ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አለሁ እኔ ደግሞ
።።።።።።።።።።።።
ከሰማየሰማይ፥
በፍቅር ተስቦ ፥ ሞቴን በሞቱ እየገደለ
የሞት ሸለቆዬን፥
በህይወት ፅኑ አለት ፥ እየደለደለ
አለኝ አንድ ንጉስ፥ሳልወደው ሚወደኝ
ዘወትር በፍቅር ድምጽ፥
ማልዶ ሚቀሰቅስ ፥ ደጁ የሚወስደኝ።
ደግሞ አለኝ አንድ ሰው፥
ሳይወደኝ ምወደው ፥ ሲሸሸኝ አጥብቆ
ልቤን መርጋት ከልካይ፥
በሱ፥በፍቅሩ እና ፥ በናፍቆቱ ሰብቆ።
አመታት አልፈዋል ፥
በሄደበት ሁሉ ፥ስሄድ ስከተለው
እግሬ በጉልበቱ፥
ነግቶ ማረፊያዬን ፥ በሩ ላይ ተከለው።
ይኼው እዚህ ደግሞ፥
ባለንፁሕ ልቡ፥ ፍቅሬን ብቻ ሽቶ
ከበሬ ማይጠፋ፥ቀን ጠብቶና መሽቶ።
"አንጀትን ባንጀት ነው"፥
የሚል ዘዬ አንግቦ ፥ ክራር ከጁ አያጣም
ክራሩን ሲገርፈው፥
ሆዴ የገባ ብርድ ፥ እስካመት አይወጣም።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ማረፊያ መርከቤ ፥ ቀድማ የሰጠመች
ባይዋሯ ነፍሴ፥
ከሀኪሟ ርቃ ፥
(በመነጠል ደዌ ፥ ላትድን የታመመች።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከሶስት አንዳቸውን፥ማመስገን ያልታደልኩ
ከአምላኬም መቅደስ፥
ባዶነት አናውጾኝ ፥ ወጥቼ የኮበለልኩ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
መሻቴን ሳሳድድ፥
ብርቱ ናፋቂዬን ፥ በርትቼ ምገፋ
በወዳቂው 'ምትስቅ፥
ተስፋ ቆራጭ ነፍሴ፥ ሞትን ተደግፋ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከእግዜሬ ጋራ ፥ ሙግት የምገጥም
የህይወትን ባህር፥
ላላይ እየሸሸሁ፥
የምኞት ባህር ውሰጥ፥ ገብቼ ምሰጥም።
በቃኝ ኧረ በቃኝ!
መሻቴን ቀብሬ ፥
ስጦታዬን ላንሳ ፥ ሻቼን ግባ ልበል
የገፋኝ ይገፋ፥
ስወድቅ ያነሳኝን ፥ በደስታ ልቀበል።
ግባ ሙሽራዬ፥
የኔ ጽኑ ወዳጅ ፥ ያነጸህ መገፋት
አድሳት ህይወቴን፥
ከሙታን ባህር ላይ፥ ለህይወት ጭለፋት።
እንሆ መቅደሴ፥
እጆቼ ይቀጡ፥ በሩን የዘጉብህ
ልቤ ይቅረብ ለፍርድ፥
ፍቅርን ስትዘምር ፥ ስላቅ የሳቀብህ።
እግዜሩም ታረቀኝ፥
ግብዝ ሰውነቴ ፥
ባርከህ በሰጠኸው ፥ ሳይልህ ተመስገን
ሲባክን መኖሩ፥
እርቃኑን ሊሸሽግ፥ ሽቶ ሌላ ተገን።
ያልከውን ሊቀበል፥
ፍቃድህን አምኖ ፥ ፍስሃን ሸምቷል
ተመስገን አምላኬ፥
አዲሱ እኔነቴ
በሙላት ተሰርቶ ፥ ባዶነቴ ሞቷል።


@getem
@getem
@paappii

#dagim hiwot
👍1
"በሰማይ ላይ ተሾምኩ"
_______________

ከዐይኑ ስር ልሰወር
ደማና ጋርጄ፣ ሰማይ ጉያ ገባሁ
የኔ ሰማይ እሱ፣
እንደሆነ ሲገባኝ፣
ኮኮቦች ለቅሜ፣ እልፍኜን ገነባው

@Getem
@Getem
@paappii

#Dagim_hiwot
👍1
ይሁና
_________________

ቀኔ ላይ ዳመና ጣለ፣
ምሽቴን ካፊያ አበላቸው።
ለሊቴን ዝናብ አድሮበት፣
ንጋቴን ጎርፍ አቆሸሸው።
ዳመና ልበሶ ላደረ፣
ቆፈናም ብርዳም ገላዬ።
ተስፋውን ጎርፍ ሲከላበት፣
ትዝታ ሆነ ጥላዬ።

@getem
@getem
@paappii

#Dagim hiwot
👍1
ከአመታት ልቃቂት ፣
ከወራቶች ድውር፣
ያስቋጠርነው ኩታ፣ ሸማኔው ቀንሶት፣
እዩት ተመልከቱት፣ ለፈታይ ገላ አንሶት።

@getem
@getem
@paappii

#dagim hiwot
ምላሽ
_________

ለቅያሜህ ሽረት፣ የይቅርታን ሸርቤ
ለፀብህ ማርካሻ፣ ፍቅርን ደርቤ
ለሓጥያትህ ስርየት፣ ሱባዬ ገብቼ
ክፍተትህ በጡብ፣ በመቻል ገንብቼ
እታረቅሀለው፣ ተመለስ ይበቃል
ይቅርት እንኳን፣ ከሰው ከእግዜር ያስታርቃል።

@getem
@getem
@paappii

#Dagim hiwot
"መኃልየ እሷ"
=========
መገን እሷ
ናፍቆቷ ሲዖል የሚያስንቅ
ፍቅሯ ገነት 'ሚያስናፍቅ።
ሳቋ የግዜር ትንፋሽ፥
ጅምር ሰውነት ላይ ፥ ነፍስን የሚሰካ
ሕይወት እራሷን ነው፣ በፍጡር ሲለካ።

@getem
@getem
@paappii

#Dagim hiwot
29👍9👎3😱1