#ይድረስ_ለናፍቆቴ
.
.
"እቴ....''
ከመንጋው ነጥሎ ለክህነት ሚያበቃኝ፣
ሞቼ ብገኝ እንኳን ከሞት የሚያነቃኝ።
የሳቅሽን ፀዳል ዜማው እያስታወስኩ፣
የደስ ደስ ገላሽን በልቤ እየሳልኩ።
እስክትመጪ ድረስ፤
እስካገኝሽ ድረስ፤
የባተለ ውሎ የሚያባዝት ምሽት፣
በትዝታ ፈረስ ትዝታዬን ሽሽት።
መኳተን መበተን መሳሳት አባባኝ፣
አልጋ ላይ አውሎ ብቻዬን አስነባኝ።"
ብዬ ባስነገርኩሽ ባስላኩሽ ማግስት፣
መተከዜ አሞሽ አሳጥቶሽ ትግስት።
በረሽ መጥተሽልኝ፤
በስስት አቅፈሽኝ ፤
ስመሽ አክመሽኝ ፤
ነቅለሽ ስታደርቂው የማጣትን አረም፣
"ኮነነ ፍስሀ" እነሆ መስከረም።
.
.
ብቻ.........
የማደርገው ሳጣ ብቸኝነት አስሮኝ፣
አንጀቴ ሲላወስ ብርዱ አስመርሮኝ።
ካለሽበት ቦታ እስካለሁበት ድረስ፣
በትሬንታ ኳትሮ በበቅሎ በፈረስ።
"ባክሽ ድረሽልኝ ነይ" ስልሽ ከመጣሽ፣
ዘመን ተለወጠ "እነሆ እንቁጣጣሽ"።
.
.
እቴ......
''አንቺን ልጥራሽ እንጂ እጣዬ እድሌ፣
ከሌላ አልገጥም ሽርክት ነው አመሌ።
ጠረንሽ ከራቀኝ ያነጫንጨኛል፣
አብረሽኝ እያለሽ መኖርሽ ያምረኛል።
.
.
በቃ ልይሽ አሁን ልታገስ ህመሜን፣
ከእቅፍሽ ልዝለቅ ተካፈዪኝ ህልሜን።''
ብዬ እንደተናገርኩ ካፌ እንደወጣ፣
ፍቅሬ መጥተሽልኝ ናፍቆት ከተቀጣ።
ማጣት ጓዙን ጭኖ ፍቅርሽን ከተካ፣
የቆዘመው ቤቴ በሳቅሽ ከፈካ፣
አውራ ዶሮ ጮኸ "እነሆ ፋሲካ"።
.
.
መቼም ሰው አይደለን፤
ተፈጥሮ በህጉ መልካም ሳያድለን፤
ምናልባት ባይፃፍ ማከምሽ መዳኔ፣
ቢፈተን እምነትሽ ቢፈተን ኪዳኔ።
መክሳትሽ መክሳቴ፤
ማጣት መገርጣቴ።
አይድረስ ከጆሮው ጠላት አይገምተው፣
እስካገኝሽ ድረስ፤
ሁሉንም ሁሉንም ለ'ግዜሩ ነው መተው።
.
.
.
እናም የኔ ናፍቆት......
መስከረም ሲጠባ ሰማዩ ሲፈካ፣
በበዓል 'ባውዳመት በገና ፋሲካ።
እምነቴን ሳላጎድፍ ቃሌም ሳይጓደል፣
በ "ትመጫለሽ" ስም ልጠብቅሽ አይደል ????።
✍ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
.
.
"እቴ....''
ከመንጋው ነጥሎ ለክህነት ሚያበቃኝ፣
ሞቼ ብገኝ እንኳን ከሞት የሚያነቃኝ።
የሳቅሽን ፀዳል ዜማው እያስታወስኩ፣
የደስ ደስ ገላሽን በልቤ እየሳልኩ።
እስክትመጪ ድረስ፤
እስካገኝሽ ድረስ፤
የባተለ ውሎ የሚያባዝት ምሽት፣
በትዝታ ፈረስ ትዝታዬን ሽሽት።
መኳተን መበተን መሳሳት አባባኝ፣
አልጋ ላይ አውሎ ብቻዬን አስነባኝ።"
ብዬ ባስነገርኩሽ ባስላኩሽ ማግስት፣
መተከዜ አሞሽ አሳጥቶሽ ትግስት።
በረሽ መጥተሽልኝ፤
በስስት አቅፈሽኝ ፤
ስመሽ አክመሽኝ ፤
ነቅለሽ ስታደርቂው የማጣትን አረም፣
"ኮነነ ፍስሀ" እነሆ መስከረም።
.
.
ብቻ.........
የማደርገው ሳጣ ብቸኝነት አስሮኝ፣
አንጀቴ ሲላወስ ብርዱ አስመርሮኝ።
ካለሽበት ቦታ እስካለሁበት ድረስ፣
በትሬንታ ኳትሮ በበቅሎ በፈረስ።
"ባክሽ ድረሽልኝ ነይ" ስልሽ ከመጣሽ፣
ዘመን ተለወጠ "እነሆ እንቁጣጣሽ"።
.
.
እቴ......
''አንቺን ልጥራሽ እንጂ እጣዬ እድሌ፣
ከሌላ አልገጥም ሽርክት ነው አመሌ።
ጠረንሽ ከራቀኝ ያነጫንጨኛል፣
አብረሽኝ እያለሽ መኖርሽ ያምረኛል።
.
.
በቃ ልይሽ አሁን ልታገስ ህመሜን፣
ከእቅፍሽ ልዝለቅ ተካፈዪኝ ህልሜን።''
ብዬ እንደተናገርኩ ካፌ እንደወጣ፣
ፍቅሬ መጥተሽልኝ ናፍቆት ከተቀጣ።
ማጣት ጓዙን ጭኖ ፍቅርሽን ከተካ፣
የቆዘመው ቤቴ በሳቅሽ ከፈካ፣
አውራ ዶሮ ጮኸ "እነሆ ፋሲካ"።
.
.
መቼም ሰው አይደለን፤
ተፈጥሮ በህጉ መልካም ሳያድለን፤
ምናልባት ባይፃፍ ማከምሽ መዳኔ፣
ቢፈተን እምነትሽ ቢፈተን ኪዳኔ።
መክሳትሽ መክሳቴ፤
ማጣት መገርጣቴ።
አይድረስ ከጆሮው ጠላት አይገምተው፣
እስካገኝሽ ድረስ፤
ሁሉንም ሁሉንም ለ'ግዜሩ ነው መተው።
.
.
.
እናም የኔ ናፍቆት......
መስከረም ሲጠባ ሰማዩ ሲፈካ፣
በበዓል 'ባውዳመት በገና ፋሲካ።
እምነቴን ሳላጎድፍ ቃሌም ሳይጓደል፣
በ "ትመጫለሽ" ስም ልጠብቅሽ አይደል ????።
✍ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
❤35👍30🔥9😱2