ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንተ እንባዬ ምረጥ
ልግለጥህ?
ልዋጥህ?
ላፍንህ?
ልልቀቅህ?
ላፍስስህ
ላምቅህ?
ምን ላርግህ? ምከረኝ
ምንድነህ? ንገረኝ

እህል ትሆን ጠፊ?
ወይስ ሽል ነህ ገፊ?
በጊዜ ልወቅህ...
ላቅርብ ወይ ላርቅህ...
አጫጅ ነህ አራሚ?
ተጓዥ ነህ ከራሚ?
አላፊ ነህ ቋሚ?
ምንድነህ?
ምን ላርግህ?
ላግድህ?
ላውርድህ?
ጋርጄ ልካድምህ?
አውርጄ ልካድህ?
ቢያፍኑህ ቀሪ ነህ?
ቢለቁህ ኗሪ ነህ?

እንባዬ ምን ላድርግህ?
ላስርግህ?
ልጥረግህ?
እንዳ'ይን እንዳ'ፍንጫ
ቋሚ መገለጫ
መታወቂያ መልኬ ፡ ሆነህ ትኖራለህ?
ወይስ ላ'ንዴ ወርደህ፡ በዚያው ትቀራለህ?

አንተ እንባዬ ምረጥ
ላብስህ?
ላልብስህ?
ወይስ እንዳላየ፡
ከኔ የወጣ ሁሉ፡
የኔ አይደለም ብዬ
ልተውህ እንባዬ?

ወይስ ልገላገል?
እውነቱን ልናገር?
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ
እያልኩኝ ከማበል
አላውቅህም ልበል?

By #red-8

@getem
@getem
@paappii
47👍38🔥8