ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
እውነት አላህ የቁርኣን ጠባቂ ነው ተብሏልን? The Islamic Dilemma

ሙስሊሞች ከሚያነሱት ሙግቶች አንዱ፣ ቀጥሎ ያለው ነው:

"መፅሐፍ ቅዱስ የተበረዘው ሰዎች ጠባቂዎቹ ስለተባሉ ሲሆን የቁርአን ጠባቂ ግን አላህ ነው ተብሏል።"

የሚጠቅሱትም ሱራ ይሄ ነው: ሱራ 15:9

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

እኛ "ቁርኣንን" እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

ነገር ግን እዚህ ላይ "ቁራኣን" ተብሎ የተተረጎመው - "አል-ዚክራ" የሚል ቃል እንጂ ቁርአን አይደለም

ዚክር- ማለት "reminder- ማስታወሻ፣ admonition- ምክር" ማለት ነው።

ታድያ መፅሐፍ ቅዱስ ዚክር አልተባለምን? መልሱ ተብሏል ነው።

ሱራ 21:48

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን (ወዚክራ) በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡

ሱራ 16:43

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ #الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ #የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ أَهْل الذِّكْرِ (አህላል-ዚክሪ) የሚለውን- የዕውቀትን ባለቤቶች ብለው ተርጉሞውታል። ኢብኑ ከሢር ግን በተፍሲራቸው አህለል ዚክር ማለት "the people of the previous Books" " የቀድሞ መጽሓፍት ባለቤቶች" ማለት እንደሆነ አስቀምጧል ።

ስለዚህ ለሙሴ የወረደውና ከቁርኣን በፊት የወረዱት መፅሓፍት "ዚክር" ከሆኑ፣ ሙግቱ ቀጥሎ ያለው ይሆናል:

1- አላህ ዚክሩን ያወረድነው እኛው ነን፣ እኛው ጠባቂዎቹ ነን ካለ እና ተውራት ዚክር ከሆነ፣ ተውራት ተበርዟል ካልን አላህ ውሸታም መሆኑ ነው። ምክኒያቱም አልጠበቀውማ።

2- አይ፣ ተውራት አልተበረዘም ከተባለም፣ አላህ ውሸታም ይሆናል። ምክኒያቱም ፔንታቱክ የምንላቸው ወይም "ተውራት" ውስጥ እግዚአብሔር ያስተማረው የቁርአን ተቃራኒ ናቸው።

ለምሳሌ: ዘጸአት 4

23 እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።

እንደ ቁርአን ትምህርት ግን አላህ ባሪያ እንጂ ልጅ የለውም!

3- አይ፣ ኦሪት ከተውራት ይለያል አልተጠበቀም ወይም አሁን ላይ ተውራት ጠፍቷል ከተባለም፣ አላህ መጀመሪያ ያወረደውን ዚክር አሁንም መጠበቅ አልቻለም ማለት ነው።

Hence, Islamic Dilemma! Damned if you do, damned if you don't!😄
👍2111😁10🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ዚክር ለጠየቃችሁት ሙግት።
👍11😁7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በፍጥረታት አለም ውስጥ አንድ አካል ሆኖ ሁለት የተለያዩ ምንነት (Nature) ያላቸው ምሳሌዎች እውነት የሉምን? ክርስቶስ ሁለት Nature ስላለው Opposing ምንነት ነውን?
👍19🔥98😁2😱2
እየሱስ እንዴት ከመጥምቁ ዮሐንስ ቀድሞ Exist አደረገ?

ዮሃ 1:30
አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ #ከእኔም #በፊት #ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

#ነበር የሚለው የግሪክ ቃል፣ "ኤን" የሚልው imperfect verb ሲሆን፣ Aspectቱ ያልተገደበ Continuous past existence የሚገልፅ ነው።

አሁን፣ ከኢየሱስ በፊት ዮሃንስ ቀድሞ ተወልዶ ሳለ፣ እንዴት እየሱስ ከሱ ቀድሞ ነበር ተባለለት?

መልስህ፣ አይ፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ እንጂ በገሃድ አይደለም ካልክ፣ ጥያቄው የሚሆነው፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ አንዱ ከሌላው ቀድሞ ይታወቃል እንዴ? አምላክ ስለ እየሱስ አስቀድሞ አውቆ፣ ስለ ዮሃንስ ያላወቀበት ጊዜ ነበር እንዴ? ይህ ማለት፣ አምላክ ሁልጊዜም ሁሉን አዋቂ አልነበረም ብሎ የሚያምን ሰው የሚያመጣው ትርጉም ስለሆነ ደካማ ሙግት ነው።

Unless of course, the Son of God LITERALLY existed from eternity 🙂
23👍11
🤣 Odd Number? Why?
😁40😱8