ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የታጠረ_እሳት
-
እኛን ለማማሰል ፥ የሚላኩ ጣቶች
ፈጥነው ይረግፋሉ ፥ እንደ ጤዛ መልኮች!
ደርሶ ጥልቅ አይልም ፥ አይደፍረንም ጭልፋ
እንኳን ብረት ቀርቶ ...
ፀሃይ ትሟሟለች ፥ በሆዳችን አልፋ!
-
ብለን በፎከርን ፥ በሸለልን ማግስት
ምን ጉድ ነው የጣሉን ፥ የከተቱነ ድስት?!
-
አጓጉል አርገውን
ረግተን ላንቀመጥ ፥ ፈንድተን ላንወጣ
ዝምብሎ መብሰክሰክ
ዝምብሎ መንተክተክ ፥ ሆኗል የኛ እጣ!!!
--------------//-------------
(በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem