ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አቤልና ቃዔል#

የነተበ ኮዳ፥ቀረ'ሽ እፍኝ ዉሃ
ይዞ እንደመሸፈት፥የጋሻ ቀርቀሃ
እንደማሳደድ ጥላን
እንደማጥመድ ነፋስን
እንደዚያ ነዉ፥ከራስ ጋር መፋለም
ጣይና ወዳቂ የለም፤

እንዉረድ ያለዉ ቀን
ቃዔል መንተያዉን
እግዜር መዉረጃዉ ላይ፥አሽዋ ቢከምር
ቴዎድሮስ በሽዋ ላይ፥ባልዘመተ ነበር፤

አቤል ሲገፈተር፥ከጊዮን አናት ስር
ያኔ ደሙን ጠጥታ፥እናት የኩሽ ምድር
ይሄዉ ዛሬም ድረስ፥መች ምጧ ቀለለ
በስንዴዋ ማሳ ፥እንክርዳድ በቀለ
አገር ሙሉ አቤል
አገር ሙሉ ቃዔል
አንዱ ባንዱ ሲያሴር
አንዱ ባንዱ ሲያብል
ለነተበዉ ኮዳ፥ ለእንክርዳዱ ሙልሙል።


#መታሰቢያነቱ በአሁኑ ሰዓት በሃገራች ለሚታኮሱት የልጅ አበባዎች

#መሪጌታ
@lula_al_greeko
@getem
@getem