ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የናቴ~ልጅ~እኔ

ከፊትሽ ገፅ ላይ
ቁጭት አነባለሁ
ማየትን የጠላ ማንነት እረክሶ
ጥርስሽ ይናገራል
የልብሽን ሚስጥር ከንፈርሽን ነክሶ

ጠይም ወዘናሽም
ሀበሻዊነቱን ማርጀትሽ ሳይነጥቀው
የግንባርሽ ሽብሽብ
ያ'ይኖችሽን ብሌን እይታ ሳይሰርቀው

ባገር ተመስሎ
እልፍ አንቺነትሽን በግልፅ እያወጋኝ
የዛሬው እኛነት
ካንቺ ሲነፃፀር ብርታቴ አሰጋኝ፡፡

ግና ተስፋ አልቆርጥም
የደምሽ ውጤት ነኝ ካንቺው የተቀዳው
ለዚህ ነው እምዬ
ሺ ዘመን ቢቀየር
በ'ናትና ባ'ገር የማላወላዳው፡፡

ልብ አልባው ገጣሚ

@getem
@getem
@getem