ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ያለ አቅሜ አልንጠራራም!!!
_====_________

ከእለታት ባንድ ቀን አይጥና ዝሆን
አብረው እየተጓዙ፣
ወንዝ ለማቋረጥ ካንድ ትልቅ
ድልድይ አጠገብ ደረሱ፣
ከዚያም ወዲያውኑ...
አይጥ ከፊት ለፊት ዝሆን ሁዋላ
ሆነው፣
መሻገር ጀመሩ ይህን ግዙፍ ድልድይ መተማመኛ አርገው።
ትንሽ እንደሄዱ...
ያ ያመኑት ድልድይ ድንገት
ነቅነቅ ብሎ
ዝሆን ወዲያው ቆመ...
ፍርሀት ተሰምቶት ለአፍታ
ቀልቡን ጥሎ
አቅሟን ሳትገድብ...
አይጥ እንዲህ አለች አይታ
የታቹን ገደል፣
«አያ ዝሆንዬ እንዴት ሚገርም ነው
ነቀነቅነው አይደል!»

ዮሐንስ ገርማሜ

#john

@getem
@getem
@getem