ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ቅኔ ናት ሀገሬ !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።

ጠፍጥፎ የሰራት ፥ ያበጃት ይመስል

ይሄ የቀለም ቀንድ ፥ የህሊና ስንኩል

ትፈርሳለች ይላል ፦

ሟርቱን ከሀገሬ ደጅ ፥ በራፏ ላይ ሊጥል ።

ደግሞም ...

ወዲህ ለቅርሻቱ ፥ ሊጠቅስ ማስረጃ

ምሳሌ አስታኮ ፥ ሊያቆም የቃል ፍርጃ!

መጥሀፉን ሊያብል ፥ ቃልኪዳኗን ሽሮ

ዓይኑ ሩቅ ማትሮ ...

ሶሪያን ይጠራል ፥ ድንበሯን ተሻግሮ ።

# እኔ 

የቃል ግንዝ አይጥ ፥ የጠቆረ ዶሮ

የሚከረፋ ደም ፥ የሟርት እንጉርጉሮ

ትፈርሳለች የሚል ፥ የምሁር ደንቆሮ

በሚዘራው ክፋት ፥ በሚያቆየው በደል 

ልቤ ሳይሸነገል !

ፈገግ ብዬ አልፋለሁ ፥ ዥልነቱን ላቀል ። 

አትፈርስም ሀገሬ !

የቃል ኪዳን ቅጥሬ.. .

ምን ዳሷ ቢያጋድል ፥ መሰረቷ ዘሞ 

ምንም ታላቅ ባትሆን ፥ እንዲያ እንደቀድሞ

መቶ ቅጠል በጣሽ ፥ ሚልዩን ደፍተራ

እልፍ ባለ ጋኔን ፥ የእርኩሰት ደመራ 

ልበትናት ብሎ.. .

በየ አዳራሹ ... ቢፎክር ቢያቅራራ

ማንነቷን ሊያሽር ...

ንጉስ ብረት ይዞ ፥  በሰይፍ ቢሸልል

ሀገሬ ቢላል ናት ...

በስጋዋ ቁስል ፥ እምነቷን የማጥል ።

አትፈርስም ኢትዮጵያ!

የአዳም መጀመሪያ.. .

ጠኔ ክንዱ ቢያይል ፥ ውሀ ጥም ቢያደብናት

የማጣት ቀንበሩ ፥ ወገቧን ቢያጎብጣት

የወደቀች ብትመስል ፥  ከሁሉ ተናንሳ

በርባን ከስር ወጥቶ ፥ ደንፍቶ ቢያገሳ 

ዓለሙ ሊሳለቅ ፥ እንጨቱን አጣምሮ ፥ መስቀሉን ቢያነሳ

ሀገሬ መሲህ ናት ... 

የክርስቶስ ሀምሳል ፥ ቀብረናታል ሲሉ ፥ ሞታ ምትነሳ ።

አትፈርስም!

አትፈርስም !

ኢትዮጵያ አትፈርስም...

ቢፈጡሩ ጥያቄ  ፥ የሰይጣን ካህናት ፥ ሳንቲም እያነሱ

የዘረጉት ወጥመድ ...

የሚምሱት ጉድጓድ ፥ ሀገሬን ሳይጥላት ፥ ይተርፋል ለነሱ።

#አዎን ማህደር ናት !

ማንም እሳት ቢጭር ፥ ማገዶ ቢከምር ፥ ሊያከስላት አሳሮ 

ሀገሬ ሚስጥር ናት !

የፈጣሪ ቅኔ ፥ የስንኞች ግማድ ፥ የፍቅር ቋጠሮ 

አፍራሿ ይፈርሳል.. .

በለኮሰው እሳት ፥ በቁሙ እያለቀ ፥ አካሉ ቀንጭሮ ።

@getem
@getem
@getem
👍1