ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እኔ_እና_መስከረም🌼

አዎ አስታውሳለሁ
አመቱን በሙሉ ሳፈቅርሽ ስለኖርኩ
ጳጉሜንም ጨምሮ ሩፋኤል ተጠመቅኩ።

ሰው እንዴት ይሆናል አፍቅሮ ሀጢያተኛ
ክፉ ሳልናገር አብሬሽ ሳልተኛ።

ከመስከረም እስከ ጳጉሜ
ባንቺው ናፍቆት ላንቺው ቆሜ።

የማፍቀሬን ምላሽ በዋዜማው እለት መልስሽን ለመስማት
ፀሎት በያዝኩበት በዛ ረጅም ሌሊት

እሺ ትለኛለች...? ለአዲስ አመትማ አብረን እንዘልቃለን በሚል ደቂቅ ተስፋ
አምሮብኝ እንድታይ ኩታዬን ሳሰፋ

ምታዪኝ ይመስል ፀጉሬን አበጥሬ
ተስፋዬን አንግቤ ባንቺ ፍቅር ንሬ

አቤት የኔ ጉጉት አቤት የኔ እምነት
ከራሴ ስጣላ ከራሴ ስሟገት

ልንገራት? ይቅርብኝ?........

ፈራ ተባ እያልኩኝ ምታዪኝ ይመስል እንዲያ ስሽኮረመም
ፎቶሽን እያየው በሳቅሽ ስታከም

ምን ያልሆንኩት አለ ለሰው ማይወራ
በከርቤ የማይተው በወይራ ማይጠራ።

በላብ ከወጣልህ ባህርዛፍ ታጠነው የሚል የሰው ምክር
አመት በዓል ሲመጣ እንዲ ያረገኝ ነበር።

ትዝ ይለኛል ቀኑ ጳጉሜ ላይ ነበረ
በአንድ የፅሁፍ መልዕክት ልቤ ተሰበረ።

እንባ ተናነቀኝ የማደርገው ጠፋኝ
ከወትሮ የተለየ የእዉነት በጣም ከፋኝ
ህይወት ጣዕም አጣ ፈፅሞ ከረፋኝ።

እንቅልፍን ጠላሁት ውሎዬ እና አዳሬ ፀሎት ብቻ ሆነ
ይሄው እስከዛሬ ባንቺ የቃል ክህደት ልቤ እየባከነ።

በአል በመድረሱ ምኞቱን ለመግለፅ ሰላምታ ቢሰጥም
ቁጣ ቁጣ ይለኛል በባህሩ ጀልባ ወዳንቺ ሲያሰጥም

እናም እናቴዋ

እኔና መስከረም ትዝታ የለንም ለሰው የሚነገር
መስከረምም ይጥባ እኔም ልቤን ልዳር።

OB'☀️ (Jadon)

@jadmasse25
@getem
@getem
👍4712😢8🔥3