ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ለቅዳሚታችን
❤️

#የሆነ ቀን ነው ማታ ላይ............

ሀንግ ተደርጊያለው ብዬ ለማመልከት አቅራቢያዬ ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩ ፣ቢሮውን
አንኳኳው ከውስጥ የሰለለ ድምፅ ይግቡ አለኝ።ገና ሳልቀመጥ ምን ልርዳህ አለኝ
ማዕረጉን እያስተካከለ፣ማታ ወደ ቤቴ ስገባ ዝርፊያ ተደርጎብኝ እሱን ለማመልከት
ነው።ስንት ሰአት ይሆናል? አለኝ በግምት ለአራት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ይመስለኛል አልኩት
ጨለማ ነበር አለኝ አይ ፀሀይ ወጥታ ነበር ማለት አማረኝ...ዝም ስለው መብራት ነበር
ወይ፣ሰዎቹን መለየት የምትችልበት ሁኔታ ነበር ወይ ለማለት ነው አለኝ።አይ መለየት
በሚያስችል ሁኔታ ብርሀን የለም ግን አንደኛው በጣም ስለተጠጋኝ በደምብ
አይቼዋለው...ምን ይዘህ ነበር ? የተወሰነ ገንዘብ ፣ስልክ እና ሀሳቦቼን። ሀሳቦቼን ማለት?
አለኝ ቀና ብሎ መስራት እና ማድረግ የምፈልጋቸውን ነገሮች አይምሮዬ ውስጥ ተሸክሜ
ነበር አደጋ አደረሱብኝ ወይ ሞትኩ ማለት እነሱም ጠፉ ማለት አይደል አልኩት እኔ ደሞ
ወንበሩ ላይ ለጠጥ ብዬ....ተኮሳተረ ሀሳብ ለፖሊስ ንብረት አይደለም ማለት ነው? ብዬ
ለራሴ አሰብኩ እያሾፍክ አይደለም አይደል አለኝ...ለምን አሾፋለው አልኩት ፈርጠም ብዬ
እሺ የብሩ መጠን ስንት ነበር አለኝ እኔንጃ በግምት ከአንድሺ አምስት መቶብር በታች
ከአንድሺ በላይ አልኩት፣ስልኩስ አለኝ ቴክኖ ነው ውስጡ ከመቶ ብር በላይ ካርድ እና
የተወሰነ የኢንተርኔት ፓኬጅ አለው አልኩት.....የምጠይቅህን ብቻ መልስ አለኝ
ቢቆጣም ባይቆጣም ድምፁ ተመሳሳይ የሰለለ ነው...እሺ ልጁ ምን አይነት ነው ?ይሄ
ሰውዬ ሁሉንም ጠይቆ ይዞት ሊካፈል ነው እንዴ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ መልኩን አሳስቼ
ልንገረው? አይ በትክክል ልንገረው እና ይጠቀም አልኩ...ምነው ዝም አልክ መልኩ
ጠፋብህ አለኝ።አልጠፋብኝም ጠይም ፣መካከለኛ ቁመት፣ሰፊ ፊት ያለው፣የተንጨባረረ
ፂም እና ፀጉር ያለው እና ቀኝ እጁ ላይ ትልቅ ቀለበት አድርጓል አልኩት...በዚ ሰአት አንገቱን
እየነቀነቀ ነበር እኔ ግን ከእንቅልፌ ላብ በላብ ሆኜ ነቅቻለው።
.
.
.
.



ግጠም ያሉኝ ጊዜ!!!

እስቲ ቅኔ ልዝረፍ፤
ቅኔ ዛር አለብኝ፤ ደርሶ የሚነሳ፤
ና ግጠም የሚለኝ፤
ና ብረር የሚለኝ፤
ብድግ የሚልብኝ፤ ደርሶ እንደግሪሳ።
እኔም አያስችለኝ፤
መቼም አይሆንልኝ፤ የቅኔ ወግ ነገር፤
እየተዘረፉ፤
እየተዛረፉ፤
ደግሞ እየዘረፉ፤ በሚበሉት ሃገር፤
ጭቁን ምን ይዘርፋል፤
ከዘለላ ግጥም፤ ካንዲት ቅኔ በቀር።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ !!!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
#የሆነ ሰው አለ!

የሆነ ሰው አለ...
ላም አለኝ በሰማይ...
ስዬ የጨረስኩት በህልሜ ቅዠት ላይ
በገፁ ምእራፍ ደስታዬን ያተመ
ጽልመት ሲያጠላብኝ ትቶኝ ያልተመመ
ሰርክ የገበርኩለት አእላፍ ቀለማት
ነፋስ ላይ ያረፉ የተስፋ ፊደላት...
የሆነ ሰው አለ...
ይሄውና ቁሞ
በጉም ተሸፍኖ ደመና አገልድሞ።

በረድኤት መጽአ

@getem
@getem
@getem