያው ላይ አክለን፣ ለገንዘብ ትርፍ ስንል በመጽሐፍ አሳትመን ለሽያጭ ገበያ ላይ ያቀረብን ለት ተመልሰህ ብትመጣና ብትወቅሰን ልንሰማህ እንችላለን፤ እስከዚያው ግን ስለማንመጣጠን የሚመጥንህን ፈልግና ተነጋገሩ የሚል ነው፡፡
------
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሌላው አስቂኝ ጉዳይ በአረብኛ “ኽ” የሚል ድምፅ ያላትን ፊደል “ክ” ብላችሁ ጽፋችኋል በማለት አቧራ ማንሳቱ ነው፡፡ ምን ብሎ እንደጻፈ ተመልከቱማ፡- ///በእስልምና ስለ መሻር የሚያወራው ናስኽ ወል መንሱኽ እንጅ ናሲክ ወል መንሱክ አይባልም። እንዲህ አይነት ስህተቶች የሚፈጠሩት ብቸኛ የመረጃ ምንጫቸው የእንግሊዝኛ ድህረገጾች በመሆናቸው ምክንያት ነው።///
አይ የሕያ ሰው በባዕድ ቋንቋ ይቅርና በገዛ ቋንቋው እንኳ ስህተቶችን ሊሠራ ይችላል፡፡ አንተስ ድረ ገጽን “ድህረገጽ” ብለህ እየጻፍክ አዲስ አማርኛ እያስነበብከንም አይደል? “ድረ/ ድር” (Web) ገፅ (Site) ለማለት ነው፡፡ “ድህረገፅ” ብለህ ከጻፍከው ግን “ከገጽ በኋላ” የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ ይህ አቧራ ለማስነሳት ሰበብ የሚሆን ትልቅ ጉዳይ አይደለም፤ ማናችንም ከስህተትና ካለማወቅ የጸዳን አይደለምና፡፡ ባለፈውም ተመሳሳይ ነገር ብለህ ግብዝነትህን የሚገልጥ ምላሽ ሰጥቼህ ነበር፡፡ ደግሜ ልጥይቅህ! የአንድ ፊደል ስህተት እንዲህ ካንገበገበህ የገዛ ወገኖችህ ስለ ክርስትና በሚጽፉበት ጊዜ ተመሳሳይ ስህተቶችን መፈጸማቸውን እንዴት ትመለከታለህ? ለምሳሌ ያህል ዑመር አርሲ የተባለ ጸሐፊ “ታላቅ ምክር…” በሚለው መጽሐፉ ውስጥ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” እንደማለት ከእንግሊዘኛ በቀጥታ በመተርጎም “ጁዳስ እስካርዮት” ብሎ ጽፏል (ገፅ 45)፡፡ ሐሰን ታጁ ደግሞ “የሐመረ ተወሕዶን ቅጥፈት…” በሚለው መጽሐፉ ውስጥ ‹ኖስቲክ› የሚለውን ‹ግኖስቲክ› ብሎ ጽፏል (ገፅ 103)፡፡ ይባስ ብሎ ‹ኮዴክስ ሲናይቲከስ› የሚለውን ‹የሲያትል ጽሑፍ› ብሎታል (ገፅ 43)፡፡ ሰልማን ኮከብም “ንቁ” በሚለው ውትፍትፍ መጽሐፉ ውስጥ ጠርጡሊያኖስን በቀጥታ ከእንግሊዘኛ በመተርጎም “ቴርቱሊያን” ብሎታል (ገፅ 61)፡፡ መርቂያን የሚለውን “ማርኪዮን”፣ ኖስቲክን “ጊኖስቲክ”፣ ሰባልዮሳውያንን “ሴባሉሳውያን”፣ ወዘተ. ብሎ ጽፏል (ገፅ 64፣ 65)፡፡ ይኸው ወዳጅህ “ሆንትዮስ፣ ቶንትዮስ” እያለ በግሪክ ቋንቋ ውስጥ የሌሉ ቃላትን መፍጠሩንስ ስታስብ ምን ይሰማሃል? እብራይስጥና ግሪክን በጠቀሰ ቁጥር የትራንስሊትሬሽን ስህተቶችን የሚፈፅመው ጓደኛህን ወሒድንስ ምን ልትለው ነው? መሰል ስህተቶችን እንደ ዕውቀት ጉድለት ከቆጠርክ እነዚህ ወገኖችህ ተመሳሳይ ነገር መፈፀማቸውን ስታስተውል እኛን በአንዲት ፊደል ምክንያት እንደዘለፍከን ትዘልፋቸዋለህ ወይንስ “አስቶጉፉሩላህ!” ብለህ ታልፋቸዋለህ? ያንተ ጉድ አያልቅ!
በመጨረሻም እስኪ በዚያ በብዙ ስህተቶች በታመሰው ድረ ገጽህ ላይ አንድ ኦሪጅናል የምትለው ሥራ ካለ ጠቁመን? እውነቴን ነው አሁን ደርሰህ በጣም እያሳዘንከኝ ነው!
----
ዳንኤል
1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የደወል-ድምጽ.pdf
671.8 KB
ሙሐመድ ቁርአንን ጂብሪል ከተባለው መንፈስ ይቀበል የነበረው በደወል ድምፅ አምሳያ መሆኑንና የዲያብሎስም ድምፅ የደወል ድምፅ እንደሚመስል በእስላማዊ ሐዲሳት ውስጥ ተጽፏል፡፡ የእስልምናን ዋና መጻሕፍት በጥልቀት ከሚያውቁ ብርቅዬ ምሑራኖቻችን መካከል አንዱ የሆነው ወንድም ሳሒህ ኢማን ሙስሊም ሰባኪያን ይህንን እውነታ ለማስተባበል የሰጡትን “ምላሽ” ከንቱነት የሚያሳይ የማያወላዳ ማስረጃና ሙግት አቅርቧል፡፡ አንብቡት፤ ለሌሎችም አጋሩት፡፡
ሙሴና ሙሐመድ የማይመሳሰሉባቸው 50 ነጥቦች!
__________
ሙስሊም ወገኖች ስለ ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ተተነበየ ይናገራሉ፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች መካከል ዘዳግም 18፡18 ላይ የሚገኘው የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ የተናገረው ትንቢት ዋነኛው ነው፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፡-

እግዚአብሔር አለኝ ፡– የተናገሩት መልካም ነው፡፡ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደአንተ ያለ ነቢይ አስነሳላቸዋለሁ፡፡ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፡፡ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ፡፡”

ይህንን ጥቅስ ለሙሐመድ የተነገረ በማስመሰል የሚያቀርቡት ሙስሊም ወገኖች ቁጥር 15-16 ላይ የሚገኘውን “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል” የሚለውን ቃል ባላየ ያልፉታል፡፡ በዚህ ጥቅስ መሠረት “ከወንድሞችህ” የሚለው 12ቱን ነገደ እስራኤልን የተመለከተ እንጂ የእስራኤል የአጎት ልጆች (የእስማኤል ልጆች) እንደሆኑ የተነገረላቸውን አረቦችን የሚጠቅስ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ጥቅሱ “ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ” በማለት ለእስራኤላውያን ብቻ የተነገረ መሆኑን አስረግጦ ሳለ ስለ ሌላ ሕዝብ የተነገረ እንደሆነ በማስመሰል መተርጎም አላዋቂነት አለበለዚያም አታላይነት ነው፤ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለእውነት ግድ የሚለውና እውነተኛውን አምላክ እንደሚከተል የሚያምን ሰው እንዲህ ላለ ሃቀኝነት ለራቀው ሙግት ቦታ አይሰጥም፡፡

ይህንን ትንቢት ለሙሐመድ የተነገረ በማስመሰል የሚያቀርቡት እስላማዊ ጽሑፎች ሙሴና ሙሐመድ እንደሚመሳሰሉ ለማሳየት አንዳንድ “መመሳሰሎችን” ይጠቅሳሉ፡፡ ሆኖም የሚጠቅሷቸው ነጥቦች ማንኛውም ተራ ሰው ከሙሴ ጋር ሊመሳሰልባቸው የሚችላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሁለቱም በተፈጥሯዊ መንገድ ተወልደዋል፣ ሁለቱም አግብተዋል፣ ሁለቱም መሪዎች ነበሩ፣ ሁለቱም ሞተዋል፣ ወዘተ. የሚሉ ተራ መመሳሰሎችን ይጠቅሳሉ፡፡ አንዳንድ ጸሐፊያን እንዲያውም የሁለቱም ስም M በሚል የእንግሊዘኛ ፊደል የሚጀምር በመሆኑ ይመሳሰላሉ ብለው እስከ መሟገት ወርደዋል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሙሴና ሙሐመድ ከሚመሳሰሉባቸው ነጥቦች ይልቅ የሚለያዩባቸው ነጥቦች በእጅጉ ይበዛሉ፡፡ ልዩነቶቹ እጅግ በርካታ ቢሆኑም በዚህ ጽሑፍ 50ዎቹን ከማስረጃ ጋር እንጠቅሳለን፡፡
_______

1. ሙሴ ከሌዊ ነገድ የሆነ እስራኤላዊ ነበር (ዘጸአት 2፡1-2)፤ የሙሐመድ የዘር ሐረግ “ቁረይሽ” ከተሰኘው የአረብ ጎሣ ይመዘዛል (ሱራ41:44፣ Sahih Bukhari 4፡698)፡፡

2. ሙሴ ወገኖቹ እስራኤላውያን በባርነት ምድር ሳሉ ነበር የተወለደው (ዘጸ. 1፡9-14)፤ በሙሐመድ ዘመን አረቦች ነፃ ሕዝቦች ነበሩ፡፡

3. ሙሴ በልጅነቱ ከሞት አዋጅ በመለኮታዊ እርዳታ ተርፏል (ዘጸ. 1፡15-16፣ 2፡2-10)፤ ሙሐመድ እንዲህ ያለ ታሪክ አልነበረውም፡፡

4. የፈርዖን ልጅ ሙሴን ታጠባው ዘንድ ለወላጅ እናቱ ሰጠችው (ዘጸአት 2፡7-8)፡፡ የሙሐመድ ወላጅ እናት ራሷ ከማጥባት ይልቅ ሐሊማ ለተባለች ሴት እንድታጠባው ሰጠችው (Ibn Ishaq, Sirat Rasulullah, p.72)፡፡

5. ሙሴ በምድረ ግብፅ ኖሯል (ዘጸአት 2፡10)፤ ሙሐመድ ግብፅን አልረገጠም፡፡

6. ሙሴ በልጅነቱ አጠራጣሪ ወይም አነጋጋሪ መንፈሳዊ ልምምድ አልነበረውም፤ ሙሐመድ በልጅነቱ ወድቆ በመንፈራገጡ ምክንያት ሐሊማ ጋኔን እንዳደረበት ስላሰበች ለእናቱ መልሳዋለች (Ibn Ishaq, Sirat Rasulullah, p. 72)፡፡

7. ሙሴ ጣዖታትን አላመለከም፤ ሙሐመድ በልጅነቱ ለጣዖት ሰውቷል (Hisham Ibn Al-Kalbi, The Book of Idols (Kitab al-Asnam), pp. 17-18; A. Guillaume, Islam, pp. 26-27)፡፡

8. ሙሴ የግብፅን ዕውቀት የተማረ ማንበብና መጻፍ የሚችል ምሑር ነበር (ሐዋ. 7፡22፣ ዘጸ. 24፡4፣ ሌዋ. 1፡1፣ 4፡1፣ 5፡14፣ ዘኁ. 1፡1፣ 33፣2፣ ዘዳ. 1፡1፣ 4፡44፣ 29፡1)፤ ሙሐመድ ማንበብና መጻፍ የማይችል መሃይም ነበር (ሱራ 7:157-158፣ Sahih Muslim Vol. 1, p. 97)፡፡

9. ሙሴ እግዚአብሔር የሰጠውን ሕግ በገዛ እጁ ጻፈ (ዘጸ. 24፡4፣ ሌዋ. 1፡1፣ 4፡1፣ 5፡14፣ ዘኁ. 1፡1፣ 33፣2፣ ዘዳ. 1፡1፣ 4፡44፣ 29፡1)፤ ሙሐመድ መሃይም ስለነበር ጸሐፊዎች ነበሩት፤ አንዳንዴም የገዛ ሐሳባቸውን እየጨመሩ ይጽፉ ነበር (Al-Wahidi Al-Naysaboori. Asbaab Al-Nuzool; p. 126 Beirut’s Cultural Libary Edition “Tub’at Al-Maktabah Al-thakafiyyah Beirut”)፡፡

10. ሙሴ አሮንና ማርያም የተሰኙ ወንድምና እህት ነበሩት (ዘኁልቁ 26፡59)፤ ሙሐመድ ብቸኛው የአብደላና የአሚና ልጅ ነበር (Ibn Sa’d. Kitab al-Tabaqat al-Kabir Volume I Parts I & II, p. 107)፡፡

11. ሙሴ እግዚአብሔርን ከሚያውቅ እስራኤላዊ ቤተሰብ ነበር የተወለደው (ዘጸአት 2፡1-3፣ ዕብራውያን 11፡23)፤ የሙሐመድ ወላጆችና ዘሮች ጣዖታውያን ነበሩ፡፡ አባቱና እናቱም ገሃነም ውስጥ መሆናቸውን ሙሐመድ ተናግሯል (Sahih Muslim Vol. 2, Book 4, Hadith 2130)

12. የሙሴ ወንድ ልጆች ጌርሳምና ዓልአዛር ለአቅመ አዳም ደርሰው አግብተው ወልደዋል (1ዜና 23፡15-17)፤ ሙሐመድ ሦስት ወንድ ልጆች የወለደ ሲሆን (ከኸዲጃ የወለዳቸው አልቃሲምና አብዱላህ፣ ከግብፃዊቷ ባርያው የወለደው ኢብራሂም) ሦስቱም በህፃንነታቸው ሞተዋል፡፡ (Ibn Ishaq, Sirat Rasulullah, p.83)

13. ሙሴ ለአገልግሎት የተጠራው በ 80 ዓመቱ ነበር (ዘጸአት 7፡7)፤ ሙሐመድ ግን ጂብሪል ታየኝ ያለው በ 40 ዓመቱ ነበር (Sahih Bukhari 5፡242)፡፡

14. ሙሴ ነቢይነቱን ለማረጋገጥ የሚስቱ ማረጋገጫ አላስፈለገውም (ዘጸአት 4፡1-18)፤ ሙሐመድ ነቢይ መሆኑን ያሳመነችው ሚስቱ ኸዲጃ ናት (The History of Tabari, translated by W. Montgomery Watt, vol. 6, p. 72)፡፡

15. ሙሴ ነቢይነቱን ያረጋገጠው እግዚአብሔር ተዓምራዊ በሆነ መንገድ ስለተገለጠለት ነው (ዘጸአት ም. 3-4)፤ ሙሐመድ ነቢይነቱን ያወቀው ኸዲጃ ቀሚሷን ገልጣ ሸፍናው ነው (Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah”, The Life of Muhammad, translated by A. Guillaume, p. 107)፡፡

16. ሙሴ እግዚአብሔር ሲገለጥለት የተገለጠለት እግዚአብሔር መሆኑን አመነ እንጂ “ሰይጣን ታየኝ” አላለም (ዘጸአት ም. 3-4)፤ ሙሐመድ የተገለጠለት አካል ሰይጣን ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት አድሮበት ነበር (Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah,” The Life of Muhammad translated by A. Guillaume, p. 106)፡፡

17. እግዚአብሔር ለሙሴ ሲገለጥ በንግግርና በምልክት አሳመነው እንጂ አላስገደደውም (ዘጸአት ም. 3-4)፤ “ጂብሪል” ሙሐመድን ከመሬት ጋር አጣብቆ በማስገደድ ቁርአንን አስነብቦታል (Sahih Muslim Vol. 1, p. 97)፡፡

18. ሙሴ 40 ቀን በሲና ተራራ ላይ ከቆየ በኋላ ፊቱ አበራ (ዘጸአት 34፡30)፤ ሙሐመድ በሒራ ዋሻ ውስጥ ከደረሰበት ሁኔታ የተነሳ በፍርሃትና በመርበትበት ውስጥ ሆኖ ወደ
ሚስቱ ተመለሰ (Ibn Sad, Kitab al-Tabaqat al-Kabir, Vol. 1, p. 225)፡፡

19. ሙሴ ብዙ ተዓምራትን አድርጓል (ዘጸ. ም. 7፣ 8፣ 14፣ 17፣ ሱራ 2፡50፣ ሱራ 2፡57)፤ ሙሐመድ አንድም ተዓምር አላደረገም (ሱራ 28:48፣ ሱራ 6:109፣ ሱራ 13:27፣ ሱራ 17:59፣ ሱራ 13:7)፡፡ በሐዲስ መጻሕፍት ሙሐመድ ተዓምራትን እንዳደረገ ቢዘገብም ከቁርአን ጋር ስለሚጋጩ ከክፍለ ዘመናት በኋላ የተጻፉ የፈጠራ ታሪኮች መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡

20. ሙሴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሯል (ዘጸ. 33፡11፣ ሱራ 4፡164)፤ ሙሐመድ አልተነጋገረም (ሱራ 42፡51፣ Bukhari Vol. 6, Book 60, No. 378)፡፡ መገለጥንም ይቀበል የነበረው በተዘዋዋሪ በጅብሪል አማካይነት ነበር (ሱራ 2፡97)፡፡

21. ሙሴ በጣም ትሁትና ለግል ጥቅሙ የማይከራከር ሰው ነበር (ዘኁልቁ 12፡3)፤ ሙሐመድ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግና ያስቀየሙትን ሰዎች በነፍሰ ገዳዮች የሚያስገድል ቂመኛ ሰው ነበር (ሱራ 33፡57፣ Bukhari vol 5 No. 369; Ibn Sa
d, Kitab al-Tabaqat al-Kabir, Vol. 2, p. 31; Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah,” The Life of Muhammad translated by A. Guillaume, pp. 675, 676)፡፡

22. ሙሴ በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ሚስት አላገባም፣ በጋብቻውም ላይ አላመነዘረም፤ ሙሐመድ መድብለ ጋብቻን ፈፅሟል(Bukhari, volume 7, No. 142)፣ በጋብቻው ላይም አመንዝሯል (Kitab al-Tabaqat al-Kabir, p. 151)፡፡

23. ሙሴ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች ህፃን አላገባም፤ ሙሐመድ አይሻ የ 6 ዓመት ህፃን ሳለች በማጨት በ 9 ዓመቷ አብሯት ተኝቷል (Sahih Al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 234; Volume 5, Book 58, Number 236; Volume 9, Book 87, Number 140; see also Number 139; Volume 7, Book 62, Number 64; see also Numbers 65 and 88; Sahih Muslim, Book 008, Number 3309; see also 3310; Book 008, Number 3311; Sunan Abu Dawud, Number 2116; Book 41, Number 4915; Book 13, Number 2380)፡፡ ሙሐመድ በዳዴ የሚሄዱትን ህፃናት እንኳ ሳይቀር ለጋብቻ ይመኝ እንደነበር በእስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ ማንበብ በእጅጉ አስደንጋጭ ነው፡፡ “የአባስ ልጅ ኡም ሐቢባ ጡት በመጥባት እድሜ ላይ በነበረች ጊዜ በፊታቸው በዳዴ ስትሄድ ነቢዩ ተመልክተዋት እንዲህ አሉ፡ ‹እኔ በሕይወት እያለሁ የምታድግ ከሆነ አገባታለሁ፡፡›” (Musnad Ahmed, Number 25636)

24. ሙሴ የማደጎ ልጁን ሚስት ቀምቶ አላገባም፤ ሙሐመድ የማደጎ ልጁ የዘይድን ሚስት ዘይነብን አግብቷል (ሱራ 33:37፣ Sahih Muslim Book 8, Number 3330)፡፡

25. ሙሴ እስራኤላውያንን ወደ ተስፋይቱ ምድር መርቷል (ኦሪት ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቁ፣ ዘዳግም)፤ ሙሐመድ እስራኤላውያንን በሰይፍ ጨፍጭፏል፣ ዘርፏል፣ ባርያ አድርጓል፣ ከአገር አባሯል ((Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah,” The Life of Muhammad translated by A. Guillaume, pp. 363, 437, 461, 510)፡፡ በመጨረሻው ዘመንም ሙስሊሞች አይሁድን በሙሉ እንደሚጨፈጭፉ ተናግሯል (Sahih al-Bukhari Volume 4, Book 52, Number 177; Sahih Muslim, Book 041, Number 6981)፡፡

26. ሙሴ ጋኔን እንዳደረበት አስቦ አያውቅም፤ ሙሐመድ ጋኔን እንዳደረበት ተናግሯል (Sirat Rasulallah p. 106, 121, 130, 136)፡፡

27. ሙሴ ራሱን ለመግደል ሞክሮ አያውቅም፤ ሙሐመድ ከተራራ ላይ ራሱን ወርውሮ ለመግደል ብዙ ጊዜ ሞክሯል (History of Tabari, translated by W. Montgomery Watt, vol. 6, p. 69-70; Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah,” The Life of Muhammad, translated by A. Guillaume, p. 106)፡፡

28. ሙሴ እስከ መጨረሻው ድረስ ጤናማ አእምሮና አስተሳሰብ ነበረው (ዘዳግም 34፡1-7)፤ ሙሐመድ ለሞት ሲቃረብ የአእምሮ መታወክ ደርሶበት ነበር (Sahih al-Bukhari Volume 2, Book 23, Number 471)፡፡

29. ሙሴ ከሰይጣን የሆነ ቃል አልተናገረም፤ ሙሐመድ ሰይጣናዊ ጥቅሶችን ተናግሯል (History of Tabari, vol. 6, pp. 108-110)፡፡

30. ሙሴ በያሕዌ ስም እንጂ በሌላ አምላክ ስም አልተናገረም (ዘዳግም 18፡20)፤ ሙሐመድ በአል-ላት፣ አል-ኡዛና መናት ስም ተናግሯል (History of Tabari, vol. 6, pp. 108-110)፡፡

31. ሙሴ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ተናግሮ አያውቅም (ዘዳግም 18፡20)፤ ሙሐመድ በአምላኩ ስም ሐሰትን መናገሩንና አምላኩ ያልተናገረውን የተናገረ በማስመሰል እንደተናገረ ተናዟል (Al-Tabari, The History of Al-Tabari, vol. vi, p. 111; Ibn Sa’d, Kitab Al-Tabaqat Al-Kabir, vol. 1, p. 237)፡፡

32. ሙሴ አስማት ሊሠራበት አልቻለም (ዘኁልቁ 23፡23)፤ ሙሐመድ በአስማት ቁጥጥር ስር ሆኖ ለአንድ ዓመት ያህል ሲሠቃይ ነበር (Al-Bukhari, vol. 7, no. 660; Al-Bukhari, vol. 7, no. 658)፡፡

33. የሙሴ አምላክ ለሕዝቡ አባት ነው (ዘዳግም 32፡6)፤ የሙሐመድ አምላክ ለማንም አባት ሆኖ አያውቅም (ሱራ 5:18)፡፡

34. ሙሴ የገዛ መገለጡን ሽሮ አያውቅም፤ ሙሐመድ መገለጦቹን በተደጋጋሚ ይሽር ነበር (ሱራ 13፡39፣ 16፡101፣ 2፡106፣ 17፡86)፡፡

35. ሙሴ የግል ብቀላን ከልክሏል (ዘሌዋውያን 19፡18)፤ ሙሐመድ ግን ይቅርታ ተመራጭ መሆኑን ቢናገርም ብቀላን ፈቅዷል (ሱራ 16፡126)፣ እራሱም ተበቃይ ነበር (Bukhari vol 5 No. 369; Ibn Sa`d, Kitab al-Tabaqat al-Kabir, Vol. 2, p. 31; Ibn Ishaq’s “Sirat Rasul Allah,” The Life of Muhammad translated by A. Guillaume, pp. 675, 676)፡፡

36. ሙሴ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ላይ አንድም ጊዜ አልተሸነፈም፤ ሙሐመድ በኡሁድ ጦርነት ላይ ክፉኛ ተሸንፏል፡፡ በዚህ ጦርነት ላይ አጎቱ ሐምዛ የሞተ ሲሆን ሙሐመድ ራሱ ከንፈሩ ተሰንጥቆ የፊት ጥርሶቹ ረግፈዋል፡፡ የሙሐመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሁለት ጥርሶች ዛሬ በኢስታንቡል ሙዚየም ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ (Paul Fregosi. Jihad in the West, Muslim Conquest from 7th to 21st Centuries; 1998, p. 53)

37. ሙሴ ወንድ የሴት ልብስ እንዳይለብስ ከልክሏል (ዘዳግም 22፡5)፤ ሙሐመድ የሚስቱ የአይሻን ቀሚስ ሲለብስ ነበር (Sahih al-Bukhari Number 2442; 2393; 3941; Sahih Muslim, Book 031, Number 5984)፡፡

38. ሙሴ የሰው ሚስት መመኘትን ከልክሏል (ዘጸአት 20፡17)፤ ሙሐመድ የሰው ሚስት ከመመኘት አልፎ ቀምቶ
ዛሬ እናን እስልምናን እየተከተላችሁ ያላችሁት ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ መሆኑን አረጋግጣችሁ ነው ወይንስ በጭፍን? ሰይፍ ፈርታችሁ ነው ወይንስ በገዛ ፈቃዳችሁ? ከእስልምና በመውጣታችሁ የሚደርስባችሁን መገለልና ጊዜያዊ ፈተና ፈርታችሁ ነው ወይንስ የዘላለምን ሕይወት አገኛለሁ ብላችሁ? ከሚመጣው ፍርድ ያድናችሁ ዘንድ ሙሐመድ ብቁ ነውን? እስኪ ሕይወቱን ተመልከቱና ለገዛ ልቦናችሁ እውነትን ተናገሩ! እንደ ሙሐመድ ኃጢአትና ክፋት ያልተገኘበትን አንድ አዳኝ እንጠቁማችሁ፡፡ ስሙ ኢየሱስ ይባላል! በእብራይስጥ ዬሹዋ መሺያኽ ብለው ይጠሩታል፣ ዓረብ ክርስቲያኖች የሱዋ አል-መሲህ ይሉታል፣ እናንተ ደግሞ አል-መሲህ ዒሳ ትሉታላችሁ፡፡ እርሱ ፍፁም ጻድቅ፣ ንፁህና ኃጢአት የሌለበት መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ እርሱ የሰው ልጆችን ከኃጢአታቸው ለማዳን ከሰማይ የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ እንዲህ ይላችኋል፡-

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴዎስ 11፡28)

ይህ ቅዱስ ጌታ እናንተ በገዛ ሥራችሁ ልታገኙት ያልቻላችሁትን የዘላለምን ሕይወት በነፃ ይሰጣችኋል፡፡ ኃጢአትን ድል የምትነሱበትንም ቅዱሱን መንፈስ ይልክላችኋል፡፡ ዛሬውኑ በስሙ በማመን ከዘላለም ጥፋት ትድኑ ዘንድ ጥሪን እናቀርብላችኋለን! እግዚአብሔር አምላክ ይርዳችሁ!
አግብቷል (ሱራ 33፡37፣ Sahih Muslim Book 8, Number 3330)፡፡

39. ሙሴ የጦር ምርኮኛ ሴቶችን መድፈርን ከልክሏል (ዘዳግም 21፡10-14)፤ ሙሐመድ ፈቅዷል፣ ለዚያውም የምርኮኞች ባሎች በሕይወት እያሉ! (Sahih Al-Bukhari 62:137; Bukhari 34:432; Abu Dawud 2150; Sahih Muslim volume 2, No. 3371; ሱራ 70፡29-30፣ 23፡5-6)፡፡

39. ሙሴ ለኃጢአት ስርየት የመሥዋዕት ሥርዓትን ሲፈፅም ነበር (ኦሪት ዘሌዋውያን በሙሉ)፤ ሙሐመድ ለኃጢአት ሥርየት ስለሚሆን መሥዋዕት አላስተማረም፡፡ በሙሴ ሕግ ለመብል እንኳ የተከለከለውን ግመልን ሲሠዋ የነበረ ሲሆን ከሙሴ የመሥዋዕት ትርጉም ጋር ጭራሽ አይገናኝም፤ ከአረብ ጣዖታውያን የተኮረጀ ነው (ሱራ 22፡32-36፣ 2፡196)፡፡

40. ሙሐመድ ከሙሴ መጽሐፍ ሲጠቅስ የገዛ ቃሉን ጨምሮ ጠቅሷል፤ ይህም የሙሴን መጽሐፍ አለማወቁን ያሳያል፡- “በነርሱም ላይ በውስጧ ነፍስ በነፍስ፣ ዓይንም በአይን፣ አፍንጫም በአፍንጫ፣ ጆሮም በጆሮ፣ ጥርስም በጥርስ (ይያዛል)፣ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ማለትን ጻፍን” (ሱራ 5፡45)፡፡ ነገር ግን ትዕዛዙ በተሰጠባቸው ቦታዎች ሁሉ “አፍንጫም በአፍንጫ፣ ጆሮም በጆሮ” የሚል የለም (ዘጸአት 21፡24፣ ዘሌዋውያን 24፡20፣ ዘዳግም 19፡21)፡፡

41. ሙሴ የግመል ሥጋ መብላትን ከልክሏል (ዘሌዋውያን11:1-4፣ ዘዳግም 14:3-7)፤ ሙሐመድ የግመል ሥጋ መብላትን ብቻ ሳይሆን የግመል ሽንት መጠጣትንም ፈቅዷል (Sahih Bukhari 8፡796; ሱራ 22:36)፡፡

42. ሙሴ ስለ ንፅህና አጠባበቅ ጥሩ ትምህርቶችን አስተምሯል (ሌዋውያን 11፡25፣ 13:47–58፣ 14፡8፣ 15፡5-13፣ ዘዳግም 23:12–14፣ )፤ ሙሐመድ ጤናን ለአደጋ የሚያጋልጡ ትምሕርቶችን አስተምሯል፤ ለምሳሌ፡- ዝንብ በመጠጫ ውስጥ ከወደቀች ወደ ውስጥ እንድትጠልቅ ማድረግ በሽታን እንደሚከላከልና የሞቱ እንስሳት የሚጣሉበትንና ሴቶች የወር አበባ ጨርቅ የሚያጥቡበትን ውኀ መጠጣት ጤናን እንደማይጎዳ ተናግሯል (Sahih Al-Bukhari Volume 4, Book 54, Number 537; Sunan Abu Dawud 67; Sunan Ibn Majah 520; Sunan Ibn Majah 521)፡፡

43. ሙሴ ለአምልኮ አገልግሎት የሚውል ምንም ዓይነት ድንጋይ ማቆምን ከልክሏል (ዘጸአት 26፡1፣ ዘዳግም 16፡22)፤ ሙሐመድ አረብ ጣዖታውያን ሲያመልኩት የነበሩትን ጥቁር ድንጋይ ስሟል፣ ተሻሽቷል፣ ተከታዮቹ በቀን አምስቴ ወደ እርሱ ዞረው እንዲሰግዱ አዟል (Sahih al-Bukhari, Volume 2, Book 26, Number 673; ሱራ 2፡150)፡፡

44. የሙሴ አምላክ ውሸትና ማታለልን የማያውቅ ቅዱስ ነው (ዘኁልቁ 23፡19)፤ የሙሐመድ አምላክ አታላይ ተብሎ ተጠርቷል፡- ሱራ 3፡54፡- “አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነዉ።” ومكروا ومكر الله والله خير الماكرين “ወአላሁ ኸይሩ አል-መክሪን” ማለት አላህ ከአታላዮች ሁሉ የበለጠ አታላይ ነው” ማለት ነው፡፡ Allah (is) the best (of) the cheaters/deceivers. ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው በርካታ የቁርአን አናቅፅ ይገኛሉ (ሱራ 7፡99፣ 8:30፣ 10:21፣ 13:42)፡፡ ነገር ግን የአማርኛ ቁርአን ተርጓሚዎች የተለያዩ ቃላትን በመተካትና በማዛባት ቢተረጉሙም ቀጥተኛው ትርጉም አላህ ከአታላዮች ወይም አጭበርባሪዎች ሁሉ የከፋው አታላይ ወይም አጭበርባሪ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ከአላህ 99ኙ ስሞች መካከል አንዱ “አል-መክር” ወይም “አታላዩ” የሚል ነው፡፡ ብዙ የአረብኛ ዲክሺነሪዎችም ቃሉን “አታላይ፣ አጭበርባሪ፣ ተንኮለኛ፣ ወዘተ.” በማለት ይተረጉማሉ፡፡

45. ሙሴ አንድም ጊዜ የግል ጥቅሙን ለማስከበር መገለጥ ተናግሮ አያውቅም፤ ሙሐመድ በመገለጥ ሽፋን የገዛ ጥቅሙን ሲያሳድድ ነበር (ሱራ 33:51፣ ሱራ 33:37፣ ሱራ 33:50፣ ሱራ 33:53፣ ሱራ 49:4)፡፡

46. ሙሴ ኢትዮጵያዊትን ሴት አግብቷል (ኦሪት ዘኍልቍ 12፡1)፤ ሙሐመድ ለኢትዮጵያውያን፣ ብሎም ለጥቁሮች ከፍተኛ ንቀት ነበረው፣ ባርያም አድርጓቸዋል (Sahih Muslim, Book 10, Number 3901; Sahih Bukhari, Volume 9, Book 91, Number 368)፡፡ ኢትዮጵያውያንን “ዘቢብ ጭንቅላት” ብሎ ተሳድቧል (Sahih al-Bukhari Book Number 89 Hadith Number 256)፡፡ ሰይጣንና ጥቁሮችን አመሳስሏል (Ibn Ishaq, Sirat Rasulallah, translated as, The Life of Muhammad by A. Guillaume, page 243)፡፡ ጥቁር ሴት የበሽታ ወረርሽኝ ምልክት መሆኗን ተናግሯል (Sahih Bukhari, Volume 9, Book 87, Number 161)፡፡ ለበለጠ መረጃ መሐመድ ለጥቁሮች የነበረው ንቀት የሚለውን ጽሑፍ ያንብቡ፡፡

47. ሙሴ በአካሉ ላይ ምንም ዓይነት እንከን እንዳልነበረው እስላማዊ ሐዲሳት ይናገራሉ (Sahih Al-Bukhari Volume 4, Book 55, Number 616; Volume 1, Book 5, Number 277) ፤ ሙሐመድ በጀርባው ላይ እባጭ ወይም ዕጢ ነበረበት፤ የቀደሙት ሙስሊሞች ይህንን የጤና ችግር “የነቢያት ማሕተም” አድርገው ተርጉመውታል (Sahih al-Bukhari Volume 1, Book 4, Number 189; Volume 7, Book 70, Number 574; Sahih Muslim Book 030, Number 5790)፡፡ ለበለጠ መረጃ የነቢይነት ማሕተም ወይንስ የጤና ችግር? በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ጽሑፍ ያንብቡ፡፡

48. ሙሴ ረጅም ዕድሜ ኖሮ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት ሞቷል፣ አስከሬኑም በመላእክት ይጠበቃል (ዘዳግም 34፣ ይሁዳ 1፡9)፤ ሙሐመድ መርዝ በልቶ ሞቷል፣ መቃብሩም በመዲና ከተማ ይገኛል (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 59, Number 713)፡፡

49. ሙሴ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚነሳ ተናግሯል (ዘዳግም 18፡18)፤

50. ሙሐመድ በአምስት ነገሮች ከነቢያት ሁሉ የተለየ መሆኑን ተናግሯል ስለዚህ በራሱ ቃል መሠረት ከሙሴ ጋር አይመሳሰልም (Sahih al-Bukhari Volume 1, Book 7, Number 331)፡፡

------------
ውድ ሙስሊሞች! ከነዚህ እውነታዎች አንፃር ሙሴን የሚመስለው ነቢይ ሙሐመድ መሆኑን ለመናገር የሚያስችል ምን ማስረጃ ማቅረብ ትችላላችሁ? ይህንን ዝርዝር ካነበባችሁ በኋላስ ኡስታዞቻችሁ በሚያቀርቡት ሙግት ላይ ያላችሁ መተማመን ምን ያህል ነው? በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ሰዎች እንኳ ሙሴና ሙሐመድ እንደማይመሳሰሉ ተገንዝበው ጥያቄን አንስተው እንደ ነበር በቁርአናችሁ ውስጥ ተጽፏል፡- ሱራ 28:48 “እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ «ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይስሰጠውም ኖሯልን» አሉ፡፡ «ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን የተረዳዱ ሁለት ድግምቶች ናቸው» አሉ፡፡ «እኛ በሁሉም ከሓዲዎች ነንም» አሉ፡፡”

ነቢያችሁ ሙሐመድ ተዓምራትን ማሳየት ባለመቻሉ ምክንያት የሙሴን ተዓምራት አስፈላጊነት አሳንሶ ለማሳየት ሲጣጣር ይታያል፡፡ ሙሴ ያንን ሁሉ ተዓምር ባያሳይ ኖሮ እስራኤላውያንን ከባርነት ነፃ ማውጣት ባልቻለ ነበር፡፡ ሙሐመድም የእውነተኛ ነቢያት ምልክቶችን ማሳየት ቢችል ኖሮ አረቦችን ለማስለም ሰይፍ መምዘዝ ባላስፈለገው ነበር፡፡
1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (ይሰማል? ሞትን አንድ ቀን ተጠጋኸው እኮ)
የወሂድ የቀድሞዎቹ ተረትና የሙግት ሐሳቡ ሲገመገም፡-

ወሂድም ይሁን ሌሎቹ በንጽጽር ላይ እንሠራለን የሚሉ ኢስላማዊ ግለሰቦች ኢስላምን በውሸታቸው የሚጠብቁት ስለሚመስላቸው ውሸትን እንደመጎናጸፊያ ላያቸው ላይ ተጎናጽፈውታል፡፡ ነቢዩም ቢሆኑ የኢስላም ጠባቂነታቸውን ያሳዩት የሚቃወሟቸውን በዘግናኝ ሁኔታ በመግደል እንጂ መለኮታዊ ምልእክተኛነታቸውን እንደቀደሙት ነቢያት በታማኝ ማስረጃ በማስረገጥ አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከገሃነም ማምለጥ ለሚፈልገው የዋህ ሕዝብ የእንቅፋት ድንጋይ መሆን እንጂ የሚያመጣው ለውጥ በፍጹም አይኖርም፤ ለራስም ቢሆን አይበጅም፡፡ ይህን ያልኩት እንዲሁ ሳይሆን ወሂድ "የቀድሞዎቹ ተረቶች" በሚል ርእስ ሱረቱል አል-አንፋል 8 ፡ 31 ን በተመለከተ ሚሽነሪ ላላቸው ወገኖች መልስ ይሆንልኛል ብሎ የለቀቀውን ጽሑፍ ሳነብ ጽሑፉ እንደ ሁልጊዜው አሁንም በብዙ ስህተቶችና ማጭበርበሮች የተሞላ ሆኖ ስላገኘሁት እርሱን ለቅኖች ግልጽ ለማድረግ ስላሰብኩ ብቻ ነው፡፡

"ብዙ ጊዜ ሚሽነሪዎች፦ ይላሉ፤ ይህ የሚያሳየው አንቀጹን በጥሞና እና በቅጡ አለማንበባቸው እና ይህንን አንቀጽ የወረደበትን ምክንያት ጠንቅቆ ካለመረዳት የሚመጣ የተሳከረ ምልከታ ነው፤"

እንዲህ እንዲል የገፋፋው ብዙ የኢስላም ዳኢዎችን የተጠናወተው ኢስላምንና መጽሐፍቱን እኛ ብቻ ነን የምናውቀው የሚለው አባዜ እርሱንም ተጠናውቶት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በእርግጥ ‘በቅጡ አለማንበብና ቁርአን የወረደበትን ምክንያት ጠንቅቆ አለማወቅ’ የሚለው የሚሠራው ለወሂድና ለሙስሊም ወንድሞቹና እህቶቹ ብቻ ነው፡፡ ለዛም ነው ያለምንም ፍርሀት "የቀድሞ ሰዎች ተረት ነው" በምትለው ሐረግ ላይ በመንጠልጠል ሐሰተኛ አስባብ በመጠቀም ያለውን ለማለት የቻለው፡፡ በዚህ ማታለልና ማስጨብጨብ የሚችለው ስለ አስባብ አይደለም ስለምንም የማያውቁትን ሙስሊሞቹን ሊሆን ይችላል፡፡ ክርስቲያኖች ላይ ግን እንዲህ እንዳታስብ የሚለው ምክሬ ነው፡፡

የወሂድ አስባብ፡-

ወሂድ ሚሽነሪ ያላቸውን ወገኖች ጉድለት ከገለጸ በኋላ የአንቀጹን አስባብ ለማብራራት የተንደረደረው "ቂያማህ" በሚል በአንቀጹ ውስጥ በሌለ ቃል ነው፡፡ ለምን? መልሱ በጣም ቀላል ነው፡፡ እንዲህ ያደረገው ለማጭበርበርና ሙስሊሞችን ለማስደነቅ እቅዱ አመች ስለሚሆንለት ነው፡፡ የሰጠው ትንታኔ ግን በየትኛውም የተፍሲር ሳይንስ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ አለው ካለም ያሳይ ይኸው ሜዳው፡፡

አይካድም "የቀድሞ ሰዎች ተረት ነው" የሚለውን ሐረግ የያዙ አስባባቸው ከቂያማህ ጋር የሚያያዝ የቁርአን አንቀጾች አሉ፡፡ አብዛኞቹን በጽሑፉ ተጠቅሷቸዋል፡፡ ታዲያ ይህንን "ቂያማሕ" የሚለውን ቃል እንደ ማዛመጃ የተጠቀመው ለአንቀጹ ሐሰተኛ አስባብ በመስጠት ከጥያቄው ለማምለጥ ስላሰበ ብቻ ነው፡፡ ለዚህ አንቀጽ እንደ አስባብ ቂያማህን የተጠቀመ አንድም የተፍሲር ሊቅ መጥቀስ አይችልም፡፡ ይህ የራሱ ግልጽ ማጭበርበርና በሐሰት ቁርአንን ለመከላከል የተደረገ ያልተሳካ ጥረት ነው፡፡ ወገን! ለሌላው ሰው መታመን ይቅር፤ ለራስ ሕሊናም አለመታመን ግን ከባድ ነው፤ ሕሊናውን ለሚሰማና ለሚኖርለት ሰው ማለቴ ነው፡፡

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት እርሱም እንዳሰፈረው ቁርአን ውስጥ "የቀድሞ ሰዎች ተረት ነው" የሚል ሐረግ የያዙ የተለያዩ የቁርአን አንቀጾች መኖራቸውን አይተናል፡፡ አንቀጾቹ ምንም ይህንን ሐረግ ቢይዙም አንቀጾቹ ተመሳሳይ አስባብ አላቸው ማለት እንዳልሆነ ግን ይታወቃል፡፡ ይህንን ሐረግ የያዙ የተለያዩት የቁርአን አንቀጾች በጥቂቱ ሁለት አስባብ እንዳላቸው የቁርአን ማብራሪያዎች ያሳያሉ፡፡ አንዱ ወሂድ እንደገለጸው ትንሳኤ ሙታን እንዳለ በማያምኑ ሰዎች ምክንያት የወረዱ ሲሆኑ ሌላው ግን ከቁርአን መለኮታዊ ቃል ያለመሆን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ የሱረቱል አል-አንፋል 8 ፡ 31 አስባብ የትንሳኤ ሙታን ጉዳይን የሚመለከት ሳይሆን ቁርአን መለኮታዊ ቃል አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ ይህ በሁሉም ሙፈሲሮች የተገለጸና የቁርአን አንቀጹ ፍሬ ሐሳብ ላይም በግልጽ የሚታይ ነው፡-

*አንቀጾቻችንም በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ*

ይህም ቁርአን "እውነተኞች እንደ ሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ" (11 ፡ 13)፣ "በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ" (2 ፡ 23)፣ "ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ" (10 ፡ 38) ለሚሉት አንቀጾቹ የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡ እንዲህ መሆኑን የሚያሳየው ኢማም ኢብን ከሲር ለአንቀጹ የሰጡት ማብራሪያ ነው፡-

An-Nadr visited Persia and learned the stories of some Persian kings, such as Rustum and Isphandiyar. When he went back to Makkah, He found that the Prophet was sent from Allah and reciting the Qur'an to the people. Whenever the Prophet would leave an audience in which An-Nadr was sitting, An-Nadr began narrating to them the stories that he learned in Persia, proclaiming afterwards, "Who, by Allah, has better tales to narrate, I or Muhammad'' When Allah allowed the Muslims to capture An-Nadr in Badr, the Messenger of Allah commanded that his head be cut off before him, and that was done, all thanks are due to Allah.

ነቢዩ እስልምናቸውንና ነቢይነታቸውን የተከላከሉት የሰውየውን ራስ በመቅላት እንጂ በትምህርትና በመገለጥ ብልጫ አልነበረም፡፡ ለማንኛውም ወሂድ የጥያቄውን ትክክለኛነት ተረድቶ ቁርአን የቀደሙት ሰዎች ተረት አለመሆኑን ለማሳየት መጣጣር ሲኖርበት የገሰገሰው ወደ ዘለፋና ለአንቀጹ ሐሰተኛ አስባብ ወደ ማዘጋጀቱ ነው፡፡ እንዲህ ማምታታቱን አቆየው፣ ለማደናገር መሞከሩንም ተወውና ቁርአን የቀደሙት ሰዎች ተረቶች አለመሆኑን ለማሳየት ሞክር፡፡ ከቻልክ፤ ካልቻልክ ደግሞ እጅን በአፍ ላይ ጭኖ ዝም ማለት አዋቂነት ነው፡፡ ለሁሉም መልስ የለም፡፡ ኢስላምን በምትፈበርከው ውሸት እውነት ልታደርገው አትችልም፣ ሰዎችን ወደ ጀሃነም ለሚመራው አገልጋይ መሆን ግን ትችላለህ፡፡
ሰላም!
ሳሂህ ነኝ
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (ይሰማል? ሞትን አንድ ቀን ተጠጋኸው እኮ)
ሱረቱል አል-አህዛብ 33 ፡ 21
ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
ሱረቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 80
መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡

እንግዲህ "አላህ" የተባለው እውነተኛው አምላክ ከሆነ በዚህ ጊዜ ላይ ማለትም የነቢዩ ሕይወት የሙስሊሞች የሕይወት መለኪያ ወይም ምሳሌ እንደሆነ ተናግሮ እያለ በቁርአኑ መለኮታዊ ቃልነት ላይ ሰዎች ጥያቄ ሲያነሱ ብሳሳት የምሳሳተው እኔው ብቻ ነኝ እንዴት ይላል? ነቢዩ ከተሳሳቱ እነዚያ የተከተሏቸው በሙሉ በስህተት ጎዳና ላይ እንደሚሆኑ እንዴት ያጣዋል? ይህ የመለኮት የዕውቀትን ጣራ የሚያሳይ ነውን? ነቢዩ ቢሳሳቱ የሚሳሳቱት እርሳቸው ብቻ እንደሆኑ ካመነ ሰይጣንን የተከተሉትን ለምን እንደ ወንጀለኛ ያያቸዋል? እርሱ ነው ከጅማሬው የተሳሳተው ስህተቱ የራሱ ብቻ ነው፡፡ የሰይጣንን ፈለግ እንዳይከተሉ ያዘዘበት ቃሉ ጋር እንዴት ይታረቃል? ይህ የሚያሳየው ቁርአን የአምላክ ቃል አለመሆኑን ነው፡፡ ይህ እንዲህ የሚለውን አስባብ ያስታውሰኛል፡-

"…The commentators of the Qur’an said: “The idolaters said: ‘Do you not see that Muhammad commands his Companions with something and then forbids them from the same and commands them to the exact opposite. One day he says something and the following day heretracts it. This Qur’an is nothing but the speech of Muhammad who has invented it. It is a speech that contradicts itself’." (Asbab al-Nuzul sura 2:106,)

4. "ነቢዩ አምላክ ሳይሆኑ ሰው እንደሆኑና ስህተት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ"

ያህያ ነው ይህንን ያለው፤ አይ ያሕያ ይህ የመጀመሪያ ሰው ያደርግሀል፤ እውቀት አጠርነትህንም በጉልህ አደባባይ ላይ ያሰጣል፡፡ ለነገሩ የሰው እየተረጎሙ የራሴ የሚሉ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ይኸው ነው፤ ያነበቡትን እንደወረደ መክተብ ብቻ ማሰላሰልና ማገላበጥ አይሆንላቸውም፡፡ ለማንኛውም ምንም የነቢዩ ስህተቶች ሕልቆ መሳፍርት የሌላቸው ቢሆኑም እንደ ኢስላም "በነቢያት ማመን" ኢማን ነቢያት እንከን የለሽ፣ ኃጢአት የማያደርጉ መሆናቸው ነው የሚታመነው፡፡ ታዲያ አንተ ከየት አመጣኸውና ነቢዩ ስህተት ይፈጽማሉ አልክ? ኢስላምን ላሽ አልከው እንዴ? እስኪ ከአንድ "የኢስላም መሠረተ ሀሳቦች" ከተሰኘ መጽሐፍ ገጽ 83 ላይ ያገኘሁትን ላስነብብህ፡-

"ረሱል (መልእክተኞች) ከኃጢአት መጠበቃቸው
ሰዎችን ከሥጋዊ ዝንባሌ ባርነት ነፃ ለማውጣትና ኃጢአት እንዳይሠሩ ከልክለው ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማውጣት አላህ የላካቸው ነቢያት ለራሳቸው በውብ ሥነ ምግራሮች የተካኑ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ነቢያት በሕዝቦቻቸው መጥፎ ተግባራት የሚካፈሉ ቢሆኑ ኖሮ የጥፋት አርአያ በሆኑና የአላህ ትምህርቶችም ፌዝና ጥመት በሆኑ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ቁርአን የመልእክተኞችን ታላቅነትና ጥራት ብዙ ቦታ ላይ አጥብቆ ያወደሰው፡፡… ሱረቱል አል-አንቢያ 21 ፡ 73፣ ሱረቱል አል-አምአም 6 ፡ 89-90"

ኢማኑ እንዲህ እየሆነ አንተ ደግሞ ይሳሳታሉ ካልክ ነቢዩ ለማንም ምሳሌ ሊሆኑ የማይችሉ ተራ ሰው ነበሩ እያልክ ነው፤ እንግዲያው የአላህ መልእክተኛ አይደሉማ! እናመሰግናለን እኛስ ምን አልን፡፡
ሠላም!
ሳሂህ ነኝ!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የነቢይነት ማሕተም ወይንስ የጤና ችግር?

የእስልምና ቅዱሳት መጻሕፍት ለሙሐመድ ነቢይነት ማረጋገጫ ብለው የሚያቀርቧቸው ነገሮች በእጅጉ አስገራሚ ናቸው፡፡ ሙሐመድ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት ለነቢይነት የሚያበቃ ማስረጃም ሆነ ማረጋገጫ ስለሌለው ጥንታውያን ሙስሊሞች ያዩትን ነገር ሁሉ ለነቢይነቱ ማረጋገጫ ምልክት አድርገው ይተረጉሙ እንደነበር መረዳት ይቻላል፡፡
ሙሐመድ ራሱን የነቢያት መደምደምያ ወይንም ማሕተም አድርጎ ይቆጥር እንደነበር ቁርአንም ሆነ የሐዲስ መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡-

“ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፤ አላህም በነገሩ ሁላ ዐዋቂ ነው።” (ሱራ 33፡40)
Muhammad is not the father of any of your men, but (he is) the Apostle of God, and the Seal of the Prophets: and God has full knowledge of all things. (33:40 Yusuf Ali)

ይህ ዓይነቱ ንግር ሙሐመድን ከነቢያት ሁሉ የበላይ በማድረግ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ ስለሚያደርገው በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ስለዚህ የነቢያት ማሕተም ስለመሆኑ ማሳያ የሚሆን የማረጋገጫ ምልክት ያሻዋል፡፡ ነገር ግን ለዚህ የሚሆን አንዳችም ልዕለ ተፈጥሯዊ ምልክት ባለመኖሩ ሳብያ ጥንታውያን ሙስሊሞች “ምልክት” ሆነው ሊተረጎሙ የሚችሉ ነገሮችን ለማግኘት ቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የገቡ ይመስላል፡፡ በዚህም ሒደት በሙሐመድ ጀርባ ላይ የሚገኝ እብጠት እንዴት ሆኖ የነቢይነቱ ምልክት ተደርጎ እንደተተረጎመ ተዓማኒ የተባሉት የሐዲስ ስብስቦች እንዲህ ይነግሩናል፡-

አስ ሳዒብ ቢን ያዚድ እንዳስተላለፈው፡- አክስቴ ነቢዩ ዘንድ ወሰደችኝና እንዲህ አለች፣ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይህ የእህቴ ልጅ እግሩ ላይ ህመም አለበት፡፡” ከዚያም እጁን በላዬ አሳልፎ የአላህን በረከት ለመነልኝ፤ ከዚያም ትጥበት ፈፀመና ከተረፈው ውኀ ጠጣሁ፡፡ ከዚያም ከበስተጀርባው ቆሜ የነቢይነት ማሕተምን በትከሻው መካከል አየሁ፤ልክ እንደ “ዚር አል-ሒጅላ” ይመስላል (የትንሽ ድንኳን ቁልፍ፣ ነገር ግን አንዳንዶች የቆቅ እንቁላል፣ ወዘተ. ይመስላል ይላሉ)፡፡ (Sahih al-Bukhari Volume 1, Book 4, Number 189)

አስ ሳዒብ እንዳስተላለፈው፡- አክስቴ ወደ አላህ መልእክተኛ ወስዳኝ እንዲህ አለች፡- “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የእህቴ ልጅ ታሟል፡፡” ነቢዩ ጭንቅላቴን በመንካት የአላህን በረከት ለመነልኝ፡፡ ከዚያም ትጥበት ከፈፀመ በኋላ ከትጥበቱ የተረፈውን ውኀ ጠጥቼ ከጀርባው በመቆም “ኸተም አን-ኑቡዋ” (የነቢይነት ማሕተም) በትከሻዎቹ መካከል ልክ እንደ ድንኳን ቁልፍ የሚመስል አየሁ፡፡(Sahih al-Bukhari Volume 7, Book 70, Number 574)

ጃቢር ቢን ማሙራ እንደዘገበው፡- የእርግብ ዕንቁላል የሚመስለውን ማሕተሙን ጀርባው ላይ አየሁ፡፡ (Sahih Muslim Book 030, Number 5790)

አብዱላህ ቢን ሰርጂስ እንደዘገበው፡- … ከዚያም ተከትዬው ሄድኩና በትከሻዎቹ መካከል የሚገኘውን የነቢይነት ማሕተም ተመለከትኩ፤ ወደ ግራ ጎኑ አቅጣጫ የቆዳ ትርፍ ሥጋ የሚመስሉ ምልክቶች አሉበት፡፡ (Sahih Muslim Book 030, Number 5793)

ቁራህ ኢብን ኢያስ አል-ሙዛኒ እንዳስተላለፈው፡- ከሙዛይናህ ጋር ሆነን ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና) መጣንና ቃል ኪዳን ገባን፡፡ የሸሚዙ ቁልፍ ክፍት ነበር፡፡ የታማኝነት ቃል ኪዳን ገባሁለትና በሸሚዙ አንገት ጌ እጄን አስገብቼ ማሕተሙን ስነካው ተሰማኝ… (Sunan of Abu Dawud Book 32, Number 4071)

ተመሳሳይ ዘገባዎች በሌሎች በርካታ እስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሙሐመድ የነቢያት መደምደሚያ የመሆኑ ምልክት በጀርባው ላይ እንደሚገኝ ይናገራሉ፡፡ ይህም ምልክት “የነቢያት ማሕተም” (ኸተም አን-ኑቡዋ) የተባለ ሲሆን ሱራ 33፡40 ላይ “የነቢዮች መደምደሚያ” ተብሎ ከተተረጎመው ጋር ተመሳሳይ የሆነ የአረብኛ ሐረግ ነው፡፡ ከዘገባዎቹ እንደምንገነዘበው ጥንታውያን ሙስሊሞች “የነቢያት ማሕተም” ብለው የተረጎሙት ምልክት በሙሐመድ ጀርባ ላይ የሚገኝ ትርፍ ሥጋ፣ እባጭ ወይንም ዕጢ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የጤና ችግር በምን መንገድ የነቢይነት ምልክት ተደርጎ እንደተወሰደና ለሙሐመድ ነቢይነት ማረጋገጫ ሆኖ እንደቀረበ ማሰብ በእጅጉ ይቸግራል፡፡ ውድ ሙስሊሞች፤ ምን እያላችሁ ነው? እስኪ አስረዱን?
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
ቁርአንና ሳይንስ
-------------
ባለፉት ሦስት ክፍለ ዘመናት በምዕራቡ ዓለም ከተቀጣጠለው የሳይንስ አብዮት የተነሳ የሙስሊሙ ዓለም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ ስጋቱ ከአብዮቱ ፖለቲካዊ ምልከታ ባሻገር ሳይንሳዊ ግኝቶች የእስልምና ሃይማኖት መሠረት በሆነው በቁርአን ውስጥ ስህተቶች መኖራቸውን ይገልጥ ይሆናል የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሳይንሳዊ ግኝቶች ለእስልምና ጥቅም ማዋል የሚቻልበትን መንገድ የቀደደ አንድ መጽሐፍ ለሕትመት በመብቃቱ የሙስሊሙ ዓለም እፎይታን አገኘ፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ መውሪስ ቡካይሌ ይሰኛል፡፡ ዶ/ር ቡካይሌ የሳዑዲ አረብያ ንጉሥ የግል ኃኪም የነበረ ሲሆን ሙስሊም አልነበረም፡፡ በ1976 ዓ.ም. መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቁርአንና ሳይንስ በሚል ርዕስ ባሳተመው ጥራዝ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ “በሳይንሳዊ ስህተቶች የተሞላ” መሆኑንና ቁርአን ደግሞ በተጻራሪው ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ “ሳይንሳዊ ቅድመ ዕውቀቶችን በውስጡ የያዘ ከስህተት የጸዳ መለኮታዊ መጽሐፍ” መሆኑን ይሞግታል፡፡ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ተጠቅሞ የቁርአንን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚደረግ ሙግት ቡካይሌኢዝም የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከዚህ ሰው ነው፡፡

ሐሰን ታጁ በዚህ መጽሐፋቸው ውስጥ ቡካይሌን ጠቅሰውታል፡፡ እንዲህ ይላሉ፡-

… በዚህ ዘመን በተለያዩ የሳይንስ መስኮች የተገኙ አዳዲስ ግኝቶችን ቁርአን ከ14 ክፍለ ዘመናት በፊት ቀድሞ ከመናገሩ የበለጠ አምላካዊነቱን መስካሪ ነገር ማግኘት ይቻላልን? በዚህ ረገድ ከተደረጉ ምርምሮች መካከል ፈረንሳዊው የሕክምና ሊቅ ዶክተር ሞሪስ ቡካይ The Bible The Quran and the science በሚል ርዕስ ያሳተመው መጽሐፍ ይገኝበታል፡፡ ጸሐፊው ምርምሩን ለማድረግ ሲነሳ ሙስሊም አልነበረም፡፡ ጥናቱን ካጠናቀቀ በኋላ ግን በደረሰበት አስገራሚ ግኝት በመደነቅ ነቢዩ ሙሐመድ እነዚህን ሳይንሳዊ እውነታዎች ሊያውቁ የሚችሉበት ምንም አይነት መንገድ እንደሌለ ከገለጸ በኋላ የቁርአን ምንጭ መለኮታዊ መሆኑን በመገንዘብ እስልምናን ተቀብሏል፡፡ (ገፅ 178)

የቡካይሌ መጽሐፍ የእንግሊዘኛ ሙሉ ርዕስ The Bible, The Qur’an, and Science: The Holy Scriptures Examined in the Light of Modern Knowledge የሚል ሲሆን መጀመርያ የተዘጋጀው በፈረንሳይኛ ነበር፡፡ መጽሐፉ ከእንግሊኛ በተጨማሪ ወደ ብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፣ በሙስሊሙ ዓለም ውስጥም በከፍተኛ ሁኔታ ተሽጧል፡፡

ፈጠራ የማይሰለቻቸው አቶ ሐሰን ቡካይሌ “እስልምናን ተቀብሏል” ቢሉም ነገር ግን እስልምናን መቀበሉን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ ሰውየው እስልምናን መቀበሉን በመጽሐፉ ውስጥም ሆነ በየትኛውም ቦታ አልገለፀም፡፡ እስላማዊ መጻሕፍትን በማሰራጨት የሚታወቀው Pak Books የተሰኘ ድረ-ገፅ በዶ/ር ቡካይሌ ካታሎግ ስለ ሰውየው ሲገልፅ፡-

“በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙትን መረጃዎች ማጥናቱ ዶ/ር ቡካይሌ ለቁርአን ከፍ ያለ አክብሮት እንዲኖረውና በክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙትን ተቃርኖዎች እንዲገነዘብ ረድቶታል፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ ለእስልምና ጥልቅ አክብሮት ቢኖረውም የክርስትና እምነቱን አልቀየረም” በማለት ጽፏል፡፡[http://www.j51.com/~alicamp/auth.htm#b]

ቡካይሌ ክርስቲያን መሆኑን ተናግሮ ባያውቅም ነገር ግን ሙስሊሞች የእስልምናን እውነተኝነት የተገነዘበ ክርስቲያን ሊቅ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ዳሩ ግን ሙስሊሞችን ሁሉ ሊያሳስብ የሚገባው አንድ ጥያቄ አለ፤ ቡካይሌ ቁርአን የፈጣሪ ቃል መሆኑን ካረጋገጠና ሌሎች ሰዎችም ይህንኑ እንዲያውቁ በሚል መጽሐፍ ከጻፈ ለምን እስልምናን አልተቀበለም? መልሱ ግልፅ ነው፡፡ ቡካይሌ እስልምና እውነት መሆኑን ከልቡ የሚያምን ሰው አልነበረም፡፡ መጽሐፉን የጻፈው ለገንዘብ እንጂ የእውነት ምስክር ለመሆን አልነበረም፡፡ ይህ መጽሐፍ ምድራዊውን ኃብት በአቋራጭ የማጋበስ ዓላማውን በማሳካት በዶላር ኮረብታ ላይ አስቀምጦታል፡፡ እንዲህ ያለ ሰው የእውነት ምስክር የመሆን ብቃት እንዴት ሊኖረው ይችላል?

ሳይንስን ማን አስተማራቸው?
------
ሳይንስን ማን አስተማራቸው? የሚለው ጥያቄ አቶ ሐሰን “የቁርአን ደራሲ ከሌሎች ምንጮች ቀድቷል” ለሚለው ሙግት የሰጡት ምላሽ ነው፡፡ የ20ኛው ክ.ዘ. ግኝቶች የሆኑ በርካታ ሳይንሳዊ እውነታዎች በቁርአን ውስጥ መገኘታቸውን ከገለጹ በኋላ ሁለት ምሳሌዎችን በመጥቀስ ምላሻቸውን በማስረጃ ለማጠናከር ይሞክራሉ (ገፅ 118)፡፡ ዳሩ ግን የጠቀሷቸው ሁለቱም ምሳሌዎች ቁርአን ምን ያህል ከሳይንስ የራቀ መሆኑን የሚያሳዩ እንጂ ነጥባቸውን የሚያረጋግጡ ሆነው አላገኘናቸውም፡፡ እንደሚከተለው እናያቸዋለን፡-

ሁሉም ነገር የተፈጠረው ጥንድ ሆኖ ነው?
እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እጽዋትም ጭምር ሴቴና ወንዴ ፆታ እንዳላቸው፤ ከዚህም አልፎ ሁሉም ነገር የጥንድ (ፖዘቲቭና ኔጌቲቭ) ባሕርይ መያዙ በቁርአን መገለፁን ለማረጋገጥ ገፅ 118 ላይ ተከታዮቹን ጥቅሶች ጠቅሰዋል፡-

“ያ ምድር ከምታበቅለው ከነፍሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ዓይነቶችን ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው፡፡” Exalted is He who created all pairs – from what the earth grows and from themselves and from that which they do not know. (ሱራ 36፡36)

“ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡” And of all things We created two mates; perhaps you will remember. (ሱራ 51፡49)

አብዱላህ ዩሱፍ አሊ የተሰኙ ሙስሊም ሊቅ ሁለተኛውን ጥቅስ ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል፡-

ሁሉም ነገር ጥንድ ነው፤ የእፅዋትና የእንስሳት ፆታ… የማይታዩት የተፈጥሮ ኃይላት፣ ቀንና ሌሊት፣ ፖዘቲቭና ኔጌቲቭ የኤሌክትሪክ ሞገዶች…

የአማርኛ ቁርአን የግርጌ ማስታወሻም ጥቅሱን በተመሳሳይ መንገድ ይተረጉመዋል፡፡

እንስሳትና እፅዋት ወንዴና ሴቴ እንዳላቸው ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ በመሆኑ እንዲህ ያለው ንግግር ሳይንሳዊ ቅድመ ዕውቀት ሊባል አይችልም፡፡ ዳሩ ግን የቁርአን ጸሐፊ ሁሉም ነገር ጥንድ ሆኖ እንደተፈጠረ በመናገር መገለጡ መለኮታዊ አለመሆኑን ይፋ አውጥቷል፡፡ ወንዴና ሴቴ የሌላቸው ብዙ የእፅዋት ዝርያዎች አሉ፡፡ ባክቴርያን የመሳሰሉት ባለ ነጠላ ሴል ፍጡራን ተባዕታይና እንስታይ ፆታ የላቸውም፡፡ ብዙ የፈንገስ ዝርያዎችም ተመሳሳይ ተፈጥሮ አላቸው፡፡[http://en.wikipedia.org/wiki/Asexual_reproduction] ተቃራኒ ፆታ የሌላቸው በዓይን የሚታዩ ብዙ የእንስሳት ዝርያዎችም አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል በኒው ሜክሲኮ የምትገኝ ዊብቴይል ሊዛርድ የተሰኘች የእንሽላሊት ዝርያ እንስታይ ፆታ ብቻ ያላት ስትሆን የራሷን ምስለኔ (Clone) ዕንቁላል በመጣል ራሷን ትተካለች፡፡[http://en.wikipedia.org/wiki/Cnemidophorus_neomexicanus] የቁርአን ደራሲ መገለጡ ከሰማይ የመጣለት ቢሆን ኖሮ ይህንን ሐቅ ማወቅ ባልተሳነው ነበር፡፡ አቶ ሐሰን ቁርአን ሳይንሳዊ ሐቆችን በውስጡ መያዙን ለማሳየት የጠቀሱት አንቀፅ አንድ የሰባተኛው ክፍለ ዘመን አረባዊ ከነበረው ዕውቀት ያልተሻለ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

የሽል እድገት
በማስከተል ደግሞ ተከታዩን ጥቅስ ጠቅሰዋል፡-
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
“…እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ ሥጋ፣ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፡፡ የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማሕፀን ውስጥ እናረጋዋለን፡፡ ከዚያም ሕፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን፡፡ ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን)፡፡” (ሱራ 22፡5)

ይህንን ጥቅስ ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል፡-

በዚህ አንቀፅ ውስጥ የፅንስ ዑደት ከሳይንስ እውነታ ጋር መቶ በመቶ በሚጣጣም መልኩ ተገልጿል፡፡ የሰው ልጅ መጀመርያ የፍትወት ጠብታ ነበር፡፡ ይህ ጠብታ ከሴቷ እንቁላል ጋር ሲዋሃድ እና ሲያዳብረው የረጋ ደም አይነት ባህሪ በመያዝ ከማህጸን ግድግዳ ላይ ይንጠለጠላል፡፡ ‹ዓለቃህ› የመንጠልጠልና የመጣበቅ ባህሪ ስላለው ነው፡፡ በመቀጠልም የተላመጠ ስጋ ይመስላል፡፡ ከነዚህ ሂደቶች በኋላ የተሟላ ቅርጽ ይይዛል፡፡ (ገፅ 119)

ቁርአን ስለ ፅንስ ዑደት ደረጃዎች የሰጠውን ትንታኔ ሙሉ ምስል ለማግኘት አቶ ሐሰን ያልጠቀሱትን አንድ ጥቅስ እንጨምር፡-

“በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡ ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡” (ሱራ 23፡12-14)

ስለዚህ በቁርአን መሠረት ሰው በማህፀን ውስጥ መጀመርያ የፍትወት ጠብታ ነበር (የሴቷ ዕንቁላል አለመጠቀሱን ልብ ይሏል) => ጠብታው የረጋ ደም ይሆናል => የረጋው ደም ቁራጭ ሥጋ ይሆናል => ቁራጭ ሥጋው ወደ አጥንቶች ይለወጣል => አጥንቶቹ እንደገና ሥጋ ይለብሳሉ => ነፍስ በመዝራት ሰው ይሆናል፡፡

ይህንን የሽል ዕድገት ደረጃ በተመለከተ ቀድሞ የእስልምና እምነት ተከታይ የነበሩት ክርስቲያን ዓቃቤ እምነት ዶ/ር ነቢል ቁሬሺ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-

የሥነ ሕይወት አጥኚ ይህንን ጥቅስ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አያገኘውም፡፡ ቡካይሌ እንኳ ትንተናውን ሲጀምር ይህንን ሃቅ በመረዳት እንዲህ በማለት ይናዘዛል፡- “ይህ ዘርፉን በሚያጠኑት ሊቃውንት ዘንድ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም፡፡”[Maurice Bucaille. The Bible, The Qur’an, and Science: The Holy Scriptures Examined in the Light of Modern Knowledge; p. 214] ነገር ግን ችግሩ ቁርአን በሰባተኛው ክፍለዘመን ለመጠቀም የተገደደው ቃል መሆኑንና “ዩተረስ” የሚለውን የዘመናዊ ሳይንስ ቃል “በተጠበቀ መርጊያ” በሚለው ቦታ ብንተካ ችግሩ እንደሚወገድ ተናግሯል፡፡[Ibid., 215] ቁርአንን አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ እየተረጎመ እንዳደገ ሙስሊም የቡካይሌን ሐሳብ እጋራለሁ፡፡ እንደ ኅክምና ተማሪ ግን ቃላትን የፈለገ ያህል ብንተካ የዚህ ጥቅስ አንዱ ችግር ፈፅሞ ሊቀረፍ እንደማይችል ተገንዝቤያለሁ፡፡ ጥቅሱ የሽልን የዕድገት ቅደም ተከተል የሚናገር ቢሆንም ቅደም ተከተሉ ግን ትክክል አይደለም፡፡ ሽል መጀመርያ አጥንት ሆኖ ከዚያ በሥጋ አይሸፈንም፡:፡ ሜሶደርም የተሰኘው የሽል ክፍል ነው በአንድ ጊዜ ሥጋም አጥንትም ወደመሆን የሚያድገው፡፡

ለዚህ የተሰጡትን ምላሾች መርመሬያለሁ፡፡ ብዙዎቹ ደካማ የሆነ ተቃውሞ መሆኑን ቢናገሩም ሙስሊም እያለሁ እንኳ ምላሹን አልተቀበልኩትም ነበር፡፡ ቡካይሌ በጥቅሱ ውስጥ የሚገኙት ቅደም ተከተሎች ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ ትክክል መሆናቸውን ለማስረዳት ቢሞክርም ቅደም ተከተሉ ግን ትክክል አይደለም፡፡ ይህ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ ቡካይሌ ጥቅሱን በስፋት ለመተንተን ቢሞክርም ነገር ግን ችግሩን አለባብሶ አልፎታል፡፡

ግልፅ በሆነው የጥቅሱ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ስህተት መረዳት ቀላል ነው፤ ነገር ግን ይህ ብቸኛው ችግር አይደለም፡፡ የጥቅሱ የመጀመርያው ክፍል የአረብኛውን የተሳሳተ ቃል በሳይንሳዊ ቃል እንድንተካ ያስገድደናል፡፡ ስለዚህ የመጀመርያውን ችግር ብቻ በመፍታት ሁለተኛውን በቸልታ የምናልፈው ከሆነ ሳይንሳዊ ተዓምር ሊባል የሚችል ምን ነገር ይኖራል? ይህ ጥቅስ ቁርአን ግልጠተ መለኮት መሆኑን እንደማያስረዳ ተገንዝቤያለሁ፡፡[Nabil Qureshi. Seeking Allah Finding Jesus; p. 233-35]

የተጠቀሱት ሁለቱም ጥቅሶች ቁርአን ከሳይንስ ጋር የተስማማ መጽሐፍ መሆኑን ከማረጋገጥ ይልቅ ተቃራኒውን እንደሚያረጋግጡ ተመልክተናል፡፡ አቶ ሐሰን ጥቅሶቹን ካቀረቡ በኋላ በአሸናፊነት ስሜት እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፡-

እነዚህንና ሌሎችን ሳይንሳዊ እውነታዎች ለነቢዩ ሙሐመድ ማን አስተማራቸው? ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀዷቸውን? በፍጹም፡፡ ሳይንስና መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እሳትና ጭድ የማይስማሙ ተጻራሪ ነገሮች ናቸው፡፡ ከአይሁድ አዋልድ መጽሐፍት? ይህም ሊሆን እንደማይችል ሐመሮች ያውቁታል …. ታድያ ሙሐመድ እነዚህን ድንቅ ሳይንሳዊ እውነታዎች ከየት አገኟቸው? ሐመሮች ከጠቀሷቸው ምድራዊ ምንጮች በላይ ከሆነ ሌላ ምንጭ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ (ገፅ 120)

[ቁርአን ከሳይንስ ጋር “የተስማማ” ሆኖ ሳለ የእስልምናው ዓለም ምንም የረባ ሳይንሳዊ ግኝት ለዓለም አለማበርከቱና አንፀባራቂ ሳይንሳዊ ግኝቶች ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታዮች በሆኑት በክርስቲያኖችና በአይሁድ የተበረከቱ መሆናቸው አስገራሚ ነው፡፡]

የቁርአን ደራሲ ስለ ሽል ዕድገት የሚያወራውን ኢ-ሳይንሳዊ ሐተታ ከላይ ከተጠቀሱት ከየትኞቹም ምንጮች አላገኘም፡፡ ከሰማይም አልወረደለትም፡፡ ጉዳዩን በጥልቀት ያጠኑት ወገኖች የዚህ ሐተታ ምንጭ ጋለን የተሰኘ ግሪካዊ የሕክምና ሊቅ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህ ሰው ቱርክ ውስጥ በምትገኝ የጴርጋሞን (የዛሬዋ ቤርጋማ) ከተማ በ131 ዓ.ም. የተወለደ ሲሆን ፅንስን በተመለከተ የሰጣቸው ትንታኔዎች ለክፍለ ዘመናት አረብያን ጨምሮ በብዙ የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ ተቀባይነት ነበራቸው፡፡ ቁርአን የጠቀሳቸው የሽል ዕድገት ደረጃዎች ያለምንም መዛነፍ በጋለን ጽሑፎች ውስጥ ተጠቅሰው እናገኛለን፡፡[Corpus Medicorum Graecorum: Galeni de Semine (Galen: On Semen) (Greek text with English trans. Phillip de Lacy, Akademic Verlag, 1992) section I:9:1-10 pp. 92-95, 101]
-------

ይቀጥላል. . .
👍1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የቁርአን ኢ-ሳይንሳዊ “መገለጦች”
-----------------------------

አቶ ሐሰን በቁርአን ውስጥ ይገኛሉ ተብለው በተደጋጋሚ ለሚነሱት ኢ-ሳይንሳዊ አናቅፅ ምላሽ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ በማስከተል መልሶቻቸውን አንድ በአንድ እንፈትሻለን፡፡

ጸሐይ በጥቁር ጭቃ ምንጭ ውስጥ?

ቁርአን ጸሐይ የምትጠልቅበትን ቦታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡-

“ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት፡፡ ባጠገቧም ሕዝቦችን አገኘ፡፡ «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም (በመግደል) ትቀጣለህ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን (መማረክን) ትሠራለህ» አልነው፡፡” (ሱራ 18፡86)

አቶ ሐሰን ለዚህ ያፈጠጠ ያገጠጠ የቁርአን ስህተት እንዲህ በማለት መልስ ይሰጣሉ፡-

ነገሩ እንደዚህ አይደለም፡፡ አንቀጹ ከሳይንስ ጋር የሚያገናኝ ነገር የለውም፡፡ እንዲያውም የቁርአንን የገለጻ ምጥቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህውም ዙልቀርነይን የተባለው ሰው ባደረገው ረዥም ጉዞ ከአንድ ውቂያኖስ ወይም ባሕር አጠገብ ደረሰ ወቅቱ የጸሐይ መጥለቂያ ወቅት ነበር፡፡ ጸሐይ ከውቂያኖሱ ባሻገር ስትጠልቅ ተመለከታት፡፡ ለእርሱ እይታ ከውሃው ውስጥ የጠለቀች ይመስል ነበር፡፡ ይህ ዘወትር የምናየው ትእይንት ነው፡፡ ከፊት ለፊታችን ተራራ ካለ ጸሐይዋ ልክ ከተራራው ጀርባ የጠለቀች ይመስለናል፡፡ ባሕር ካለ ወደ ባህሩ ስትጠልቅ እናያለን፡፡ ዙልቀርነይን ያየውን ክስተት ቁርአን ምስል ሰርቶ ውብ በሆነ ቋንቋ አስቀመጠው እንጅ የጸሐይ መጥለቂያ ምንጭ ወይም ባሕር ነው የሚል ቃል አልወጣውም፡፡ (ገፅ 179)

አቶ ሐሰን የሰጡት ትንታኔ አሳማኝ አይደለም፡፡ ይህንን ትርጉም ለማግኘት “ምንጭ” የሚለውን ወደ ውቂያኖስ ቀይረውታል፤ “አገኛት” የሚለውንም “ተመለከታት” በሚል ቃል ተክተዋል፡፡ ጥቅሱ ዙልቀርነይን የተባለው ሰው ወደ ፀሐይ መግቢያ እንደደረሰ እንጂ ሲሄድ ሳለ እንደመሸበት አይናገርም፡፡ ክስተቱ ሲፈፀም በቦታው እንደተገኘ ነው የሚናገረው፡፡ ይህ ጉዳይ በተከታዩ ጥቅስ ተጠናክሯል፡-

“ከዚያም መንገድን (ወደ ምሥራቅ) ቀጠለ፡፡ ወደ ፀሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነሱ ከበታችዋ መከለያን ባላደረግንላቸው ሕዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት፡፡” (ሱራ 18፡88-89)

ሰውየው ፀሐይ የምትጠልቅበትን ቦታ ከጎበኘ በኋላ በቀጥታ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በመሄድ ስትወጣ አገኛት፡፡ ከበታቿም ሰዎች ነበሩ፡፡ ይህንንስ እንዴት ይተረጉሙት ይሆን?

“አገኛት” የሚለው ቃል በአረብኛ “ወጀደሃ” ሲሆን በቁርአን ውስጥ በተለያየ መልክ 107 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ነገር ግን “ማየት” ወይም “አየ” የሚል ትርጉም የለውም፡፡ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ ስለማየት መናገር ከፈለግን “ረዐ” የሚለውን ቃል ነው የምንጠቀመው፡፡ ለምሳሌ ሱራ 6፡78 እንዲህ ይላል፡-

“ፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ (ረዐ) ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው» አለ፡፡”

የዘመናችን ሙስሊሞች ይህንን ያፈጠጠ ያገጠጠ ሳይንሳዊ ስህተት አለባብሶ ለማለፍና መጽሐፋቸውን ከስህተቱ ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም የቀደሙት እስላማዊ ምንጮች የእነርሱን ትርጓሜ ውድቅ በማድረግ ስህተቱን ያፀናሉ፡፡ አል-ዘመቅሻሪ የተሰኙ ሙስሊም ሊቅ መሐመድ ይህንን ጥቅስ የተረጎሙበትን መንገድ እንዲህ ይነግሩናል፡-

“አቡ ዘር (ከመሐመድ ወዳጆች መካከል አንዱ) በፀሐይ መግቢያ ሰዓት ከነቢዩ መሐመድ ጋር በመስጊድ ውስጥ ነበር፡፡

ነቢዩ መሐመድ እንዲህ ብለው ጠየቁት፡- “አቡ ዘር ሆይ የት እንደምትጠልቅ ታውቃለህን? እርሱም ‹አላህና መልእክተኛው የበለጠ ያውቃሉ› በማለት መለሰ፡፡ ነቢዩም ‹በድፍርስ ውሃ ውስጥ ነው› አሉ፡፡” [Al-Zamakhshari. Al-Kash-shaf; 3rd Edition, Volume 2, p. 743, 1987]

አል-በይደዊ የተሰኙ ሌላ ሊቅ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡-

“ፀሐይ የምትጠልቀው በድፍርስ ምንጭ ውስጥ፣ ማለትም ጭቃ ያለበት ምንጭ ውስጥ ነው፡፡ አንዳንድ የቁርአን አንባቢዎች ‹… ሞቃት ውሃ› በማለት ያነቡታል፡፡ ይህ ማለት ውሃው ሁለቱም ባሕርያት አሉት ማለት ነው፡፡ ኢብን አባስ ሙአዊያ ‹ሞቃት› ብሎ ሲያነብ እንዳገኘው ይነገራል፡፡ እርሱም ‹ጭቃማ ነው› ብሎ ነገረው፡፡ ሙአዊያም ወደ ካዕብ አል-አሕባር ‹ፀሐይ የት ነው የምትጠልቀው› የሚል ጥያቄ ላከ፡፡ ጥቂት ሰዎች በሚገኙበት ውሃና ጭቃ ውስጥ ነው በማለት መለሰ፡፡ ስለዚህ እርሱም ከኢብን አል-አባስ ሐሳብ ጋር ተስማማ፡፡”[Al-Baidawi. The Lights of Revelation; (p. 399]

አቶ ሐሰንና በማስረጃነት የጠቀሷቸው ዘመንኛ ሙስሊም መምህራን ከመሐመድና ከጥንታውያኑ ሙስሊም ሊቃውንት በላይ ያውቁ እንደሆን ይንገሩን፡፡
---------

ይቀጥላል. . .
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የቁርአን ኢ-ሳይንሳዊ መገለጦች
--------

ጋራዎች ምድር እንዳታረገርግ ይጠብቃሉ?

ቁርአን ጋራዎች የተፈጠሩበትን ምክንያት ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-

“ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ…” (ሱራ 31፡10)

“በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፡፡ ጂረቶችንም፣ መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ (አደረገ)፡፡” (ሱራ 16፡15)

“በምድርም ውስጥ በእነሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን፡፡ ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን፡፡” (ሱራ 21፡31)

አቶ ሐሰን ማብራርያ ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፡-

… ምድር ብዙ እንቅስቃሴዎችን እንደምታደርግ በሳይንስ ይታወቃል፡፡ በዛብያዋ አማካይነት በሰአት 1000 ማይሎችን እንደ እንዝርት ትሾራለች፡፡ በምህዋሯ አማካይነት ደግሞ በጸሐይ ዙርያ በሰአት 65000 ማይሎችን ትሽከረከራለች፡፡ እርሷና ሌሎች የከዋክብት ስብስቦችም በሰአት 20000 ማይሎችን ወደ መዳረሻቸው ይቀዝፋሉ፡፡ ምድር ይህን ሁሉ እንቅስቃሴ እያደረገች ግን አታረገርግም፡፡ ለሰው ልጅ ሕይወት ምቹ ናት፡፡ ይህ እንዲሆን ካደረጉ በርካታ ምክንያቶች መካከል የጋራዎች መኖር አንድ ምክንያት እንደሆነ አንቀጹ ያስረዳል፡፡ ይህ ነገር ሳይንሳዊ ነው፡፡ የዘመኑ የሳይንስ ሊቃውንት አረጋግጠውታል፡፡ ለአብነት የዶክተር ሞሪሳ ቡካይን <<The Bible the Quran and the science>> የተሰኘ መጽሐፍ ማንበብ ይቻላል፡፡ ታዋቂው የስነ ፈለክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዘጉል ነጃር ይህንኑ አጀንዳ የሚመለከት ጥናት አዛጅተዋል፡፡ (ገፅ 182)


ጸሐፊው በዘርፉ ሊቃውንት የተጻፈ ምንም ዓይነት የተጨበጠ ማስረጃ እንዳልሰጡ ልብ በሉ፡፡ ማውሪስ ቡካይሌ በመጽሐፉ ውስጥ እነዚህን ጥቅሶች በመጥቀስ ሳይንሳዊ ለማስመሰል ቢሞክርም የሕክምና ባለሙያ እንጂ የስነፈለክ ተመራማሪ ባለመሆኑ ከራሱ ግምት በመነሳት የሰጠው ሐተታ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ከሰጡት የበለጠ ዋጋ ያለው አይደለም፡፡

ዘጎሎል ኧል-ነጋር ኡስታዝ እንዳሉት የሥነ-ፈለክ ተመራማሪ ሳይሆኑ ጂኦሎጂስት ናቸው፡፡[www.elnaggarzr.com/en/aboutus.php] በዚህ ጉዳይ ላይ ትንታኔዎችን የመስጠት አቅም ሊኖራቸው ቢችልም ከምሑርነት ወደ ሙስሊም አቃቤ እምነት ያደሉ በመሆናቸው ሚዛኑን የጠበቀ ሐቀኛ መረጃ ከእሳቸው አንጠብቅም፡፡ ለምሳሌ ያህል እኚህ ሰው በአንድ ወቅት የግመል ሽንት መጠጣት “ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ” ለማስረዳት ሲሞክሩ በግብፅ ቴሌዢዥን ታይተዋል፡፡[http://www.clarionproject.org/blog/sharia-medicine-debate-about-benefits-drinking-camel-urine https://www.youtube.com/watch?v=r5nv292dN4c] ይህንን ያደረጉት ነቢዩ መሐመድ የሰጡትን ትዕዛዝ ሳይንሳዊ ለማስመሰል ነበር፡፡[Sahih Al-Bukhari; 7:71:623; 5:59:505; 1:4:234; 4:52:261; Sahih Muslim; 16:4131; 16:4130; 16:4132; 16:4134; Abu Dawud; 38:4356; 36:4357]

እኔ የመጀመርያ ዲግሪዬን በጂኦግራፊ ነው የሠራሁት፡፡ ብዙ የጂኦግራፊ መጻሕፍትን አንብቤያለሁ፤ ከተራሮች ጋር የተያያዙ ብዙ መረጃዎች አሉኝ፡፡ ነገር ግን ተራሮች በምድር ውስጥ በሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ምክንያት መፈጠራቸውን እንጂ እንቅስቃሴ እንዳይኖራት መከልከላቸውን የሚያረጋግጥ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ መረጃ አላየሁም፡፡ አቶ ሐሰን ከላይ ላቀረቡት “ሳይንሳዊ” ድምዳሜ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡ ይህንን ድምዳሜ ያገኙት ከየትኛው የሳይንስ መማርያ መጽሐፍ ወይም ጆርናል ነው? የመጽሐፉን ስም፣ ገጹንና የታተመበትን ዓመተ ምህረት እንዲጠቅሱልን እንፈልጋለን፡፡ የሁለት ግለሰቦችን ስም ጠቅሶ ማለፍ በምንም መስፈርት ይህንን ለመሰለ ግዙፍ አባባል ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከሙስሊም ወገኖች ጋር መሰል ውይይቶችን የምታደርጉ ክርስቲያን ወገኖች ሙስሊም ሰባኪያን ብዙ ጊዜ ማስረጃ የሌላቸውን መሰል አባባሎች ስለሚጠቀሙ ተጨባጭ ማስረጃ እንዲሰጧችሁ አጥብቃችሁ እንድትጠይቁ እንመክራችኋለን፡፡

አቶ ሐሰን ከተናገሩት በተጻራሪ እነዚህ ጥቅሶች ተራሮች ከላይ ወደ ታች የተጣሉ ለብቻቸው የተፈጠሩ አካላት በማስመሰል መናገራቸው ተራሮች በከርሰ ምድር እንቅስቃሴዎች ምክንያት ከምድር ውስጥ የወጡ የመሆናቸውን ሳይንሳዊ እውነታ ስለሚጣረስ ትክክል አይደለም፡፡

ይቀጥላል...
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ከመሥዋዕት ይልቅ ምህረትን እወዳለሁ” – ታድያ የኢየሱስ መሠዋት ለምን አስፈለገ?
==========
በማቴዎስ 9:13 ላይ “ከመሥዋዕት ይልቅ ምህረትን እወዳለሁ” ይላል፡፡ አምላክ “ከመስዋዕት ይልቅ ምህረትን እወዳለሁ” እያለ እንዴት ዓለም በሠራው ኃጢአት ምህረት ማድረግ ሲችል ኢየሱስን በማሠቃየት መሥዋዕት አደረገው?


ጠያቂው የጠቀሱት ክፍል ስለ እግዚአብሔር ምህረት ሳይሆን ሰዎች ለባለንጀሮቻቸው የሚያደርጉትን ምህረትና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት የተመለከተ ነው፡፡ ጌታችን ቃሉን የጠቀሰው ከትንቢተ ሆሴዕ 6፡6 ላይ ሲሆን በዕብራይስጥ “ኼሲድ” የሚለው “ምህረት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ሰው ለባለንጀራው የሚያሳየውን ቀና ባሕርይ ወይም ለእግዚአብሔር ያለውን ሎሌነት እንዲሁም እግዚአብሔር ከአገልጋዮቹ የሚጠብቀውን ሁሉ በጥቅሉ የሚያመለክት ነው፡፡ ሆሴዕ 6፡4 ላይ ይኸው ቃል “ፍቅር” ተብሎ ተተርጉሞአል፡፡ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ታማኝ ሳይሆኑ መሥዋዕት ማቅረብ በእርሱ ዘንድ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም (1ሳሙኤል 15፡22-23፣ ኢሳይያስ 1፡11-20፣ ኤርምያስ 7፡21-22፣ አሞፅ 5፡21-24፣ ሚክያስ 6፡6-8፣ ማቴዎስ 9፡13፣ 12፡7)፡፡ ስለዚህ የክፍሉ መልዕክት እግዚአብሔር ከሰው ለእርሱ ከሚቀርብ መስዋዕት ይልቅ ሰው ለባለንጀራው የሚያሳየው ምህረት እና ለእርሱ ያለው ታማኝነት ያስደስተዋል የሚል እንጂ ያለ ክርስቶስ መስዋዕትነት የሰው ልጆች ከኃጢአታቸው ይድናሉ የሚል አይደለም፡፡


ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጠያቂው ክፍሉን የተረዱበት መንገድ ትክክል ቢሆን እንኳ (ስህተት መሆኑ ይሰመርበት) ድምዳሜያቸው ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡


እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ገሃነም ከመላክ ይልቅ ምህረትን ቢያደርግ ደስ ይለዋል ነገር ግን ምህረትን መውደዱ ሰዎችን ሁሉ ወደ ገነት እንዲያገባ እንደማያደርገው ሁሉ ከመስዋዕት ይልቅ ምህረትን መውደዱ ያለ መሥዋዕት ኃጢአትን ይቅር እንዲል ያስችለዋል ወደሚል ድምዳሜ አይመራም፡፡ እግዚአብሔር አፍቃሪ አባት የሆነውን ያህል ፍትሃዊ አምላክም በመሆኑ ምክንያት በኃጢአተኞች ላይ እንዲፈርድ ፍትሃዊ ባሕርዩ ግድ ይለዋል፡፡ ነገር ግን ከሥላሴ አካላት መካከል አንዱ የሆነው ወልድ የኃጢአት ዕዳችንን በመክፈል ከእግዚአብሔር ፍትሃዊ ፍርድ ነፃ አውጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር ፍትህና የእግዚአብሔር ፍቅር በእኩል ሁኔታ የተገለጡበት ብቸኛ ቦታ ቢኖር የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የኢየሱስ ሞት ፍትሃዊ ነውን?
ጥያቄ

------------------------

አምላክ ፍትሃዊ ነው፡፡ ፍትህ ደግሞ በአንዱ ኃጢአት ሌላውን ያለመቅጣትን ይጠይቃል፡፡ “አምላክ እኛን ሊያድን ኢየሱስን መስዋዕት አደረገው” የሚለው አባባል የፍትህን ፅንሰ ሀሳብ አይፃረርምን? አንድ ሰው ሌላውን ገድሎ ወይም ወንጀል ፈፅሞ ፍርድ ቤት ቢቀርብና ዳኛው እርሱን በመቅጣት ፋንታ ልጃቸውን ቢቀጣ ፍትሃዊነት ይሆናልን?

መልስ

ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት ጥያቄ የሚጠይቅ ሙስሊም 6 መሠረታዊ እውነታዎችን ዘንግቷል

1. ሰዎችን በመስዋዕት አማካይነት ከኃጢአታቸው ማንፃት በአዲስ ኪዳን የተጀመረ ሥርኣት አለመሆኑን
በዘመነ ብሉይ ሰዎች እንስሳትን በመሰዋት ኃጢአታቸው ይሸፈንላቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የመስዋዕትን ሕግ ከመስጠቱ በፊት ይህንን ሥርኣት ሲፈፅሙ የነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህል አቤል (ዘፍጥረት 4፡3-5)፣ ኢዮብ (መጽሐፈ ኢዮብ 1፡5) ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የፋሲካው በግ መስዋዕትም ቢሆን እግዚአብሔር በሌዋውያን አማካይነት የሚፈፀመውን የመስዋዕት ሥርኣት ለሙሴ ከመስጠቱ በፊት የተደረገ በመሆኑ ከሕጉ በፊት እንደተፈፀመ ሥርኣት ይቆጠራል (ዘጸአት 12፡1-30)፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በእንስሳት መስዋዕት አማካይነት ሕዝቡን የማንፃት ሥርኣት ሰጠ (ዘሌዋውያን 6፡1-7፣ 16፡15-22)፡፡ ይህ ሥርኣት ከክርስቶስ እርገት በኋላ ለተወሰኑ ዓመታት ቢቆይም በ70 ዓ.ም. ከቤተ መቅደሱ መፍረስ ጋር ተያይዞ ቀርቷል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ እግዚአብሔር አዲስ ቃል ኪዳን ከሕዝቡ ጋር እንደሚያደርግ ተንብዮ ነበር (ኤርምያስ 31፡31-34)፡፡

2. ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ትንቢት መነገሩን

መሲሁ መስዋዕት ሆኖ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው እንደሚዋጃቸው አስቀድሞ የተነገረ በመሆኑ ሐዋርያት ወይም ከእነርሱ በኋላ የተነሱት ክርስቲያኖች የፈጠሩት ትምህርት አይደለም (ኢሳይያስ 53)፡፡

3. ክርስቶስ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ለመዋጀት በገዛ ፈቃዱ መምጣቱን
ጌታችን ወደ ምድር የመጣው እና ራሱን ስለ እኛ ቤዛ ያደረገው በገዛ ፈቃዱ እንጂ በማንም አስገዳጅነት አልነበረም (ዮሐንስ 10፡11፣ 10፡15፣ 10፡17-18 15፡13፣ ማርቆስ 10፡45)፡፡ ራስን ስለሌላው መስዋዕት ማድረግ ደግሞ የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ ተግባር አይደለም፡፡ የሚከተሉትን ተግባራት የፈፀሙ ሰዎች መጥፎ ሥራ እንደሠሩ መናገር ይቻል ይሆን?:-

የባንክ ሀራጅ የወጣበትን የወዳጁን ቤት እዳውን በመክፈል የታደገ ሰው፤
የመኪናው ፍሬን በመበላሸቱ ሕዝቡን ከእልቂት ለመታደግ በራሱ አቅጣጫ ከብረት ምሰሶ ጋር አጋጭቶ በማቆም የሞተ ሾፌር፤
ሕፃን ልጅ መሃል አስፓልት ላይ በመኪና ተገጭታ ከመሞቷ በፊት ገፍትሮ በማትረፍ የሞተ ሰው፤
ጓደኞቹን ለማትረፍ በፈንጂ ላይ ተራምዶ የሞተ ወታደር፤
በከባድ በሽታ የታመመ ሰው ስታክም ተበክላ ሕይወቷን ያጣች ዶክተር፤
ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዳይገደል በመሸፈን በጥይት ተመትቶ የሞተ አጃቢ፤
እነዚህን ድርጊቶች በፈቃደኝነት የሚፈፅሙ ወገኖች እንደ ጀግና ይወደሳሉ እንጂ አይወቀሱም፡፡ ጌታችንም እኛ ልንከፍለው የማንችለውን የኃጢአት እዳችንን በመክፈል ነፃ አውጥቶናል፡፡ እርሱ እዳችንን ባይከፍልልን ኖሮ የመዳን ተስፋ አልነበረንም፡፡ የእርሱ ተግባር እኛን ለማትረፍ በፈቃደኝነት የተፈፀመ መስዋዕትነት በመሆኑ የፍትህ ጥያቄን የሚያስነሳ አይደለም፡፡

4. የሌላውን ሰው ዕዳ መክፈል ፍትሃዊ መሆኑን
በሰው የፍትህ ሥርአት ውስጥ አንዱ ስለሌላው የማይቀጣባቸው ብዙ ጉዳዮች ቢኖሩም ነገር ግን አንዱ ለሌላው የሚቀጣባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው ያለበትን የገንዘብ ዕዳ ራሱ መክፈል የማይችል ከሆነ ሌላ ሰው በፈቃደኝነት በመክፈል ከቅጣት ሊያተርፈው ይችላል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከጌታው ለሸሸው እና ባለ ዕዳ ለሆነው ኦናሲሞስ ለተሰኘ ባርያ ይህንን አድርጎ ነበር (ፊልሞና 1፡17-19)፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኃጢአት ሙስሊሞች እንደሚሉት “ወንጀል” ሳይሆን መከፈል ያለበት እዳ ነው (ማቴዎስ 18፡21-35፣ ሉቃስ 7፡36-50፣ ቆላስይስ 2፡13-15)፡፡ እዳን በመክፈል ባለ እዳውን ከቅጣት ማትረፍ በምድራዊው የሰው ፍትህ ሥርአት ውስጥ እንኳ ተቀባይነት ያለው ተግባር ነው፡፡

5. እግዚአብሔር ሉኣላዊ ሥልጣን እንዳለው
ሰዎች የአንዱን ኃጢአት በራሳቸውም ሆነ በሌላ ሰው ላይ የማኖር መብትም፣ ስልጣንም ሆነ ችሎታ የላቸውም፡፡ የእግዚአብሔር ሥልጣን ግን ሉኣላዊ በመሆኑ የገዛ እዳችንን ወደ ራሱ በማስተላለፍ ሊከፍልልን ይችላል፡፡ ከሥላሴ አካላት መካከል አንዱ የሆነው ወልድ ወደ ምድር በመምጣት በኛ ምትክ ሆኖ የኃጢአት እዳችንን በመክፈል ነፃ አወጣን (2ቆሮንቶስ 5፡17-21፣ ዮሐንስ 1፡29፣ 10፡14-18፣ ገላቲያ 2፡20፣ ቆላስይስ 1፡13-23፣ 2፡13-15፣ ራዕይ 1፡5-6)፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ማድረግ ከወደደ ስጦታውን በታላቅ አክብሮትና ምስጋና ከመቀበል ውጪ የእርሱን ሉኣላዊነት እንቃወም ዘንድ እኛ ማን ነን?

6. በመስዋዕት መቤዠት በክርስትና ብቻ ሳይሆን በእስልምና ሃይማኖትም ውስጥ የሚገኝ መሆኑን
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኘውን የመስዋዕት ሥርኣትም ሆነ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛነት በመቃወም የሚጽፉና የሚሰብኩ ሙስሊሞች በገዛ መጻሕፍታቸው ውስጥ ተመሳሳይ ትምህርቶች ሰፍረው መገኘታቸውን አለማወቃቸው የሚያስገርም ነው፡፡ አላህ አብርሃምን ልጁን እንዲሰዋ እንዳዘዘው ቁርአን ናገራል፡፡ አብርሃም የታዘዘውን በማድረግ ፈተናውን ማለፉን ካረጋገጠ በኋላ ልጁ እንዳይገደል እንዴት እንዳተረፈው ሲናገር፡- “በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው” ይላል (ሱራ 37፡106)፡፡ በመስዋዕት መቤዠት ለዘመናችን ሙስሊም ሰባኪያን እንግዳ ቢሆንም ላለፉት 14 ክፍለ ዘመናት በቁርአን ውስጥ ተጽፎ የተቀመጠ ትምህርት ነው፡፡

በሌላ ቦታ ላይ ቁርአን መስዋዕትን የማቅረብ ትዕዛዝ ከሙስሊሞች በፊት በነበሩት ሕዝቦች ሁሉ ላይ እንደተደነገገ ይናገራል፡- “ለሕዝብም ሁሉ (ወደ አላህ) መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡” (22፡34)፡፡ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ባለመሰጠቱ ይህ ጥቅስ “ለሕዝብም ሁሉ” በማለት ክርስቲያኖችን በማካተት የተሳሳተ መረጃ ቢያስተላልፍም ነገር ግን መስዋዕት ማቅረብ ከአምላክ የተሰጠ ትዕዛዝ መሆኑን በመመስከር የዘመናችን ሙስሊሞች የሚያስተምሩትን ትምህርት ውድቅ ያደርጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሙስሊሞች ወደ ገነት መግባት ይችሉ ዘንድ አላህ የእነርሱን ኃጢአት በአይሁድ እና በክርስቲያኖች ላይ በማስቀመጥ ወደ ገሃነም እንደሚልካቸው እስላማዊ ሐዲሳት በብዙ ቦታዎች ላይ ያስተምራሉ፡-

“አቡ ቡርዳ አባቱን ዋቢ በማድረግ እንዳስተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡- ከሙስሊም አንድም አይሞትም አላህ በእርሱ ፋንታ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን በገሃነም ውስጥ የሚጥል ቢሆን እንጂ፡፡” [Sahih Muslim, Book 037, Number 6666; number 6665]

በሌሎች ዘገባዎች ደግሞ በእለተ ትንሣኤ ሙስሊሞች ተራራ የሚያካክሉ ኃጢአቶቻቸውን ተሸክመው እንደሚመጡና አላህ ይቅር ብሏቸው በእነርሱ ፋንታ አይሁድ እና ክርስቲያኖችን ወደ ገሃነም እንደሚልክ ተጽፏል፡፡[Sahih Muslim, Book 037, Number 6668]
ሙስሊሞች በኢየሱስ ቤዛነት ባያምኑም የእርሱ የሥጋ ዘመዶች በሆኑት በአይሁዳውያንና የእርሱ ተከታዮች በሆኑት በክርስቲያኖች ቤዛነት ያምናሉ ማ
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ለት ነው፡፡ ፍፅምና የሌላቸው አይሁድ እና ክርስቲያኖች የኃጢአት እዳቸውን መክፈል እንደሚችሉ ለማመን ያልከበዳቸው ሙስሊም ወገኖቻችን ንፁህና ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ የኃጢአታቸውን ዕዳ የመክፈል ብቃት እንዳለው ማመን ለምን ይሆን የከበዳቸው?