ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አወራሽ ይመስል
ቁርጥ           ቁርጥ
ይላል ቃሌ ከስልኬ ሲሰፍር
አያድርስ ነው አቦ
ይጃጃሉትም የል ወንድ ልጅ ሲያፈቅር
ቁርጤን እንዳላውቀው እያዘላበድሽኝ
ወይ እሺ
ወይ እንቢ የሚል ቃል ሳይወጣሽ
       ድንገት አሳበድሽኝ
ጨርቅ መጣል ቀረኝ
           የገላዬን ሽፋን
እኔና ይህ ቀልቤ
            በትግል ተላፋን
ሰው እንዴት ከግሉ
ሰው እንዴት ከውሉ
                  ይላፋዋል ትግል
እሺ በይኝና ለክብርሽ ላገልግል።

ህይወት አይሉት ወይ ሞት
ቃሉ ተምታቶብኝ የአገባብ ፍቺው
      በይ አሳይኝ አንቺው
ከአፍሽ ላይ ቃል ይውጣ እየተሯሯጠ
  እቋቋመዋለሁ ወንድ ልጅ ቆረጠ
ቆርጫለሁና በምታወጪው ቃል
     እሺታን ማን ያውቃል
     እንቢታን ማን ያውቃል

#እስቲ_እንተዋወቅ!

ከንደገና መለስ
ወደኋላ ቀለስ
አሁን ለጠየኩሽ አይጠፋም 1 መልስ።

እውነቴን ነው ምልሽ
የበላኝን መዳፍ ደጋግሜ ሳከው
አገኘኋት ይላል ባንቺ የታወከው
ግራዬን
ወይ
ቀኜን....አላስታውሰውም
ብቻ ያዝኩሽ ይላል ባይታወቅ አንድምታው
ባይን ብቻ ፍቅር
ቀርቤ ሳላውቅሽ እንዴት ነው ምረታው
እንደ ፈሪ ዱላ መተንኮሶ ነው ልምዱ
መጣው ይላል አይንሽ እግሮችሽ ሲሄዱ
ቻው ይለኛል ጀርባሽ ሄዶ በዛው ሊቀር
እንዲህ ነው ሚያደርገው ሰው በሰው ሲፈቀር
ኩራት ጥግብ
ጅንን
እንደ እትጌ መነን........

እስቲ እንተዋወቅ!

ሳላውቅሽ ነው እንግዲ

እንቢታን ምጠይቅ እሺታን ምለምን
ሳይተዋወቁ ይቻላል እንደምን?
መብላቴን ሳላውቀው ታጥቤ የቀረብኩት
እኔው ነኝ እንግዳሽ ወጤን የረገጥኩት
የራሴን መስመር ልክ ላንቺ ላንዷ ብዬ የተተላለፍኩት።

አልጨረስኩም!

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍4515😱1