ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
​••◉❖ #አዎ_መምህር_ነኝ!….👨‍🏫❖◉●••
የትውልዱን ነገ ያዘልሁኝ በጀርባ
መጪውን እያሰብሁ በህልም የምባባ
አዎ መምህር ነኝ የእውቀት ደብተራ
ከፈጣሪ በታች ሰውን የምሰራ
የጠመኔ ብናኝ በላጠው መዳፌ
በመለፍልፍ ብዛት በደረቀው አፌ
ሰው ሃብታም የማደርግ ድህነት ታቅፌ
#አዎ_መምህር_ነኝ
የእውቀት ደብተር እንጂ የባንክ ቡክ የሌለኝ
እንደ ደረሰች ሴት እውቀትን እያማጥኩ
ጠመኔ ታቅፌ ከትውልድ ፊት የቆምኩ
ነገን እንዲሸከም ጮሄ የምሞግት
ደሞዝ ቀን የራቀኝ እንደ ዳግም ምፃት
#አዎ_መምህር_ነኝ!
የመቶ ብር ምስል የሚያስደነግጠኝ
የቱጃር ቀበጦች የዋሌት ግልምጫ
ገንዘብ የሚያጋብስ የ ነጋዴ ሩጫ
ያላስበረገገኝ
ያላስደነበረኝ
ቁርሴን ተራምጄ ተማሪ ፊት ምገኝ
#አዎ_መምህር_ነኝ!
እስትንፋስ ምዘራ ትንፋሽ እያጠረኝ
የለበስኩት ጃኬት ቢያልቅም ከጫንቃዬ
ሁለተኛ እግሬ ብታልቅም ጫማዬ
ምንም ቢቸግረኝ ከፊትህ ማልጠፋ
የእውቀት አባትህ ነኝ ለነገህ ምለፋ
በል እንግዲህ ልጄ አስተውለህ ስማ
እኔ መምህር ነኝ በችግር ማልደማ
“ካለው ወስዶ መስጠት
በእጅ ይዞ ንፍገት”
እንደዚህ ቢሆንም የአለሙ አባዜ
ትርፌ አንተ ነህ ልጄ አይደለም ደሞዜ
••◉❖◉●••
#ክብር_ለመምህራን

@getem
@getem
@getem
👍1