///የማይቻል አንድ ነገር///
እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።
#ጌትነት_እንየው
@getem
@getem
@gebriel_19
እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።
#ጌትነት_እንየው
@getem
@getem
@gebriel_19
* ግራ የገባው መውደድ *
ነጭ የፈካ ጠዋት * ጥቁር ያዘነ ምሽት
ፈገግ ያለ ውሎ * ትክዝ ያለ ሌሊት
አንድ የጨዋታ ቀን * ሌላ የሰቀቀን
ያልሰከነ ሀሳብ * አንድ ያልሆነ ምኞት
የተቀያየረ * ጉራማይሌ ህይወት
ከተጋረጠባት
ስቃ ከምታለቅስ * ግራ ከገባት ነፍስ
ግራ ተዋድጄ * ግር አላት የኔ ነፍስ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ "ግር" አዲስ አይደለም
እንኳን አንቺ ቀርቶ ግር ብሏት ዓለም
ከዋከብት አጋጭታ
ፀሀይን ጨረቃን አቅጣጫ አስታ
አስክራው ታውቃለች ሁሉን ግራ አጋብታ
እንደ አንቺ ነገሩ ግር ያለባት ለታ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ ተስፋ እንዳትቆርጪ
ምን ግራ ቢገባሽ ቀኝሽን ብታጪ
ግራ ከወደድሻት
ግራ ከገባት ነፍስ ደስታ ለመቋደስ
መስሎ መራመድ ነው
ስትስቅም መሳቅ ስታለቅስ ማልቀስ
የግራ መንገዷ ቀኝ እስኪሆን ድረስ።
@getem
@getem
@paappii
#ጌትነት
ነጭ የፈካ ጠዋት * ጥቁር ያዘነ ምሽት
ፈገግ ያለ ውሎ * ትክዝ ያለ ሌሊት
አንድ የጨዋታ ቀን * ሌላ የሰቀቀን
ያልሰከነ ሀሳብ * አንድ ያልሆነ ምኞት
የተቀያየረ * ጉራማይሌ ህይወት
ከተጋረጠባት
ስቃ ከምታለቅስ * ግራ ከገባት ነፍስ
ግራ ተዋድጄ * ግር አላት የኔ ነፍስ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ "ግር" አዲስ አይደለም
እንኳን አንቺ ቀርቶ ግር ብሏት ዓለም
ከዋከብት አጋጭታ
ፀሀይን ጨረቃን አቅጣጫ አስታ
አስክራው ታውቃለች ሁሉን ግራ አጋብታ
እንደ አንቺ ነገሩ ግር ያለባት ለታ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ ተስፋ እንዳትቆርጪ
ምን ግራ ቢገባሽ ቀኝሽን ብታጪ
ግራ ከወደድሻት
ግራ ከገባት ነፍስ ደስታ ለመቋደስ
መስሎ መራመድ ነው
ስትስቅም መሳቅ ስታለቅስ ማልቀስ
የግራ መንገዷ ቀኝ እስኪሆን ድረስ።
@getem
@getem
@paappii
#ጌትነት
👍2
#ጌትነት እንየው
የተጀመረ አንጀት
በደል ያሰለለው :-
ጥቃት የበዛበት ፣
የተገዘገዘ ፣
የተጀመረ አንጀት ፣. . .
ባልጎለደፈ ቃል ፣
ባልገረጀፈ ጣት ፣
በስሱ ካልነኩት ፣
በፍቅር ካልዳሰሱት ፣
በስስት ካልያዙት
በእውቀት ካላገሙት ፣ . . .
በበደል ፣ በጥቃት ፣
ዳግም ከደፈቁት ፣
ደፍቀው ከጓጎጡት ፣
የተብሰከሰከ ፣ የተጀመረ አንጀት ፣
እንኳንስ ሊቀጥል ፣
ጥቂት ይበቃዋል ፣ ቆርጦ ለመለየት ።
#ጌትነት እንየው
@getem
@getem
@beckyalexander
የተጀመረ አንጀት
በደል ያሰለለው :-
ጥቃት የበዛበት ፣
የተገዘገዘ ፣
የተጀመረ አንጀት ፣. . .
ባልጎለደፈ ቃል ፣
ባልገረጀፈ ጣት ፣
በስሱ ካልነኩት ፣
በፍቅር ካልዳሰሱት ፣
በስስት ካልያዙት
በእውቀት ካላገሙት ፣ . . .
በበደል ፣ በጥቃት ፣
ዳግም ከደፈቁት ፣
ደፍቀው ከጓጎጡት ፣
የተብሰከሰከ ፣ የተጀመረ አንጀት ፣
እንኳንስ ሊቀጥል ፣
ጥቂት ይበቃዋል ፣ ቆርጦ ለመለየት ።
#ጌትነት እንየው
@getem
@getem
@beckyalexander