#እንደ_ግሌ_መቅደስ
:
:
እኔ ላንቺ ፍቅር እኔ ላንቺ መውደድ
ምንም አይመስለኝም እስክከስል ብነድ።
:
:
እውነት እውነት ውዴ
አትጠራጠሪ፣ሂጂ ተናገሪ
ላልሰሙት አብስሪ፣ለሰሙት ጨምሪ
እሱ እኮ ለኔ ሲል የማይሆነው የለም ብለሽም ዘክሪ።
:
:
አዎ ውዴ
ለፍቅራችንም ስል የማልሆነው የለም
ውሸቴን ከሆነ ጀርባ ትስጠኝ አለም።
:
:
ደግሞም የኔ ፍቅር ...
እንኳን ሰዉን ቀርቶ እኔኑ መልሶ
ትንግርት የጫረብኝ የገረመኝ ደርሶ
ካለሽበት ቦታ ዘውትር ምመላለስ
ቆጥሬሽ እኮ ነው እንደግሌ መቅደስ።
:
:
አዎ ውዴ ...
አንቺው ነሽ እምነቴ አንቺው ነሽ መቅደሴ
አንቺው ነሽ አዳኜ አንቺው ነሽ ፈውሴ።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ...
ሰሊሆም አልሄድም ብርሀንን ፍለጋ
ጭቃም እንዳትቀቢኝ እሱም የለው ዋጋ
የሚበጀኝማ ዐይኔን እየሳምሺኝ አኑሪኝ ካንቺው ጋ።
እንደ ጥላ ሆኖም እንዳላይ ያገደኝ
ስትስሚኝ ይገፋል ዐይኔን የጋረደኝ።
:
:
ይህቺንም አድምጪኝ ...
ዮርዳኖስ ለምኔ ዮሀንስም ይቅርብኝ
ከቻልሽ አንቺው ጠርተሽ ንስሀ አስተምረሺኝ
ሁሉን ምወጣበት መሰላል ሰተሺኝ
በጣቶሽ ዳብሰሽ በፍቅርሽ ጥመቂኝ።
:
:
የሚገርመው እኮ ...
አንቺን እየቆጠርኩ እንደ ግሌ መቅደስ
ስምሽን ስዘክር ንግሱን ላንቺው ሳነግስ
ቀኑን ባንቺ ወክዬ ምስልሽን ስስመው
ገነት ያለው ያህል ለኔ እጅግ ደስታ ነው።
:
:
ታዲያ ይህ ደስታዬ ሰላም ስለሰጠኝ አንቺን በመውደዴ
በፆምና ፀሎት እየተመላለስኩ ልክ እንደ ሁዳዴ
አግባኝ ያልሺኝ ዕለት ስለት ገብቻለው ለመሄድ በዳዴ።
:
:
ስለዚህ መቅደሴ ...
አንቺም እሺ በዪኝ እንዲ ስደክም
ዘላለም ኑሮዬ የሰማዩ አለም
መቅደስ ውዬ ውዬ እንዳይሆን ገሀነም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
:
:
እኔ ላንቺ ፍቅር እኔ ላንቺ መውደድ
ምንም አይመስለኝም እስክከስል ብነድ።
:
:
እውነት እውነት ውዴ
አትጠራጠሪ፣ሂጂ ተናገሪ
ላልሰሙት አብስሪ፣ለሰሙት ጨምሪ
እሱ እኮ ለኔ ሲል የማይሆነው የለም ብለሽም ዘክሪ።
:
:
አዎ ውዴ
ለፍቅራችንም ስል የማልሆነው የለም
ውሸቴን ከሆነ ጀርባ ትስጠኝ አለም።
:
:
ደግሞም የኔ ፍቅር ...
እንኳን ሰዉን ቀርቶ እኔኑ መልሶ
ትንግርት የጫረብኝ የገረመኝ ደርሶ
ካለሽበት ቦታ ዘውትር ምመላለስ
ቆጥሬሽ እኮ ነው እንደግሌ መቅደስ።
:
:
አዎ ውዴ ...
አንቺው ነሽ እምነቴ አንቺው ነሽ መቅደሴ
አንቺው ነሽ አዳኜ አንቺው ነሽ ፈውሴ።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ...
ሰሊሆም አልሄድም ብርሀንን ፍለጋ
ጭቃም እንዳትቀቢኝ እሱም የለው ዋጋ
የሚበጀኝማ ዐይኔን እየሳምሺኝ አኑሪኝ ካንቺው ጋ።
እንደ ጥላ ሆኖም እንዳላይ ያገደኝ
ስትስሚኝ ይገፋል ዐይኔን የጋረደኝ።
:
:
ይህቺንም አድምጪኝ ...
ዮርዳኖስ ለምኔ ዮሀንስም ይቅርብኝ
ከቻልሽ አንቺው ጠርተሽ ንስሀ አስተምረሺኝ
ሁሉን ምወጣበት መሰላል ሰተሺኝ
በጣቶሽ ዳብሰሽ በፍቅርሽ ጥመቂኝ።
:
:
የሚገርመው እኮ ...
አንቺን እየቆጠርኩ እንደ ግሌ መቅደስ
ስምሽን ስዘክር ንግሱን ላንቺው ሳነግስ
ቀኑን ባንቺ ወክዬ ምስልሽን ስስመው
ገነት ያለው ያህል ለኔ እጅግ ደስታ ነው።
:
:
ታዲያ ይህ ደስታዬ ሰላም ስለሰጠኝ አንቺን በመውደዴ
በፆምና ፀሎት እየተመላለስኩ ልክ እንደ ሁዳዴ
አግባኝ ያልሺኝ ዕለት ስለት ገብቻለው ለመሄድ በዳዴ።
:
:
ስለዚህ መቅደሴ ...
አንቺም እሺ በዪኝ እንዲ ስደክም
ዘላለም ኑሮዬ የሰማዩ አለም
መቅደስ ውዬ ውዬ እንዳይሆን ገሀነም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
👍1