ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እኔ_ወይስ_ፍቅር

(ከአይነ-ስውሩ ፍቅር ጋር የተደረገ ምልልስ)

ሰላም በሰፈነ በዛች ለምለም ቦታ
ድምፁ ሚያስተጋባ የወፎች ጫጫታ
በለሙ ምድር ላይ አበቦች ተተክለው
መአዛው ግሩም ነው...

አንድ ሽታ ነበር ሰርፆ ከኔ የዋለ
ልቤም ጠረጠረ አይኔም ሸነገለ።

የሸተተኝ ነገር ምንጩን ልፈልገው
ፍቅርን ላገኘው ላየው ስለጓጓው
ሲሄድ ስከተለው ዞሮ እንኳን ሳያየኝ ከታጠረው ቦታ መርቶ አደረሰኝ

ስገምት ከፍቶታል......
በተፈጥሮ ጠረን እየተገረመ
ብሬሉን አንስቶ ግጥሙን ገጠመ

"አይኔ ጠፋ ብዬ አላማርርህም
መሪዬም ከጎኔ የለም አልልህም
ግና ግን አምላኬ...
#ንፁህ ልብ ላለው ፍቅር ለሚገባው
እኔን ለሱ ሰጥተህ ህይወቱን ላስውበው"

በፍቅር ግጥሞች እንዲህ ተገርሜ
አብሬው ገጠምኩኝ በብዕሬ ታክሜ

ጉሮሮዬን ጠራርጌ....

"እኔ ነኝ ፍቅር ሆይ ስከተልህ ነበር
ምን እንደምታደርግ ለማወቅ ስታትር
አንተን አገኘውህ ተቀምጠህ ካጥር"

"ስትገጥም ሰማሁኝ ለአምላክህ ስትለምን
ንፁህ ልብ ላለው ስጠኝ ያልከው ለምን?"

#የጎደፈ ልቡ ባንተ እንዲጠራ
ለሱ ነበር መሆን የሰጠህ አደራ

ግና ግን አንተ ራስ ወዳድ ነህና
ንፁህ ልብ ላለው ጠየክ በልመና"

እንዲ ስለው ድንገት እንደ ደነገጠ
ካለ'ውበት ጥሎኝ ሮጦ ፈረጠጠ

ማነው ቆይ ትክክል? ፍቅር ወይስ እኔ
በፅድቅ መንገድ ላይ የገባው ኩነኔ

OB'☀️(ja)
👇👇For your comments @jadmasse25
@getem
@getem
@getem
👍3718😢2😱1🎉1