ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ምኞት
(!)
ሴት እናት ናት
ሴት ሀገር ናት . . . ፤
ሲሉ ሰምቼ : በአበዉ ቃል መደብር
ተፅፎ አይቼ : በሊቅ ፃፊ ብዕር
ልቤ ተመኘ : ሴትን የመሆን የሴትነትን ሚስጥር።

ከዚህ ምኞት ስር
ከዚህ ብዕር ስር
ከዚህ ግጥም ስር ፣
ሴት እህት : ሴት ሚስት ናት
ሴት እናት : ሴት ሀገር ናት
ቢባልም፣
ወንድ አባት ነዉ . . . ይህን አስተዉል ሀቁ አይካድም።

ቢካድም፣
የዚህ ብዕር አባት ፡ ራሱ ወንድ ነዉ : ክህደቱን አናምንም።

ብናምንም፣
የሴትን እህት ሚስትነት
የሴትን እናት ሀገርነት
በፍፁም አንክድም።

ብንክድም፣
የሴት ሀቅ ዘለን ፡ የከሃዲን ክህደት : በፍፁም አናምንም።

እናም ይህን ምታምን አምላክ . . . . .
ሴት ሆኜ እንድቆም ሀገር ሆኜ እንዳብብ ጮክ ብዬ እንድታይ ከሰማይ ግድግዳ
#ሰላም_ልምላሜ #ጀግንነት እንዳሳይ ማህፀኔም ቅን ወልዳ . . .

እባክህን ጌታ
ሴት አ'ርገኝና መቼም የማ'ረሳዉ ዋልልኝ ዉለታ።

@getem
@getem
@getem

#@Tekuzhan