ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(ዐደይ .... )
=====================

ዋ.. ለወራት አካሌን ስለመሸከምሽ
      እንደ አክርማ ለሁለት ስለመከፈልሽ
ዋ.. አንድ ጊዜ በጎን አንድ ጊዜ በጀርባ                    
      ስለመሸከምሽ
      ከእይታሽ ስሰወር ስለመታመምሽ
ዋ.. እያደር እያነስሽ እኔን ለመስቀልሽ
      ለመኖሬ ዋጋ ደም ስለመክፈልሽ
                        ::
    ዳግም ተፈጥሬ ተሰንጥቄ ወልጄሽ
   ካልሆን በስተቀረ  ምንድነው ምከፍልሽ?
    ዐደይ እናንዋ  .. ተቀበይ መሻቴን
   ጥቂት ኢምንት እንኳ ካሳ ከሆነልሽ  !!

   by #kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍3916🎉4
(በሻማ..)
=============

ጀምበር እስክትወጣ
ስጠብቃት ፍቅሬን ውጥኔ እስኪሞላ
ሄደች አሉኝ ጥላህ የአልፎ ሂያጅ ጎረምሳ
ሻማ ተከትላ..
ምን አደርጋታለው
ይሙላላት ይሁናናናና !

ለዛሬ ዛሬማ ኩራዝ መቼ ጠፋ
ላምባ መች አነሰኝ
የፀና መሠረት ላቆም መሻቴ ነው
በፊቷ ያሳነሰኝ ...
ይሁን ትከተለው ጸሀይ ትውጣ ያለ
ተስፋዬ አሰልችቷት
ሞኝነቴን ታውጋው ያልታየ በረከት
መጠበቄ ደንቋት
ያየችው ብርሀን ማይቀልጥ የማይጠፋ
የማያልቅ መስሏት...
በዘመን መሳለቅ በጊዜ መዘበት
ሞኝነት ቢመስልም
ሰውን ተደግፎ እልፍ ከመራመድ
እግዜርን ሺ አመት ቆሞ መጠባበቅ
ሳይሻል አይቀርም !

#kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍3028
(ከወደቀ ወዲያ... )
=============+

ፍቅር የህጻን ገላ
ጠዋት አቁስለውት ቀትር ይፈ'ወሳል...
ፍቅር የህጻን አንጀት
ቀትር በድለውት ማታውን ይረሳል...
እምነት ግን አዋቂ
ትልቅ ሰው ነው መሰል
ወድቆ መች ይነሳል ??

#kiyorna

@getem
@getem
@paappii
53👍28🔥4🤩1
(በእርሳስ..)
==========

በስተመጨረሻ
ሲጻፍ የያዘውን
አልለቅም እያለ ት'ግል እንዳያፋፍም
ሰው ልቤ ሲገባ...
በእርሳስ ካልሆን በቀር
በቀለም አልጽፍም  !

#kiyorna
    (መነሻ ሀሳብ ...  red-8)

@getem
@getem
@getem
54👍33😁16👎7🔥3
(ካ..ል..ቆ..ሰ..ሉ)
============

አምላክ...
ፍቅርን አፍላ ችግኝ
የእለት ዘር ቢያደርገው
ውሀ አልሻ ብሎ
በአልቃሽ አፍቃሪዎች
እምባ ነው የሚያድገው  !

አምላክ...
ፍቅርን እንደመሬት
ለፍሬ ቢመርጠው
ይበልጥ ተቀዶ ለቆሰለ ሰው ነው
አብዝቶ ሚሰ'ጠው

አምላክ ....
ፍቅርን እንደ ጅረት
ዝቅ አርጎ ቢያፈሰው
ክብሬን ሳይል ቁልቁል ያዘነበለ ነው
ጠጥቶ ሚርሰው
:
ታዲያ
ከእኔነት ከፍታ ሳይንከባለሉ
ከመታበይ ዳገት ቁልቁል ሳይጣሉ
ተገፍተው ተረግጠው ዘምበል ሳይሉ
መች ቤቱን ሊሰራ
መች በዋዛ ሊገኝ
ፍቅር በቀላሉ
በሰው ካ..ል..ቆ..ሰ..ሉ  !

#kiyorna

@getem
@getem
@paappii
👍6635🔥3🎉3👎2
(ጥኢም ቁስል..)
===---====---===

በአማናዊ ልኬት ፍቅርን ከመዘንን
የኛማ መዋደድ ከአድማስ ወዲያ ማዶ
ዳርም የለው ካልን...
ልጠይቅሽ ውዴ
ስንት ህመም ተጋራን
ስንት ፍዳ ቻልን ?
ስንቴ አንገት ደፋን
ስንቴ አብረን ጠቆርን  ?
ስንቴ ተላቀስነው
ስንቴ ተጯጯህን  ?

አደራ አበባዬ....
ጣር አሳር ሲበዛው ከቶ እንዳሰለችው
በደስታዎች አጀብ ሚዛን እየሰፈርሽ
ፍቅርን አትገምችው
ያሰረን ቃልኪዳን
ያለምነው ብርቱ ሀይል
ከሳቆች ዳር ድንበር እጅጉን ይሰፋል
ፍቅር ጥኢም ቁስል
በጋራ ዕምባችን ልክ
እያደር ይገዝፋል  !

#kiyorna

@getem
@getem
@paappii
👍356🔥2
(የታመመ እንጠይቅ..)
==============

እውነትና ንጋት
እንዲህ ከልብ ሲርቅ
አምርሮ ጠያቂን
መ..ምህሩ ሲያ'ንቅ
የሰውነት አፍላግ
ከምንጩ ሲደ'ርቅ
ማን በጤናው ሊገኝ
ኑ ቢያመንም እንኳ...የታመመ እንጠይቅ  !

By #kiyorna

@getem
@getem
@paappii
38👍26🎉4🔥1
("አለማወቅ ")
=============

ተጠራርተው ሰማይ
አርያም የሄዱት ደጋግ ሊቃውንቱ
ታውቋቸው ይሆን ወይ
ሲመረምሩ አይተው
ማርጀቷን ምድሪቱ  ???
ክፉ ቀን መምጣቱ  ??
እንጃ
እኛ ብኩኖችን ያንከራትተናል
አለማወቅ ከንቱ  !

#kiyorna

@getem
@getem
@getem
43👍28🔥8😢6
(ውረጅ..)
============

አንቺ ጸሐይ ሆነሽ
ጸሐይ ትመኛለሽ
በጸደቀ ገላሽ ጻድቅ ባል ትሻለሽ
ከንጹሐን መንደር ንጹሕ ታስሻለሽ
እስቲ እንደው በሞቴ
በቃል ልሞግትሽ
እንዲ ነው ወይ ጌታ ወንጌል ያስተማረሽ ?
አንድ በግ ፍለጋ
ማያቅ ግራ ቀኙን
አልሰማሽ ወይ አምላክ ትቶ እንወረደ
ዘጠና ዘጠኙን !

ጻድቃንን ተያቸው
ጻድቃንን ተያቸው
በስራቸው ታምነው ሺ ጊዜ ይድናሉ
ያንቺ አይነት ነፍሳት ግን
ለኔ ቢጤው  ኃጥእ ግድ ያስፈልጋሉ
ውረጅ አበባዬ
ዛሬም ደጅሽ አለው ጠፍቶኝ ግራ ቀኙ  !

by #kiyorna

@getem
@getem
@getem
49👍25🔥4👎2
መንገድ አላፊ
=========

የዘመን ተረኛ
ቅጽበት ከእድል ገጥሞ ለዕለት ያጀገነው
የጊዜን ባለቤት
ፍቅር አስገድዶት ተቸንክሮ ቢያየው
አፉን አላቀቀ ሊራገም ሊሳደብ
ሊንቅ ሊያቃልለው
አይ አለመታደል
ምን ያለው ሞኝ ነው ..  ?

እንደ ቀሬናዊ በአላፊ እግሮቹ ለተገፋ ቆሞ
ነፍሱን እንዳያጸድቅ በግፍ አደባባይ
መስቀል ተሸክሞ ...
የገዳይ ፉከራ ከሟች የሲቃ ድምጽ
ለጆሮ ነግሶበት
ባላወቀው ሴራ ባልዋለበት ችሎት
ሆድ አመዝኖበት
እየተላገደ ጥርሱን በፈጠረ ጌታ ላይ ሳቀበት

ምናል እንደው ለአፍታ
ጥቂት መለስ ብሎ ደንዳናው አንገቱ
መምጫውን ቢቃኘው ዘልቆ ማንነቱ
ያንቋሸሸው መሲህ የናቀው መለኮት
ነበረ ትላንቱ ...
አሻግሮ ቢያማትር ትንሽ ከቁመቱ
የሰደበው ያ ቃል የተስፋው ጉልላት
ነበረ ውበቱ ...
ለልጅ ልጅ ሚወረስ የነገ ትርክቱ
ግና አፌዘበት
ድንገት ጠልቆ ቢያየው
ፀሀይ ደምግባቱ  ...  እግዚኦ አቤቱ !

ይደንቃል ለሰማ
የቅጽበታት ባርያ በዘመናት ንጉስ
እንደተሳለቀ
ይጨንቃል ለሰማ
በአላፊ ተረኞች ክብርን የፈጠረ
ጌታ እንደተናቀ
ክቡድ ነው ለአእምሮ
ሀጥእ ስለጻድቅ አንገት መነቅነቁ
በመላእክት ፈንታ
የሸንጋዮች ጉልበት በፊቱ መውደቁ
አሳላፊው ጌታ በአላፊ አንደበቶች
ስድብ መጨነቁ  !

ወዮለት ለዛ ሰው
ጥበብ ለጎደለው
ጽድቁ እንኳ ቀርቶበት
ምን ነበር ንጉሱን በቅጥ በኮነነው
ምናልባት ቢጠየቅ ተይዞ በድንገት
ቀራንዮ መሐል ...
ይህ መንገድ አላፊ አልሞ የሚሄደው
ኢየሩሳሌምን ሊሳለም ይሆናል  ...
አይደንቅህም ጎበዝ
የዚች አለም ጉዞ
ማደርያ ለመሳም ሰርክ መሽቀዳደም
በአዳሪው አፊዞ  !

by #kiyorna

@getem
@getem
@paappii
26👍22😱3
(ነበር ለካ  ...)
==============

በለመድነው ውብ ጎዳና
ፈሩን ሳይለቅ የእግርሽ የእግሬ ኮቴ ዳና
የለኮስነው ብርሃን ፋና...
ሩቅ ሳይደርስ ከመድመቁ ጨለመና
ያልጀመረ ታሪካችን አምና ሊባል ወይ አቻምና
ቀናት ቀሩ ወይ ሰው መሆን ወይ ፈተና....
:
የጊዜ ህግ ከቶ ይገርማል
ሚያልፍ ባይመስል ዛሬ ሲባል
ሺ ቢያወሩ እልፍ ቢማል
'ካሁን' ይልቅ 'ነበር' ለካ ቅርብ ኖሯል

By #kiyorna

@getem
@getem
@paappii
👍337🔥3
(ማርያም የሳመችኝ ....)
=================

መውጪያ መግቢያ ጠፍቶ
ሕይወት ሸክሟ ሲከብድ
የምታሳልፈኝ .. እሷ የማርያም መንገድ

ስራዬ ልክ አጥቶ ነፍሴን አቆሽሾ
ከእግዜሩ ሲያጣላት
የምታስታርቀኝ .. እሷ የማርያም ጣት

መራመድ ተስኖኝ ድካም ተጫጭኖኝ
ጉዞዬ ሲንኳሰስ
ፈጥና ምታደርሰኝ... እሷ የማርያም ፈረስ

ከገላዬ መሐል ጥቁር ነጥቧን ሳጣ
ተከፍቼ ሳለቅስ መስሎኝ የጠላችኝ...
ለካስ በሷ በኩል በትልቁ ኖሯል
ማርያም የሳመችኝ  !

#kiyorna

@getem
@getem
@paappii
135👍30🔥8🤩6👎1😢1
( ምክረ ደቂቅ ፩ ... )
=====+===+====

የሞላለት መርጣ..
በሆታ በፌሽታ
ዓለም ጀግኖች ስትኩል
ምንጊዜም ተሰለፍ
አንተ በዝምታ
በጎደለው በኩል .. !!

By #kiyorna

@getem
@getem
@paappii
👍259🔥2
( ኩራት ...)
==========

የዘመኑስ ህመም
መች ጉልበት ሀይል አለው
ዛሬ ሰውን ሁሉ ...
ኩራት ነው የገደለው !

By #kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍3314
( እከተላታለሁ )
==========

እከተላታለሁ
ዳገት የበዛበት ቢሆንም መንገዷ
ከልቤ አምናታለሁ
ምን እንደሸሸገች ባላውቅም በሆዷ
እጓዛለው አጽናፍ
ክንዷ እስካልደከመ ጉልበቷ እስካልዛለ
ይባስ ምን ሊመጣ
በለሷን አምኜ ጎርሼላት የለ !

by #Kiyorna

@getem
@getem
@getem
38👍18🔥7😁2
( ተስፋ እኮ ነው...)
============

የፍቅር ሰው የእምነት ባርያ
የእውነት ባዛኝ መልከ አንድያ
ደጉ ልቤ ...
በማጣት ምች ለጠቆረው
ምስኪን ገራም አንቺነትሽ
መጥቶ ነበር አምሐ ይዞ
ምን እንዲሻል ሊጠይቅሽ...

ግን አፈረ ...
ተጨነቀ ውስጡ አረረ
አንገት ደፋ አቀረቀረ
ከሩቅ ቢያየው ስንቱን ጎበዝ
ደጃፍሽ ላይ እንዳማተረ

አንዱ ሀብቱን አንዱ ከብቱን
አንዱ ወርቁን አንዱ ምርቱን
ከእግርሽ በታች ያለዋጋ ያለስስት ሲጥልልሽ ....
ሞኝ ልቤ ደነገጠ ከረጢቱን ደበቀልሽ

     ምን ያርግ ዓለም ?

በአሁን ሚዛን.. ላይ ሲሰፍሩት ልክ የሌለው
በዛሬ አይን ሺ ቢያፈጡ ማይታየው
የልቤ ስንቅ ከረጢቴን ሞልቶ የነበር
'ተስፋ' እኮ ነው ....

by #kiyorna

@getem
@getem
@paappii
32👍14
( የፍቅር ትግል...)
===============

አለ አይደለ አትወጅኝም
አለ አይደለ አልተውሽም
በገፋሺኝ በራቅሽኝ ልክ
ስንዝር ርቄ አልሸሽሽም

እጥራለሁ እስካልሞትኩኝ ተግቶ ለፍቶ
ያጣ የታለ ...
በፍቅር ትግል.. እንኳን አንቺ
ታላቁ እግዜር ወድቆ የለ !!

(ማስረጃ ዘፍ 32 : 28 )
by #Kiyorna

@getem
@getem
@getem
40👍23😁3🔥2😱1
( ስታነቢ'ው ...)
=============
ወይ ጉድ ....

መዳፌ ላይ ያለው
ዝብርቅርቅ ቅብ መስመር
አንቺ እስክታነብቢው
ትርጉም ያለው ስንኝ
አይመስለኝም ነበር ...
ቃሉ የተዛነፈ ሀሳቡ የጠፋ
በዝቶ ወጪ ገቢው
የህይወቴ ድርሳን ጣዕሙን ያገኘው
አንቺ ስታነ'ቢው ...

መንፈሴ ሲራቆት
ኑሮ ሲጸልምብኝ
የዘመኔ ካርታ እያደር ሲምታታ
ሲወሳሰብብኝ
ለካ ...
'ታንብብልህ' ብሎ
ኖሯል ፈጣሪዬ
አንቺን የላከልኝ

By #Kiyorna_Gracy

@getem
@getem
@getem
👍5725😁4🔥2
( መጽናኛ .. )
==============

ያ ሁሉ የስንኝ መአት
ያ ሁሉ የቃል ውርጅብኝ
ካየሁሽ ዕለት ጀምሮ
በነነ ድንገት ጠፋብኝ

እንኳን ሰም : ወርቅ ማራቀቅ
አንድ ቤት መምታት ቸገረኝ
ቃል ግጥም .. ስጋ አንቺን ነስቶ
ወረቀት አልይዝም አለኝ

ለካ ...
ሳይደግስ ማይነሳው ጌታ
በቃላት ሞልቶ ያኖረኝ
ፍቅሬ አንቺ እስክትመጪ ነው
መጽናኛን ' ግጥም ' የቸረኝ

ከመጣሽ ካለሽ ወዲያማ
ከብዕር ምን አታገለኝ !!!

ይመስገን 🙏
#Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
54👍33😁13😢2
( የበዛ ፍቅር )
===========

አንዳንዴ ...
ያዩት እንደው በጥልቅ ቆመው ከአፋፉ
ያልመጠኑት ፍቅር ሞት ነው ሁሌ ትርፉ

እምቢታ ያልገባት መጨከን ያልቻለች
ፍቅር ያበዛች እናት ልጇን ትገላለች !!!

#Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
59😢17👍16🔥9