ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
"ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ፣ ሲበቃው ያባራል
መጠለያ ሞልቶ...
እየበሰበሱ ፣ መኖር ግን ይመራል"
ያልሽኝን እያሰብኩ ፣ ዶፍ ዝናብ ቢጥልም
እየበሰበስኩኝ...
ወዳንቺ 'መጣለሁ ፣ ከቶ አልጠለልም፡፡
ከዝናብ ነው እንጂ ...
ጥላው ካንቺ ናፍቆት ፣ እኔን አያስጥልም።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

(በላይ በቀለ ወያ )
#የግጥም_አብዮት fb

@getem
@getem
👍1
እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል
አብዮተኛ ይደግሳል😊
ነሐሴ ➋➌
#የግጥም_አብዮት 🙏

ቦታ ☞ አ.አ ደምበል ህንፃ ጀርባ ወረዳ 9 የወጣቶች ማዕከል አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡

⭕️ 400 ሰው ብቻ!

📍100 ብር 👌
#ይነበብ
ውድ የቴሌግራምና ፌስቡክ ጓዶች እንዴት ናችሁ?

መቼም በዚህ ሰዓት 'ሰላም ነው?' የሚለውን ቃል ከአንደበታችን እንዳናወጣ በሀገራችን እየሆነ ያለው ነገር ያስረናል፡፡

አዎ፡፡ እኛ ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን ጎን ነን !!! ኢትዮጵያ ምንጊዜም ድል ታደርጋለች፡፡ አዎ እኛ ከንግግር በዘለለ አንድ ነገር በጋራ ብናደርግስ ፡ ብለን ወሳኝ ጉዳይ ለማከናወን ተነስተናል፡፡

ይህ ጥሪ ለሁላችሁም ነው ህዳር 20 እሁድ እለት #የግጥም_አብዮት እና የ #ግጥም_ብቻ ከተሰኙት ግሩፕ ጋር ለመልካም ነገር ዘምታችሁ #ደሜን_ለሀገሬ እያላችሁ ትለግሱ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እኔ ከኢትዮጵያ ጎን ነኝ የሚል ሁሉ ደሙን ሰጥቶ አለሁልሽ ይበላት፡፡ መልካምነት ዋጋው ትልቅ ነው ወደ ህይወታችን ይዞ የሚመጣው በረከትም አያልቅም፡፡ ኑ ለመልካም እንዝመት! ሩቅ ያላችሁ በየትኛውም ክፍለ ሀገራት የሚገኙ #ለመልካም_ዘማቾች ቀኑን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቀይ መስቀል በመሄድ እለቱን ያስቡ፡፡

በዚህም መሰረት ፦

ህዳር 20 (እሁድ )
ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
ስቴዲየም ወደሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ግቢ ውስጥ እንገናኝ 🙏🙏🙏

*
Telegram
@Tkida and @gebriel19

#ለመልካም_ዘማቾች
#የግጥም_አብዮት
#ግጥም_ብቻ

📍📍📍 በዚህ ዘመቻ ላይ አብረን እንዘምታለን የምትሉ ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ ፡፡ #Share

📍📍📍 ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ሁሉ ቢያንስ ለ10 ሰው ይህንን በማካፈል ዘመቻውን እንቀላቀል/እንደግፍ 🙏

@getem
@TkYEGITMABIYOT
😢1