ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እኔ_ነኝ
:
:
ትዝታ እና ተስፋን ድንበር ተከልሎ፤
በነገ እና ትናንት መሀል ድንኳን ተክሎ፤
ቀንበርን ሳይፈራ፤
ማቅ እና እጀ ጠባብ ለብሶ በየተራ፤
ለመላቅ ከቅድም፤
እራሱን ለመርታት እራሱን ሚቀድም።
እኔ ነኝ!


ተድላና ትካዜ ሚፈራረቁበት፤
ተንጋሎ የሚጓዝ ወደ ህልሙ አቀበት፤
ደጋን የማይወጥር ሾተልን የማይልስ፤
ፍላፃና ሎጋን በፍቅር ሚመልስ።
እኔ ነኝ!
:
:
አሜን ይሁን የሚል ክፉም ሆነ ደጉን፤
እኔ ነኝ ያ ምስጉን!

#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita

@getem
@getem
19👍11