ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የ አይሻ ቤት ወይስ የ አይሸ ቀሚስ?

እውቀት አልባውን ሙስሊም ሰብስቦ ሲያስጨፍር የሚውል አንድ 'ጥንጥ' ጭንቅላት የተሸከመ ሕይወቱን ሙሉ ሲንከራተት ያሳለፈና ምን ማመን እንዳለበት እንኳን የማያውቅ አንድ 'ኡስታዝ ነውም ይሉታል'፣ አለ። ልክ በራሱ አጥንቶ እንዳመጣ ሰው፣ ነብዩ ሙሓመድ 'የ አይሻ #ቀሚስ ውስጥ ካልሆነኩ ወሒ(መገለጥ) አይመጣልኝም' ብሎ የተናገሩትን፣ "የ አይሻ #ቤት" ማለት ነው ብሎ ሙግቱን አቅርቧል።ክርስቲያኖችም ይህንን መረዳት ያልቻሉበት ምክኒያት ከ ጎግል ስለሚጎረግሩት እንጂ እውቀት ስላላቸው እንዳልሆነ ተናግሯል። የሚገርመው ነገር ግን ይህ ሰው ሙግቱን ቃል በ ቃል 'Answering Christianity' ከተሰኘ ድሕረ ገፅ  በ 'ኦሳማ አብዱላህ' ከተፃፈው አርቲክል እና 'አቡአልራብ' የሚባል ሰው ከፃፈው አርቲክል ኮፒ ፔስት ማድረጉ እጅጉን ፈገግ የሚያደርግ ነው። "ሌባ እናት ልጇን አታምንም" ይሉ ይለ?

ሳሂህ አል ቡኻሪ መፅሓፍ 51 ሓዲሥ 16

ነብዩ እንዲህ ብሏል "...ወሒ(መገለጥ) በ አይሻ ቀሚስ(ሠውብ 'ثوب') ውስጥ(في) ካለሆነ በ ሌሎች ሴቶች ቀሚስ ውስጥ አይመጣልኝም።"
فدار إليها فكلمته فقال لها ‏ ‏لا تؤذيني في ‏ ‏عائشة ‏ ‏فإن الوحي لم يأتني وأنا في ثوب امرأة إلا ‏ ‏عائشة.

ሳሂህ ሙስሊም መፅሓፍ 31 ሓዲዝ 5907

زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم وَعُثْمَانَ حَدَّثَاهُ أَنَّ أَبَا بَكْرٍ اسْتَأْذَنَ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ مُضْطَجِعٌ عَلَى ِرَاشِهِ لاَبِسٌ ِرْطَ عَائِشَةَ
Abu Bakr requested permission from the prophet to enter when the prophet was lying down on Aisha’s #bed wearing her #garment (mirt)
"አቡ በከር ነብዩ ወዳሉበት ክፍል ለመግባት ፍቃድ ጠየቀ። ነብዩም በ አይሻ #ፍራሽ ላይ የሷን #ቀሚስ(mirt) ለብሶ ጋደም ብሎ ነበር።"

ነብዩ በ እርግጥ የሴት ልብስ እንደሚለብሱና መገለጥም በሱ ውስጥ እንደሚመጣላቸው መናገራቸው ግልፅ ነው። እነኚህ የሙሃመድ "ጠባቂያን" ግን ይህንን የሚያክል አሳፋሪ ድርጊት ለመሸፈን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም።

የ ሙስሊም ነኝ ባዩ ሙግት እንዲህ የሚል ነው፦

"ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ......ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” #ፍራሽ ወይም #ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው..."

ይሄ ሙግት በጣም የወረደ መሆኑን ላስነብባቹ።

1. ነብዩ "ለበሱ" የተባለው " ሠውብ" ብቻ አይደለም። "ሚርት" ተብሏል።ትርጉሞቹን እንመልከት

ሠውብ፦ ከ ዲክሺነሪ
ثَوْب
apparel
- clothes worn on a special occasion
(ልዩ የሆነ ቀን ላይ የሚለበስ ልብስ)
- clothes; dress(ልብስ፣ቀሚስ)

2. "ሚርት"
 እውነት ሓዲዙ የሚነግረን ነብዩ መገለጥ ይመጣልኛል ያሉት የ አይሻ #ቤት ወይም #ፍራሽ ላይ እንጂ የሷ ቀሚስ ውስጥ አይደለምን?

ከ ላይ እንዳነበብነው፣ ሳሂህ ሙስሊም 5907 እንዲህ ይላል፦
"አቡ በከር ነብዩ ወዳሉበት ክፍል ለመግባት ፍቃድ ጠየቀ። ነብዩም በ አይሻ #ፍራሽ فِرَاشِهِ ላይ የሷን #ቀሚስ(ሚርት) ለብሶ ጋደም ብሎ ነበር።"

ልብ በሉ፣ በዚህ ሓዲዝ ላይ በ ግልፅ "ፍራሽ" እና "ልብስ" ሁለት የተለያዩ ቃላቶች ሆኖ ተቀምጧል።
A. ነብዩ ምን ላይ ነው የተኙት? መልሱ፦ የ አይሻ ፍራሽ
B. ነብዩ ምን ለብሶ ነበር?፦ የ አይሻ ቀሚስ

ስለዚህ በ ሌሎች ሓዲሣት ውስጥ ነብዩ "በ አይሻ ቤት ውስጥ እንጂ በሌሎች ሶቶች ቤት ውስጥ መገለጥ አይመጣልኝም (ሙስነድ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293") ብለው እንደተናገሩ ተደረጎ የተፃፉ፣ ነብዩ የ አይሻ ልብስ አይለብሱም ማለት አይደለም። ይልቁንስ ከላይ ባነበብነው ሓዲሥ መሠረት "በ አይሻ ቤት ውስጥ የሷን ቀሚስ ለብሶ" ማለት ነው እንጂ።

በተጨማሪም "ሚርት" የሚለበሰው በ ሴቶች #ብቻ መሆኑን የ ሙስሊሞች መፃሕፍት መስክሯል። ምሳሌ፦

ፈትሁል ባሪ፣ የ ሳሂህ አልቡካሪ ማብራሪያ (ኢማም ኢብን ሓጀር አል አስቀላኒ) ቅጽ 2፤
Volume 2፦ The Book of Prayer Times; Chapter of Dawn Prayer

"..'ሚርት' ተብሎ የሚጠራ ልብስ በ ሴቶች #ብቻ የሚለበስ ነው" ይላል።

#የሴት_ልብስ_መልበስ_በ_ሓዲሣት_ህግ

ሱናን አቡ ዳውድ 4098
Narrated AbuHurayrah:

The Messenger of Allah (ﷺ) cursed the man who dressed like a woman and the woman who dressed like a man. (Sahih)
حَدَّثَنَا زُهَيْرُ بْنُ حَرْبٍ، حَدَّثَنَا أَبُو عَامِرٍ، عَنْ سُلَيْمَانَ بْنِ بِلاَلٍ، عَنْ سُهَيْلٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الرَّجُلَ يَلْبَسُ لِبْسَةَ الْمَرْأَةِ وَالْمَرْأَةَ تَلْبَسُ لِبْسَةَ الرَّجُلِ ‏.‏
:  (  صحيح   (الألباني)
"ነብዩ እንዲህ ብሏል፦ 'የ ሴት ልብስ(እንደሴት) የሚለብስ  ወንድ ወይም የ ወንድ ልብስ የምትለብስ ሴት #የተረገመ/ች ነው/ናት"

መደምደሚያ:

ነብዩ የሴት ልብስ ይለብሱ ስለ ነበረ እራሳቸው በተናገሩት ንግግር መሠረት #የተረገሙ ናቸው ማለት ነው!! አከተመ።

ነብዩ ለ እርግማናቸው የሞተውን ክርስቶስ ለመቀበል ሁለተኛ እድል አይሰጣቸውም። ይህን ፅሁፍ የምታነብ ሙስሊም ግን ማምለጥ ትችላለህ። የሞተልህን ክርስቶስ ተቀበል!!!

 " እንግዲህ። በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:24)
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified