የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
40 subscribers
89 photos
1 video
Download Telegram
Birhanu Dechassa:
"አልረሳውም" ፣ እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ" በሚል መሪ ቃል አጠቃላይ የጎፋ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ለ45 ሰኮንድ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት የሕልና ፀሎት አደረጉ።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አሸባሪው የሕወሓት ጁንታ ቡድን የፈፀመውን እኩይ ተግባር በማስታወስ መላው የዞናችን ሕዝቦች የአከባቢያቸውን ሠላም እንዲጠብቁና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲሰለፉ መልዕክት ተላልፏል ።

#ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም
ሣውላ
የጎፋ ዞን ነዋሪዎች አሸባሪዎቹን ሕወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሣውላ፣ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም የጎፋ ዞን ነዋሪዎች የሽብር ቡድኖቹን ሕወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በሣውላ ከተማ አካሂደዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ለሰልፉ ታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊት ታሪክ ያላትና የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌትና ኩራት መሆኑዋን ተናግረዋል።

ዶ/ር ጌትነት አክለውም እኛ ኢትዮጵያውያን የአባቶቻችን ፈለግ በመከተልና አንድነታችንን በማጠናከር የአሸባሪዎቹን የሕወሓትና ሸኔን ሀገር ሴራ በማክሸፍና የሚያጋጥሙንን ጊዜያዊ ፈተናዎችን በመቋቋም የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በማስከበር ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።

የሰልፉ ታዳሚዎች በበኩላቸው አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ ለማክሸፍ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የትም፣ መቼም እና በምንም ሁኔታ ለሀገራችን እንዘምታለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና 17 የዞኑ አመራሮች በበኩላቸው የመንግሥትን ጥሪ በመቀበል የሽብር ቡድኖቹን ሕወሓትና ሸኔን እስከ ግንባር በመሄድ ለመፋለምና ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ሰልፈኞቹ " በፕሮፓጋንዳው ጦርነት አንበገርም፣ ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን አይደናቀፍም፣ ክብር ለጀግናው መከላከያችንና ለመላው የፀጥታ ኃይላችን፣ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በሕዝባዊ ቁጭትና ጽናት ተሰልፈናል የሚሉና ሌሎችም የሽብር ቡድኖቹን ሕወሓትና ሸኔንና የውጭ ሚዲያዎች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያወግዙ እንዲሁም ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።

አከባቢያችሁን ጠብቁ!

ወደ ግንባር ዝመቱ!

መከላከያን ደግፉ!

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!

የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ


#ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም
#ሣውላ