ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
     ( ሚስትህ የኔ እኮ ናት )

አገሬው ቢተቸኝ በገዛ ድግሴ ሳለሁ ተባርሬ ፤
ስቀህ ብታየኝም አንተ ተደስተህ ሳልፍ ተማርሬ ፤

አዎን ያንተው መውደድ የራስህ ያረካት ፤
ሳታገባት በፊት ለኔ ሚስቴ እኮ ናት ፤

      የምሬን ስነግርህ......

አብልጬ ምወዳት ከራሴ ከሁሉ ፤
ሚስትህ ሚስቴ ደሆነች ባያውቅልኝ ሁሉ ፤
የሰው ሚስት ተመኘ ይለኛል ሰው ሁሉ ።

ግዴለም ይበሉኝ እነሱ ያሻቸውን ፤
ቆርጠው ይቀጥሉ ያለ የሌለውን ፤

አንተ ግን አደራ እንዳትዘብተኝ ፤
ደርሰህ በነሱ ፊት እንዳትቦጭቀኝ ፤

ወዳጅን መቀማት ፤
በለሆሳስ ማጥቃት ፤
ሳይቆፍሩ መቅበር ፤
ያውም ባንድ ጀንበር ፤
ሙሾም ሳይወረድ ፤
ምነው ሳይረገድ ።

ሰሚ ባይሰማልኝ ባላቆም ጠበቃ፤
ይኸን ሁሉ ነገር አርገህ ስታበቃ ፤

ሚስቴን ቀማኝ ብለህ ብትሄድ አቤቱታ ፤
ለወናፍ አፍ ሁሉ ብታቀርብ ስሞታ ፤

የምሬን ነው ምልህ ዳኛውም አይፈርድም ፤
እኔ አልከሰስም እኔ አልወቀስም ፤

ከቻልክ የሚስቴ ባል ምላስህን ሰብስብ ።

#ኢዮብ_አሰፋ
@yomin1_2

@getem
@getem
@getem
😁46👍4119😢10🤩1