ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ይድረስ_ለተከፋች_ሴት
.
.
ይኸውልሽ የኔ አይናማ፤
አንዴ ብቻ እኔን ስሚኝ አታለቃቅሺ እርሺው እንባሽን፤
ሰው ከመሆንሽ ሳትሸራርፊ እጥፍ ውደጂው ያስለቀሰሽን።
ልብሽን በእምነት አፅኚው የዛሬ ቀንሽም ያልፋል፣
ችግርሽ ምን ቢደራረብ በእግዜር እጆች ይገፋል።
የምታምኚው አምላክሽ እኮ፤
ከሞት መንጋጋም ነፍስ ያስተርፋል።
"ተሳሳትኩ " ??

አልተሳሳትኩም !!!!!
የተስፋ መሃረብ ይዘሽ ትኩስ እንባሽን በይ አደራርቂው፣
መደነቃቀፍ ብርታት ከሆነ ገፊሽን ሁሉ ወደሽ መርቂው።
ወርቅን እራሱ፤
"ወርቅ ሆነ" እንዲባል የተጋጋመ እሳት በልቶታል፣
ታድያ አምላክሽ ይመካብሽ ዘንድ ሺ ቢፈትንሽ ክፋቱ የታል ????
"እኔ አልታየኝም"።
.
.
እናምልሽ ውድ ዓለሜ መፈተንሽን እንዳትጠዪው፣
ይልቅናሽስ ፈገግ ብለሽ "ፈጣሪዬ ሆይ ተመስገን" በይው።


ዓቢይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
👍5442🔥2😱2🎉2