ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የታል?



ፈጣሪ ጥበቡን ሊያሳይ ውብ አርጎ ስለፈጠራት፤
መሬት አይንካኝ እያለች ይመሻል ቀኑ እያጠራት።
ኩራት ልቧን ወድሯት ምድር አንሷት ይመስል፤
አግዝፋው የራሷን ምስል፤
በመልኳ ስትጓደደው ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች፤
ካንጀቴ ታስቀኛለች።


የፈጣሪ እደ ጥበብ የውበት ዳር የታየበት፤
ፍፁም ገላ ፍፁም ውበት፤
እግዜር ሰጥቷት ተላብሳለች፤
በራሷ አይል እሷ ለሷ አንዳች ቅጥል ምን አርጋለች?


ዓይኗን ሰራች?
ጥርሷን ሰራች?
ወይ ከንፈሯን?
ደም ግባቷን?
ወይስ መላ ሰውነቷን?
የፈጠራት በጥበቡ ቸሯት እንጂ ውብ ቁንጅና፤
ለማማሯ ለውበቷ ተጫውታለች አንዳች ሚና?


ካካላቷ ለሚታየው ለሰፈረው ውብ ታንጽኦ፤
የቱኛው ነው የሷ ድርሻ ያኖረችው አስተዋጽኦ?
ምንም የለም ካለም የታል?
ባልፈጠረው ሰው ሲጎበር ጭንቅላቱን ያስገምታል።
ንገሯት!

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
👍4513🤩5
#የታል?



ፈጣሪ ጥበቡን ሊያሳይ ውብ አርጎ ስለፈጠራት፤
መሬት አይንካኝ እያለች ይመሻል ቀኑ እያጠራት።
ኩራት ልቧን ወድሯት ምድር አንሷት ይመስል፤
አግዝፋው የራሷን ምስል፤
በመልኳ ስትጓደደው ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች፤
ካንጀቴ ታስቀኛለች።


የፈጣሪ እደ ጥበብ የውበት ዳር የታየበት፤
ፍፁም ገላ ፍፁም ውበት፤
እግዜር ሰጥቷት ተላብሳለች፤
በራሷ አይል እሷ ለሷ አንዳች ቅጥል ምን አርጋለች?


ዓይኗን ሰራች?
ጥርሷን ሰራች?
ወይ ከንፈሯን?
ደም ግባቷን?
ወይስ መላ ሰውነቷን?
የፈጠራት በጥበቡ ቸሯት እንጂ ውብ ቁንጅና፤
ለማማሯ ለውበቷ ተጫውታለች አንዳች ሚና?


ካካላቷ ለሚታየው ለሰፈረው ውብ ታንጽኦ፤
የቱኛው ነው የሷ ድርሻ ያኖረችው አስተዋጽኦ?
ምንም የለም ካለም የታል?
ባልፈጠረው ሰው ሲጎበር ጭንቅላቱን ያስገምታል።
ንገሯት!

#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
👍3222🤩8🔥4😢2