ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ለምን አልሰለምኩም?
ሰልማን-3.pdf
"ንቁ" ላይ የተሰጠ ሒስና ግምገማ-3
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
በእስልምና መሠረት ሐዋርያው ጳውሎስ የአላህ መልእክተኛ ነው http://www.ewnetlehulu.org/am/paul-apostle
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
ለሰልማን መጽሐፍ የተሰጠውን ምላሽ ክፍል 3 ያንብቡ፡፡ የሰልማን ስህተቶች አስቂኝ ናቸው፡፡ ዘና በሉበት 👇👉😊 http://www.ewnetlehulu.org/am/sel-book-review-3/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
መሐመድ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰችውን አይሻን ስለ ማግባቱ
ለሙስሊሞች ምላሽ የተሰጠ ምላሽ http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/mo_marriage_to_aisha/
ኦሮምኛ ተናጋሪዎች እንኳን ደስ አላቹ!

"ለምን አልሰለምኩም" ቻናል ከዛሬ ጀምሮ በኦሮምኛ በሌላ አዲስ ቻናል ስራ ጀምሯል። በዚህኛው ቻናል ላይ የተፃፉትን በተቻለ መጠን መተርጎም እንጀምራለን።

ሊንኩን ተጭናቹ መግባት ይቻላል።
https://tttttt.me/Jesuscrucified_oromo
ኡስታዝ አቡ ሃይደር ሃላባ ላይ ኮንፍራንስ ከአካሔደ በኋላ ቤተ-ክርስቲያናትን ማቃጠልና ሰዎችን መግደል ተጀምሯል። #አል-ሃቅ የሚል ቻነል ላይ ከ ፎቶግራፍ ማስረጃ ጋር ታገኛላቹ። ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናቹ እዩ፦

@JESUS_ALHAQ
@JESUS_ALHAQ

ኦሮምኛውን ማንበብ ለምትፈልጉ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭናቹ ግቡ
@Jesuscrucified_oromo
@Jesuscrucified_oromo
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የሚጽፉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው!
ኢየሱስ ለእስራኤል ቤት ብቻ? 👉👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/jesus-mission-is-universal/
ቁርአንስ ተጠብቋልን.pdf
476.3 KB
የቁርአን ማኑስክሪፕቶችስ ተጠብቋልን??

አጭር ጽሁፍ ከባለፈው የቀጠለ

ሳሂህ ኢማን

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
➡️ለምን ይዋሻል- ዶኩመንተሪ⬅️

🔔ማንም ሰው እንዳያመልጠው🔔

የሙስሊሞች ቅጥፈት ከሳይንስ እስከ ሙሓመድ ነብይነት ሲጋለጥ

👉አዘጋጅ ሳሂህ ኢማን

Notice: በ"ለምን አልሰለምኩም አፖሎጄቲክስ ቲም" ውስጥ ሁለት ሓኪሞች እንደመኖራችን መጠን፣በቪድዮው ውስጥ ቁርአንና ኢምብሪዮሎጂ ይሚለውን ክፍል በጥንቃቄ አይተናል። ስለዚህ፣ ዶኩመንተሪው accurate መሆኑንና ቁርአንን በኢምብሪዮሎጂ አይን እንይ ከተባለ ቁርአንና ኢስላም ቁልቁል የሚገቡ መሆኑን ያለ ምንም ጥርጥር እንገልፃለን። ቪድዮው 2 ሰአት ቢሆንም ማንም እንዳያመልጠው እናሳስባለን።

➡️ለምን አልሰለምኩም?? አፖሎጄቲክስ

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የአሕመድ ዲዳት አስደንጋጭ ቅጥፈቶች
ሙስሊም ዳዒዎች እስልምና “እውነተኛ” ሃይማኖት መሆኑን ለማሳየት የሚጠቀሙባቸው ስልቶ በእጅጉ አስገራሚ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች ከአውዳቸው ገንጥሎ በማውጣት በማጣመም ከመተርጎም አንስቶ ራሳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ቋንቋዎች ሊቃውንት በማስመሰል በማቅረብ ግልጽ ቅጥፈቶችን እስከመፈጸም ሲደፍሩ ይስተዋላሉ። ለዚህ እንደ ምሳሌ ሊነሱ ከሚችሉት ግለሰቦች መካከል አሁን በሕይወት የሌሉት ደቡብ አፍሪካዊው አሕመድ ዲዳት ይጠቀሳሉ። በዚህ ጽሑፍ “Christ In Islam” በሚል ርዕስ ተጽፎ “ክርስቶስ በኢስላም” ተብሎ ወደ አማርኛ በተመለሰው አነስተኛ መጽሐፋቸው ውስጥ የፈጸሟቸውን ቅጥፈቶች ለአንባቢያን እናቀርባለን። በመጽሐፉ ገፅ 55 እና 56 ላይ “ግሪካዊ እንጂ ዕብራይስጥ አይደለም” በሚል ርዕስ ስር በጻፉት ጽሑፍ ሚስተር ዲዳት የአዲስ ኪዳን ግሪክ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው በማስመሰል ራሳቸውን ለአንባቢያን ያቀርባሉ፡፡ አገልጋይ ከመሆኑ በፊት የግሪክ ቋንቋን ለአምስት አመታት ካጠና አንድ የሥነ መለኮት ሊቅ ጋርም ያደረጉትን ውይይትና ሊቁን እንዴት በክርክር እንደረቷቸውና እንዳሳፈሯቸው ይናገራሉ፡፡
ዲዳት እንዲህ ይላሉ፡ “ብጹዕነታቸውን የግሪክ ቋንቋ ያውቁ እንደሆን ጠየቅኳቸው? <አዎ> አሉ፡፡ የብጹዕነት ማእረጋቸውን ከማግኘታቸው በፊት ለአምስት ዓመታት የግሪክ ቋንቋ ማጥናታቸውን አረጋገጡልኝ፡፡ ‹ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ› በሚለው አንቀፅ ውስጥ ‹እግዚአብሔር› (God) ለሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ የተሰጠው ትርጉም ምንድነው? በማለት ጠየቅኩ፡፡ አፈጠጡብኝ፣ መልስ ለመስጠት አልደፈሩም፡፡ ሆሲዬስ (HOTHEOS) የሚለው ቃል እንደሆነ ነገርኳቸው፡፡” [አነባበቡን ተርጓሚው በትክክል አላስቀመጠም፡፡ ሆስዬስ ሳይሆን ሆቴዎስ ነው፡፡]

ሚስተር ዲዳት ቅጥፈታቸውን ከዚህ ይጀምራሉ፡፡ “ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ” በሚለው ውስጥ “እግዚአብሔር” የሚለው ቶንቴዎን (TONTHEON) እንጂ ሆቴዎስ (HOTHEOS) አይደለም! ሚስተር ዲዳት ዋሽተዋል!
ይቀጥላሉ ሚስተር ዲዳት፡ “ለብጹዕነታቸው የሚከተለውን ጥያቄ አቀረብኩ ‹ቃልም እግዚአብሔር ነበር (and the word was God) በሚለው ሐረግ እግዚአብሔር (God) ለሚለው ቃል የግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠው ትርጉም ምንድነው?› ብጹዕነታቸው ዝም አሉ፡፡ የግሪክ ቋንቋ ስለማያውቁ አልነበረም፡፡ ወይም ግሪክ አውቃለሁ በማለት አልዋሹም፡፡ ነገሩ ገብቷቸዋል፡፡ እንደተሸነፉ አረጋግጠዋል፡፡ አዎ and the word was God በሚለው አንቀፅ ውስጥ ለሚገኘው ‹God› ለሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ በተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠው ትርጉም ‹ቶንቲዎስ› (TONTHEOS) ነው፡፡”

ሚስተር ዲዳት በድጋሜ ዋሽተዋል! “ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” በሚለው ውስጥ እግዚአብሔር ለሚለው በግሪክ ቋንቋ የገባው ቃል ቴዎስ (THEOS) የሚል እንጂ ቶንቴዎስ (TONTHEOS) የሚል አይደለም! በግሪክ ቋንቋ ቶንቴዎስ የሚል የቃል አጠቃቀም የለም፡፡ ከግሪክ ቋንቋ ስነ ልሳን አኳያም የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ሚስተር ዲዳት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የአብና የኢየሱስን አምላክነት ለመግለፅ ሐዋርያው ዮሃንስ አንዱን ቃል በተለያዩ መንገዶች በመጠቀሙ ምክንያት “አብ ትልቅ አምላክ ሲሆን ኢየሱስ ደግሞ ትንሽ አምላክ ነው” የሚለውን የይሖዋ ምስክሮች ያረጀ ክርክር ነው ለመጠቀም የሚሞክሩት፡፡ ይሁን እንጂ የክርክሩንም አካሄድ ሆነ የግሪኩን ቃላት አልተረዱም፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ አንድን የሥነ መለኮት ሊቅ እንደረቱና እንዳሳመኑ ጽፈዋል፡፡ እንግዲህ ይህ ታሪክ የሚስተር ዲዳት ፈጠራ መሆኑና እሳቸውም ምላሳቸውን አጣፍጠው ምሁር መስለው ለመታየት ቢሞክሩም ነገር ግን ሐሳዊ መምህርና አታላይ መሆናቸው በዚህ ታሪክ ውስጥ ለተጠቀሰው ምናባዊ “የሥነ መለኮት ሊቅ” ካልሆነ በስተቀር ለማናችንም ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ ስለምን እንዲህ ዓይነቶቹን ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸውንና ለእውነት ግድ የሌላቸውን ሐሰተኛ መምህራን በመከተል ነፍሳችሁን ታጠፋላችሁ? እስከ መቼስ በሕይወታችሁ ትቀልዳላችሁ? እስከ መቼስ ትታለላላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ የልብ ዓይኖቻችሁን በመክፈት ወደ እውነት ይመራችሁ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው። http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/deedat_lies/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የምክር_ቃል_ለስደተኛዋ_ቤተክርስቲያን
ክርስቶስን መከተል ወንጀል በሆነባቸው አካባቢዎች ድልን ለመቀዳጀት የሚረዱ ስልቶች
_________//_______

በጥንቷ ሮም ውስጥ ቤተክርስቲያን ለ300 ዓመታት ያህል ክፉኛ ስትሰደድ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ የመጀመርያው ክርስቲያን ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እስከነገሠበት ጊዜ ድረስ ለቤተክርስቲያን ታስቦ የተሠራ ሕንፃ አንመለከትም፡፡ ክርስቲያኖች በግላጭ አይሰበሰቡም ነበር፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሮም ውጪ “ካታኮምብ” የተሰኙ ዋሻዎች ይገኛሉ፡፡ በእነርሱ ውስጥ ክርስቶስን የሚያከብሩ ጽሑፎችን እንመለከታለን፡፡ የክርስትና ምልክት የሆነው ታዋቂው የዓሣ ምስል ከዚህ ዘመን የመጣ ነው፡፡ አማኞችን ለይቶ ለማወቅ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ ዓሣን የሚያመለክተው የግሪክ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅና አዳኝ የሚል ምህፃረ ቃል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ አንድ ሰው ቢያጋጥማችሁና ክርስቲያን መሆኑን እርግጠኞች ካልሆናችሁ ግማሽ የዓሣ ምስል ትስሉና ሰውየው ክርስቲያን ከሆነ ይጨርሰዋል፡፡
የመጨረሻውና አስከፊ የሚባለው ስደት በንጉሥ ዲዮቅላጢስ ዘመን የተደረገው ነው (284-305 ዓ.ም.)፡፡ ራሱን አምላክ ስላደረገ በሮም ግዛት የነበረ ሰው ሁሉ ለእርሱ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ መሥዋዕት ካቀረባችሁ በኋላ መስማማታችሁን የሚገልፅና ለባለሥልጣናት የምታሳዩት ምልክት ይሰጣችኋል፡፡ ያንን ካላደረጋችሁ ልትገደሉ ትችላላችሁ፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ባለመስማማታቸው ምክንያት ተገድለዋል፡፡ አንዳንዶች በእሳት ተቃጥለዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ በጫወታ አደባባዮች ውስጥ ለዱር አውሬዎች ተጥለዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ያልተለመደ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ሰዎች ክርስቲያኖች ለስደት የሰጡትን ምላሽ በመመልከት ማመን ጀመሩ፡፡ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ጠርጡሊያኖስ እንደተናገረው “የሰማዕታት ደም የቤተክርስቲያም ዘር ነው፡፡” እነዚህ ሰዎች መሥዋዕቱን በመሠዋት ብቻ ከሞት ማምለጥ ይችሉ ነበር ነገር ግን ያንን በማድረግ ጌታን ከማቃለል ሞትን መርጠዋል፡፡ ይህ ሌሎችን ገድሎ መሞትን ከሚያስተምረው የእስልምና የሰማዕትነት አስተሳሰብ ምንኛ የተለየ ነው! http://www.ewnetlehulu.org/am/forchristians/church-response-for-persecution/
Greek-Selman.pdf
675.7 KB
የሰልማን ግሪክ

ተዋረድ ያለው አብዱል ግሪክ ይጠቅሳል

ማንም እንዳያመልጠው፣ ተዝናኑበት

Dan Beltshazar

Website for similar articles

http://www.ewnetlehulu.org

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
ከላይ የተለጠፈውን "የሰልማን ግሪክ"፣ በዚህ ድረገጽ ገብታቹ ማንበብ ትችላላቹ።

http://www.ewnetlehulu.org/am/sel-greek/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የመሐመድ መገለጥ ከሰይጣን ዘንድ ከሆነ መልካም ትምሕርቶች እንዴት በውስጡ ሊገኙ ቻሉ? www.ewnetlehulu.org/am/wolf-in-sheep-clothing/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
ውበት የእውነት መለኪያ ሊሆን ይችላልን?

የቁርአን ሚዛን አመክንዮአዊ ችግሮች www.ewnetlehulu.org/am/quran-aesthetics/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የሙስሊሞች አስገራሚ ሙግት
እግዚአብሔር ምላጭ ተከራየ?
ኢሳይያስ 7:20 “በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ፤ የራሱንና የእግሩን ጠጉር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል” ይላል፡፡ አምላክ ምላጭ ይከራያልን? ሁሉን የፈጠረና ዓለሙ ሁሉ የርሱስ አይደለምን? ጸጉር ይላጫልን? ተራ የሰው ማህበራ ድርጊቶቹን ሁሉ የፈጣሪ እለታዊ ድርጊት እንደሆኑ አድርጎ መግለፅ ለፈጣሪ ያለንን እሳቤ በብዥታ የተሞላ አያደርግምን?

“ምላጭ” የተባለው የአሦር ንጉሥ መሆኑ በግልፅ እየታየ ይህ ጥያቄ መነሳቱ በራሱ በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡ ይህ ቃል እግዚአብሔር እርሱን በማያቀውቀው፣ ጣዖት አምላኪ በሆነው የአሦር ንጉሥ ተጠቅሞ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ጠላት የሆነውን ኤፍሬምን እንደሚያዋርድ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው፡፡ (መላጨት የኀዘንና የውርደት ምልክት ነው 2ሳሙኤል 10፡4፣ ኤርምያስ 41፡5፡፡) ይህ ነጥብ የሙግት ሐሳብ ሆኖ መቅረቡ በራሱ እጅግ አስቂኝ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሙስሊም ወገኖች ይህንን ነጥብ “ከጠንካራ” ሙግቶቻቸው መካከል እንደ አንዱ በመቁጠር በተደጋጋሚ ማንሳታቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞች አንዱ የጻፈውን በመያዝ በደመነፍስና በድርቅና ከመከራከር በዘለለ ክፍሉን አውጥቶ የማንበብ ልማድ የላቸውም፡፡ http://www.ewnetlehulu.org/am/razor/
ዶር_ባርት_ኢ_ኸርማን_ከዶር_ዳንኤል_ዋላስ.pdf
637.4 KB
በ ዶ/ር ባርት ኸርማንና በዶ/ር ዳንኤል ዋላስ መካከል የተደረገው ውይይት እነሆ

#አዲስ_ኪዳን_ተአማኒ_ነውን??

ለምን አልሰለምኩም አፖሎጄቲክስ

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified